Synergy Healthcare Consultancy Ethiopia/ሲነርጂ የውጪ ሃገር ህክምና አገልግሎት

  • Home
  • Ethiopia
  • Addis Ababa
  • Synergy Healthcare Consultancy Ethiopia/ሲነርጂ የውጪ ሃገር ህክምና አገልግሎት

Synergy Healthcare Consultancy Ethiopia/ሲነርጂ የውጪ ሃገር ህክምና አገልግሎት Synergy is a private healthcare consultancy firm, that focuses on helping patients who are referred abroad to seek treatment for their conditions.

12/05/2017

የህፃን ልጅ አእምሮ በ ሰከንድ 1000 አዳዲስ የነርቭ ግንኝነቶችን ይፈጥራል! ለዛም ነው የ መጀመሪያዎቹ 1000 ቀናት ለ ህፃን ልጅ ወሳኝ የሆኑት! ልጅዎትን #ያብሉያጫውቱይንከባከቡ http://uni.cf/earlymoments

11/05/2017

በየቀኑ ካለን ጊዜ ውስጥ 5 ደቂቃ በመመደብ የሚገኙ የደስታና የጤና ጥቅሞች..
በየቀኑ ስራችንን ለማከናወን ከምንጠቀመው እያንዳንዱ ጊዜ ውስጥ 5 ደቂቃ በመመደብ ጤናማ እና ደስተኛ የሚያደርጉ ጠቃሚ ነገሮችን ማግኘት እንችላለን።
እነዚህ በየቀኑ የሚመደቡ 5 ደቂቃዎች ለሰዎች ስለሚሰጧቸው የደስታና የጤና ጥቅሞች በምርምር የተደገፉ መረጃዎች ቀርበዋል፡፡
1. በየቀኑ ለአምስት ደቂቃ መሮጥ በህይወት መኖርን በሶስት ዓመት ይጨምራል፡፡
በየቀኑ ለአምስት ደቂቃ መሮጥ አስቀድሞ የመሞት እድልን በመቀነስ የመኖር እድልን ይጨምራል፡፡
በ55 ሺህ ወንዶች እና ሴቶች የተጠና ጥናት በየቀኑ የሚሮጡ ሰዎች ከማይሮጡት በአማካይ 30 በመቶ የመሞት እድላቸውን ይቀንሳሉ፡፡
ለልብ ህመም የመጋለጥ እድላቸውም የሚሮጡት ሰዎች ከማይሮጡት በ45 በመቶ ዝቅ ያለ ነው ብሏል ጥናቱ፡፡
የሚያጨሱ እና ክብደታቸው የጨመሩ ሰዎችም በየቀኑ አምስት ደቂቃ ቢሮጡ ጥቅሙ ከፍተኛ ነው ተብሏል፡፡
በርካታ ጥናቶች እንደሚሉት አነሰም አደገም በየቀኑ መሮጥ የጤና ጥቅሙ ከፍተኛ ሲሆን፥ አዛውንቶች ለ15 ደቂቃ ያህል እርምጃ ቢራመዱ 20 በመቶ የመሞት እድላቸው ይቀንሳል፡፡
2. በስራ ቦታ አካባቢ በየሰዓቱ ለአምስት ደቂቃ መንቀሳቀስ ድብርትን ያስወግዳል፤ ጤናማ ያደርጋል፡፡
ብዙ ጊዜ ተቀምጠው የሚያሳልፉ ሰዎች ለውፍረት፣ ለስኳር በሽታ እና ሌሎችም በመቀመጥ ብዛት ለሚመጡ የጤና ቀውሶች ይጋለጣሉ፡፡
በስራ ሰዓት ሁሉ ባሉት ጊዜያት ለአምስት ደቂቃ መንቀሳቀስ ድብርትን ያስወግዳል፣ ድካምን በማስወገድ ብርታትን መጨመርና ሌሎችም አዕምሯዊ ጥቅሞች አሉት ተብሏል፡፡
3. ስራን ከተቀመጠው ጊዜ አምስት ደቂቃ ቀድሞ መጨረስ እና አለማዘግየት
ሰዎች በየቀኑ መስራት የሚገባቸውን ስራ ከማዘግየት ይልቅ የጊዜ ሰሌዳ

ህጻናት እንደ ስማርት ስልክ ያሉ መገልገያዎችን እንዲጠቀሙ ማድረግ የአፍ መፍቻ ጊዜያቸውን ያዘገያል- ጥናትህጻናት ልጆችን ለማባበልም ይሁን እንዲጫወቱ ለማድረግ ስማርት ስልካችንን እና ሌሎች ...
11/05/2017

ህጻናት እንደ ስማርት ስልክ ያሉ መገልገያዎችን እንዲጠቀሙ ማድረግ የአፍ መፍቻ ጊዜያቸውን ያዘገያል- ጥናት

ህጻናት ልጆችን ለማባበልም ይሁን እንዲጫወቱ ለማድረግ ስማርት ስልካችንን እና ሌሎች የኤሌክትሮኒክስ መገልገያዎችን መስጠት የተለመደ ነው።
ይህ ተግባር ግን ትክክል አይደለም፤ ምክንያቱ ደግሞ ህጻናት ልጆች የቴክኖሎጂ ቁሳቁሶች ላይ ጊዜያቸውን እንዲያሳልፉ ማድረግ የአፍ መፍቻ ጊዜያቸውን ስለሚያዘገይ ነው ይለናል ከሰሞኑ የወጣ ጥናት።
ጥናቱ ከ6 ወር እስከ 2 ዓመት መካከል ያሉ ህጻናት እንደ ስማርት ስልክ፣ ታብሌት እና ኤሌክትሮኒክስ ጌሞች ላይ በሚያሳልፉት ጊዜ መጠን የአፍ መፍቻ ጊዜያቸውን እየዘገየ ይሄዳል የሚለውን አመልክቷል።
በካናዳ ቶሮንቶ የህጻናት ሆስፒታል የተካሄደው ጥናት ላይ 900 ህጻናት እንዲሳተፉ የተደረገ ሲሆን፥ ልጆቹ እድሜያቸው 1 ዓመት ከ6 ወር እስኪሞላ ድረስ ምን ያክል ጊዜን ከሞባይል እና ሌሎች የኤሌክትሮኒክስ መገልገያዎች ጋር እንደሚያሳልፉ ወላጆቻቸው ተጠይቀዋል።
በመቀጠልም ተመራማሪዎቹ ህጻናቱ በ1 ከ6 ወር እድሜያቸው የመናገር ችሎታቸው እና ቋንቋን የመጠቀም ክህሎታቸው ምን ያክል ጨምሯል የሚለውን ለመለየት የሚረዳ መሳሪያ ተጠቅመው ለክተዋል።
በዚህም ህጻናቱ ከሌሎች ትኩረት ለማግኘት ሲሉ ቃላቶችን እንዴት አንድ ላይ ጠምረው ይጠቀማሉ፤ እንዲሁም ምን ያክል ቃላትን ይጠቀማሉ የሚለውን አይተዋል።
በጥናቱ ላይ ከተሳተፉ ህጻናት ውስጥ 20 በመቶ ያክሉ በቀን ውስጥ በአማካኝ 28 ደቂቃ ያክል በስማርት ስልኮች እና ሌሎች መገልገያዎች ላይ ጊዜያቸውን እንደሚያሳልፉ ጥናቱ ለይቷል።
ህጻናቱ በስክሪን ላይ የሚያሳልፉት ጊዜ በ30 ደቂቃ እየጨመረ በሄደ ቁጥር አፍ የመፍቻ ጊዜያቸው የመዘግየት እድል ደግሞሞ በ49 በመቶ እየጨመረ እንደሚሄድም ተመራማሪዎቹ በጥናታቸው ውጤት ላይ አስፍረዋል።
በካናዳ ቶሮንቶ የህጻናት ሆስፒታል የአጥኚዎች ቡድን መሪ ዶክተር ካትሪን በይርከን፥ “ተንቀሳቃሽ የሆኑ የኤሌክትሮኒክስ መገልገያዎች የህጻናት የመግባባት ጊዜ ላይ መዘግየትን እንደሚያስከትል የለየው ጥናት እስካሁን ከተሰሩት በአይነቱ የመጀመሪያ ነው” ብለዋል።
“ሆኖም ግን የጥናቱን ውጤት አሁንም በጥልቀት ማየት ይኖርብናል፤ ምክንያቱ ደግሞ አሁን ያገኘነው ውጤት ገና የመጀመሪያ ምልከታ ስለሆነ ነው” ሲሉም ተናግረዋል።
እንደ አውሮፓውያኑ አቆጣጠር በ2013 የወጣ ሪፖርት እንደሚያመለክተው እንደ ሞባይል ስልክ ያሉ ተንቀሳቃኝ የኤሌክትሮኒክስ መገልገያዎችን የሚጠቀሙ ህጻናት ቁጥር በ2011 ከነበረበት 10 በመቶ ወደ 40 በመቶ ከፍ ብሏል።
አሁን ላይ ደግሞ የስማርት ስልኮች በዓለም ዙሪያ በብዛት ጥቅም ላይ መዋል መጀመራቸውን ተከትሎ ይህ አሀዝ በእጥፍ ሊጨምር እንደሚችል ተገምቷል።
ታዲያ ወላጆችም ልጆቻቸው እንደ ስማርት ስልክ፣ ታብሌት እና ሌሎች የኤሌክትሮኒክስ መገልገያዎች ላይ የሚያሳልፉትን ጊዜ መገደብ መልካም ነው፤ ልጆች ከኤሌክትሮኒክስ መገልገያዎች ውጭ ተፈጥሯዊ በሆነ መልኩ እንዲጫወቱም ማድረግም ይመከራል።
ምንጭ፦ http://edition.cnn.com/

View the latest news and breaking news today for U.S., world, weather, entertainment, politics and health at CNN.com.

የዐይናችን ቀለም የመለየት አቅም (color blindness)ምን ያህል ነው?? የሚታያችሁን ቁጥር Comment አድርጉ
08/05/2017

የዐይናችን ቀለም የመለየት አቅም (color blindness)ምን ያህል ነው?? የሚታያችሁን ቁጥር Comment አድርጉ

08/05/2017

አስማ ምንድን ነው? እንዴትስ መከላከል እንችላለን? ህክምናውስ ምን ይመስላል?

አስማ በአማርኛ አስም፣ የአስም በሽታ ወይንም የአስም ህመም በመባል ይታወቃል፡፡ አስማ በህፃናት ሆነ በአዋቂዎች ላይ ሊከሰት ይችላል፡፡ አስማ የአየር ቧንቧዎችና የሳምባ ህመም ነው፡፡ አስማ የሚነሳው የሳምባና የአየር ቧንቧ ክፍሎች በቀላሉ ሲቆጡና በአየር ውስጥ በሚገኝ ነገር ሲተነኮሱ ነው፡፡ አስማ ያለበት ሰው የሚያጋጥሙት የተለያዩ ነገሮች ህመሙን ሊቀሰቀስበት ይችላል፡፡ እነዚህንም ከሚያጠቃልሉት ነገሮች፡
• ጉንፋን • የሲጋራ የማገዶ ጭስ • የአየር ብክለት • የሳር ብናኝ ወይም የአበባ ሽታ • አቧራ • እንሰሳት ወይንም የቤት እንሰሳት ብናኝ
• ቅዝቃዜ ወይንም የአየር መለዋወጥ • የተለያዩ ሽታዎች ሽቶ፣ ቀለም፣ ፀረተባይ መድሃኒቶች፣ እጣን ወይንም ሰንደልና የመሳሰሉት ናቸው፡፡
እነዚህ ሁሉ ነገሮች የአስማን ምልክቶች ሊያባብሱ ይችላሉ፡፡ ሌሎች አስማን ሊያባብሱ የሚችሉ ነገሮች
• የእስፖርት እንቅስቃሴ ወይንም ከባድ የጉልበት ስራ • ሳቅ ወይንም ለቅሶ • ድንጋጤና ብስጭት • አንዳንድ የምግብ አይነቶችን ይጨምራል፡፡
አስማ በቤት ውስጥ ወይንም ከቤት ውጪ ሊነሳ ይችላል ቤቶች በሮቻቸው አብዛኛውን ጊዜ ዝግ እንዲሆን ከተሰራ እቤት
ውስጥ ያሉ አስም የሚቀሰቅሱ ነገሮች ቤት ውስጥ ታፍነው አስማን ሊያባብሱ ይችላሉ፡፡ ከእነዚህም የአስማ ምልክቶች፡
• ጊንፋን • ሳል ድምፅ የሚያሰማ ትንፋሽ ወይንም ሲርሲርታ • ደረት ላይ የመወጠር ወይንም የመጨነቅ ስሜት
• የመተንፈስ ችግር • ፈጣን ትንፋሽ (ቁናቁና መተንፈስ) የሚጨመሩ ሲሆን አብዛኛውን ጊዜም ትኩሳት የለውም፡፡ እነዚህ ምልክቶች የሚከሰቱት የአየር ቧንቧዎች በመጥበባቸው የተነሳ አየር ወደሳንባ ውስጥ እንደልብ ሊገባና ሊወጣ ስለማይችል ነው፡፡
አብዛኛውን ጊዜ አስማ የሚከሰተው እያሰለሰ ወይንም ፋታ አየሰጠ ነው፡፡ በአመቱ ውስጥ የተወስነ ወቅት ላይ ወይንም በምሽት አስማ ሊስብ ይችላል፡፡ አስማ በልጅነት (በህፃንነት) ጀምሮ አስከ እድሜ ልክ ሊዘልቅ ይችላል፡፡ አንዳንድ አስማ ያላቸው ሰዎች በቤታቸው ወይንም በዙሪያቸው አስማ ያለበት ሰው ይኖራቸዋል፡፡ ሆኖም ግን አስማ ተላላፊ በሽታ አይደለም፡፡ አስም ከአንድ ሰው ወደሌላ ሰው በነዚህ አይተላለፍም፤
• አንድን ሰው በመንካት • ምግብ አብሮ በመብላት • ወይንም አብሮ በመኖር
አስማ ያላቸው ሰዎች በሳምባቸው በተፈጥሮው አየር ውስጥ ባሉ ነገሮች በቀላሉ የሚቆጣ ይሆናል፡፡ አስማ ያላቸው ሰዎች የሚከተሉት ምልክቶች ካሉዋቸው ሀኪም ማማከር ይገባቸዋል፡፡
• ብርቱ ሳል • አይናቸው እምባ ሲዘራ የጉሮሮ መከርከርና የማይቋረጥ ንፍጥ ሲተነፍሱ • ስር ስር የሚል ድምፅ የሚሰማ ከሆነና
• የመተንፈስ ችግር ከገጠማቸው ሀኪም ዘንድ መሄድ ያስፈልጋቸዋል፡፡
አንዳንድ ጊዜ የበረታ አስም አስጊ ደራጃ ሊደርስ ይችላል፡ ስለዚህ የሚከተሉት ምልክቶች ከተከሰቱ በድንገተኛ ሀኪም ዘንድ መሄድ ያስፈልጋል፡፡
• የደረት ላይ ጭንቀት (መወጠር) • በጣም ፈጣን አተነፋፈስ • ከንፈርና ጥፍር ቀለም መለወጥ (መጥቆር) • የሰውነትን የጎን አጥንት በሚተነፍሱበት ወቅት ማየት ሲቻል • የአስም መድሃኒቶች አልሰራ (አላስታግስ) ካሉ • ከአራት ሰዓት አንድ ግዜ በላይ መድሃኒት መውሰድ ካስፈለገ፡፡
ሀኪም ከመረመረና አስም መሆኑ ከተረጋገጠ በኋላ መድሃኒቶች ይታዘዛሉ፡፡ መድሃኒቶቹ የአየር ቧንቧዎችን ለመክፈት የሚረዱ ናቸው፡፡ ሳሉን ለማስታገስም ትንፋሹ በቀላሉ እንዲገባና እንዲወጣ ይረዳሉ፡፡ አስማን ለማከም የተለያዩ አይነት መድሃኒቶች ይታዘዛሉ፡፡ እነዚህ የተለያዩ መድሃኒቶች በተለያየ መንገድ የአየር ቧንቧዎችን ይከፍታሉ፡፡ አንዳንድ ጊዜም ካንድ በላይ መድሃኒቶች አንድ ላይ ይታዘዛሉ (ይወሰዳሉ)፡፡ አንዳንድ መድሃኒቶች ለጥቂት ቀናት ብቻ የሚታዘዙ ሲሆን አንዳንዶቹ በረጅም ጊዜ ይወሳዳሉ፡ አንዳንድ ጊዜም በቀን ውስጥ በርከት ያለ ጊዜ መውሰድ ይኖርባቸዋል፡፡መድሃኒቶቹ በተለያየ መንገድ ይወሰዳሉ፤
• የሚጠጡ ሽሮፓች • የሚዋጡ ኪኒኖች • በትንሽ መያዣ ውስጥ በመንፋት ለሳንባዎ በሚረዱ ነገሮች ይገኙበታል፡፡
የሚተነፍሱት ወይንም የሚነፉት መድሃኒቶች Iንሄለርስ ይባላሉ፡፡ ለጨቅላ ህፃናትና በጣም በጠና ለታመሙ የአስም በሽታዎችንም በሚሽን የሚሰጥ መድሃኒት ይታዘዝ ይሆናል፡፡ ይህም ማሽን የአየርና መድሃኒቱን ቀላቅሎ ወደ ሳምባ ያስገባል፡፡ የዚህ ማሽን ስም ኒቡላይዘር ይባላል፡፡
የተወሰኑ የአስም መድሃኒት ስሞች ከዚህ በታች የሚጠቀሱት ናቸው፡ እነሱም
• አልቡቴሮል • ቲዮፊሊን • ፕሬድኒሶን ወይንም ፕርሬድሶሎን ወይንም ፕሬድንስሎን ወይንም ስቴሮይድ ናቸው፡፡
እነዚህ መድሃኒቶች በተለያየ ስም ሊሸጡ ይችላሉ፡፡ ሀኪሞች የሚወስዱትን መድሃኒቶች አይነቶች (ስሞች) ማወቅ ይፈልጋሉ፡፡ ስለሆነም • ምክንያቱም ስለህመሙ ሁኔታ የበለጠ ለሃኪሙ ሊያስረዱ ይችላሉና ነው፡፡ • አዚህ የመድሃኒቶቹን ስሞችና መድሃኒቶቹን ወይንም ማስቀመጫ ብቃጦቹን ሃኪም ቤት ይዞ መሄድ ይገባል፡፡
አስም ያለባቸው ሰዎች
• አስማቸውን ከሚያባብስ ነገር መራቅ አለባቸው፡ • የአስማን ምልክቶችም መለየትና ማወቅ ይኖርባቸዋል • አስም ሲጀምራቸውም በቶሎ መድሃኒቶቻቸውን መውሰድ መጀመር አለባቸው፡፡ የመድሃኒቱ አወሳሰድም ሃኪም ባዘዘው መሰረት መሆን አለበት፡፡ ሌሎች የአስም ህመምተኞች ሊረዱ የሚችሉ ነገሮችም
• ማረጋጋትና በተቻለ መጠን ንህመምተኛውን ማዝናናት • በቀስታና በርጋታ እንዲተነፍሱ ማበረታታት • አክታውን ለማለዘብ እንዲሁም በርካታ ፈሳሽ መጠጣት ያስፈልጋል፡፡
ቤት ውስጥ የሚፈጠሩ እንደ አቧራና ሻጋታ የመሳሰሉ ነገሮችን አስማን ሊያባብሱ ይችላሉ፡፡ ስለዚህ የአስም ታማሚ ያለበት ቤተሰብ ቤቱን ለህመምተኛው እንዲስማማ ለማድረግ መጣር የገባዋል ህመምተኛው ቤት በማይኖርበት ወቅት ቤቱን ማጽዳትና ማናፈስሊረዳ ይችላል፡፡
ቁርጥራጭና ያረጁ ምንጣፎችን ማስወገድ፡፡ እነዚህ ምንጣፎች ማስወገድ ካስቸገረዎ ቤቱን በየእለቱ ማፅዳት (ቫክዩም) ማድረግ፡፡
በውሃና በመወልወያ ወለሎችን ማፅዳት፡፡ የቤት እቃዎችን ቀላልና እንዳያስቸግሩ ማድረግ፡፡ የቤት እቃዎችን አቧራ እንዳይዙ በየጊዜው መወልወል ያስፈልጋል፡፡
መስኮት አጠገብ የሚገኙ ሻጋታዎችን ለማስወገድ ብሊች (በረኪና) ነገር መጠቀም መጋረጃዎችን ወይንም ፀሃይ መከለያዎችን የሚታጠቡ አይነት እንዲሆኑ ማድረግ ቤቱንም በሚገባ ማናፈስ ያስፈልጋል፡፡ የሲጋራና የእጣን ጭስ እንዳያገኘው ማድረግም ይገባል ጪስን አስማ ከያዘው ሰው ማራቅ ያስፈልጋል፡፡ የቤት እንስሳትንም ከአስም በሽታ ማራቅ ያስፈልጋል
አስማ ያለበትን ሰው መኝታ ቤቱን፤
• የአልጋ ልብስ፣ ብርድ ልብስና፣ አንሶላዎች በሳምንት አንድ ቀን በፈላ ውሃ ማጠብ
• ትራስና ብርድ ልብስና አንሶላዎችን በሳምንት አንድ ቀን በሞቀ ውሃ ማጠብ፡፡
• ትራስና ብርድ ልብስ፣ ጥጥ ወይንም ሱፍ ካልሆኑ ነገር የተሰሩ እንዲሆኑ ማድረግ ፍራሽና ትራሱን ጨርቅ ከማልበስ በፊት በላስቲክ መጠቅለል፡፡
• እንደዚሁም አስማ ያለበት ህፃን ከሆነ ከእንሰሳት ውጤት እየጠቀጠቁ መጫዎቻቸውን ወይንም አሻንጉሊቶችን ከህፃኑ ማራቅ ያስፈልጋል፡፡

የማህፀን ውስጥ ዕጢ መንስኤና ምልክቶቹ :-የማህፀን ዕጢ የምንለው የካንሰርነት ባሕርይ የሌለው የማሕፀን ውስጥ እባጭ ሲሆን በአብዛኛው የሚከሰተው በወጣትነት ዕድሜ ላይ ነው፡፡ የማህፀን ውስጥ...
04/05/2017

የማህፀን ውስጥ ዕጢ መንስኤና ምልክቶቹ :-
የማህፀን ዕጢ የምንለው የካንሰርነት ባሕርይ የሌለው የማሕፀን ውስጥ እባጭ ሲሆን በአብዛኛው የሚከሰተው በወጣትነት ዕድሜ ላይ ነው፡፡ የማህፀን ውስጥ ዕጢ ወደ ማኅፀን ካንሰርነት የመለወጥ ዕድሉ እጅግ በጣም አናሳ ነው፡፡
የማሕፀን ዕጢ ከማሕፀን ግድግዳ ጡንቻዎች የሚነሳ ሲሆን የሴሎች ጤናማ ባልሆነ ሆኑታ ሲከፈሉ የሚመጣ ሆኔታ ነው፡፡ ይህ የማሕፀን ዕጢ በፍጥነት የሚያድግ ወይንም በዝግታ የሚያድግ ሊሆን ይችላል፡፡ አንዳንድ ጊዜም ተመልሶ በራሱ ሊጠፈም ይችላል፡፡
የማሕፀን ዕጢ በሴቶች ላይ እጅግ የተለመደ በመሆኑ ምክንያት ከ4 ሴቶች ሦስቱ በሕይወት ዘመናቸው የማሕፀን ዕጢ እንደሚኖራቸው ጥናቶች ያሳያሉ፡፡ ነገር ግን ምልክት ስለማያሳዩ እንዳላቸውም የማወቅ ዕድል የላቸውም፡፡ በአብዛኛው የሚገኘው በድንገት በሚደረግ ምርመራ ነው፡፡
>> ምልክቶቹ -
የማኅፀን ዕጢ በአብዛኛው ምንም ዓይነት ምልክት የማያሳይ ቢሆንም በአንዳንድ ሰዎች ላይ የሚከሰቱ ምልክቶች እንዚህ ናቸው፡፡
• ከፍተኛ የሆነ የወር አበባ መብዛት
• ከሰባት ቀናት በላይ የሚቆይ የወር አበባ ማየት
• ማሕፀን አካባቢ ግፊት መሰማት ወይንም ሕመም
• ቶሎ ቶሎ የውሃ ሽንት መምጣት
• የሆድ ድርቀት
• የጀርባ እና የዕግር ሕመም ስሜት
• አልፎ አልፎ ከፍተኛ የሆነ ሕመም (አጣዳፊ) የሚያስከትል ሲሆን ይህም የሚሆነው የደም ዝውውር በሚቀንስ ጊዜ/በሚቋረጥ ጊዜ ነው፡፡
የማሕፀን ዕጢ ለምን ይከሰታል፡፡ ይህ ነው የሚባል ዕርግጥ ምክንያት የሌለው ቢሆንም ጥናቶች የሚያመለክቷቸው ከሆርሞኖች እና የጀኔቲክ ሁኑታዎች ጋር ተያያዥነት እንዳላቸው ነው፡
>> ለማሕፀን ዕጢ ተጋላጭነት የሚጨምሩ ሁኔታዎች -
• ከዘር፡- እናት ወይንም እሕት የማሕፀን ዕጢ ወደ ዘር ካላቸው ተጋላጭነትን ይጨምራል፡፡
• ጥቁር ዘር፡- ጥቁር ሴቶች በአብዛኘው ተጋላጭነታቸው ይጨምራል፡፡
• በልጅነት የወር አበባን ያዩ ከሆነ እና አመጋገብ ናቸው፡፡
የማኅፀን ዕጢ ለከፋ የጤና ችግር የሚዳርግ ባይሆንም የደም ማነስ እና ምቾት ማጣትን ግን ሊያስከትል ይችላል፡፡
>> የማሕፀን ዕጢ እና እርግዝና -
የማሕፀን ዕጢ በአብዛኛው እርግዝናን የማይቃረን ቢሆንም አንዳንዴ ዕጢው በሚገኝበት ቦታምክንያት በጥቂት ሰዎች ላይ እርግዝናን እንዳይፈጠር መንስዔ ይሆናል፡፡ ይህ በመሆን ጊዜ ሐኪምን በማማከር ከእርግዝና በፊት መደረግ ያለባቸውን ቅድመ ሆኔታዎች ማድረግ ተገቢ ነው፡፡
>> ሐኪምዎን ማማከር የሚገባዎ መቼ ነው ?
• የማያቋርጥ የማሕፀን አካባቢ ሕመም ካለ
• ከፍተኛ ሕመም ያላቸውና በብዛት የሚያስቸግሩ የወር አበባ ጊዜያት
• ከወር አበባ ፅዳት ውጪ የደም መፍሰስ
• በግብረ ስጋ ግኝኑነት ጊዜ የሕመም ስሜት ከተሰማዎተግ
• የሆድ ዕብጠት ካለዎዘ
• የውኃ ሽንትን ማስወገድ መቸገር
• እጅግ ከፍተኛ የሆነ ድንገተኛ የማኅፀን አካባቢ ሕመም ካለዎትና ከፍተኛ የደም መፍሰስ የሚኖር ከሆነ በአፋጣኝ ወደ ሐኪም እንዲሄዱ ይመከራል፡፡

03/05/2017
02/05/2017

የጡት ካንሰር የቀዶ ጥገና ሕክምና (ላምፔክቶሚና ማስቴክቶሚ)
የጡት ካንሰር ያለባቸው Aብዛኛዎቹ ሴቶች የቀዶ ጥገና ሕክምና ማድረግ ይኖርባቸዋል፡፡ Aብዛኛው ካንሰር በቀዶ ጥገና ሊወገድ ይችላል፡፡ የቀዶ ጥገናውን ዓይነት Eርስዎ ያሉበት ሁኔታ ወሳኝ ነው፡፡ ይህም የካንሰሩን Eጢ መጠንና ካንሰሩ Eየተሰራጨ ነው Aይደለም የሚሉትን ያገናዝባል፡፡ ቀዶ ጥገናውን ለማድረግ ደግሞ የEርስዎና የሐኪሙ መስማማትም ወሳኝ ነው፡፡ ቀዶ ጥገና ከማድረግ በፊት በሽተኞች የሁለተኛ ሀኪም Aስተያየት መውሰድ የተለመደ ነው፡፡
የቀዶ ጥገናን ክንውን ለማስረዳት ብዙ የAገላለጽ ዘይቤዎች Aሉ፡፡ ነገር ግን በዋነኛነት የሚታወቁት ሁለት ዓይነቶች ብቻ ናቸው፡በላምፔክቶሚ ቀዶ ጥገና ካንሰራማውን ምርቁዝና (lump) ከባቢውን ያሉትን ቲሹዎች ማስወገድ ነው፡፡ ስለዚህ Aካል ተቆርጦ Aይወጣም፡፡ ይህ ቀዶ ጥገና የጡቱን Aካልም ሆነ በተፈጥሮ ያለውን መልክ Aይቀይረውም፡፡ የላምፔኬቶሚ ቀዶ ጥገና ክንውን Aንዳንዴ የጡት ነፍስ Aባት ወይም Aዳኝ ተብሎ ይጠራል፡፡
ባንጻሩ የማስቴክቶሚ ቀዶ ጥገና በAጠቃላይ የጡቱን Aካል ቆርጦ ማስወገድ ነው፡፡ የበሽተኛዋ ምርጫ ከሆነ ከማስቴክቶሚ ቀዶ ጥገና በኋላ ጡቱን Eንደገና መገንባት ይቻላል፡፡ በላምፔኬቶሚም ሆነ በማይሴክቶሚ ቀዶ ጥገና ሊምፍ ኖዶች (lymp nodes) ተቆርጠው ሊወጡ የሚችሉት የተለየ ቀዶ ጥገና በማድረግ ነው፡፡ ከቀዶ ጥገና በማስከተል ሌላ ተጨማሪ ሕክምና ማለትም Eንደሆርሞናል ቴራፒ (hormonal therapy) ወይም ኬሞቴራፒ በመስጠት በሰውነት ውስጥ የካንሰሩን ስርጭት ለመቋቋም ይቻላል፡፡
ካንሰሩ ተስፋፍቶ ወደሌላ የሰውነት ክፍሎች የተሰራጨ ከሆነ ካንሰርን ለማስወገድ የሚጠቀምበት የሕክምና ዘዴ ማስቴክቶሚ ይባላል፡፡ ቀዶ ጥገና ከመደረጉ በፊት በAካል የተስፋፋውን ካንሰር በኪሞቴራቢ ማሟሸሽ ከተቻለም የላምፔኬቶሚ ቀዶ ጥገና ዘዴ Aማራጭ ይሆናል፡፡ Aነስተኛ የሆነ የጡት ካንሰር (ማለትም ከAራት ሴንቲሜትር ወይም በታች) የሆነ በማስቴክቶሚ ወይም በላምፔክቶሚ በተጨማሪ በጨረራ (Radiation) ሕክምና መጠቀም Aብዛኛውን ጊዜ ውጤታማ የቀዶ ጥገና ሕክምና ነው፡፡
ሁለቱም የቀዶ ጥገና ይዞታዎች መልካምና Aስከፊ ውጤት Aላቸው፡፡ ለምሳሌ የላምፔክቶሚ የቀዶ ጥገና መንገድ ጡቱ Eንዳለ ሆኖ Eንዲቆይ ሲረዳ ግን ከ6 Eስከ 7 ሳምንታት የሚፈጁ ቀዶ ጥገናው ከተደረገበት ቀን Aንድ ወር በኋላ ጀምሮ የጨረራ ቴራፒ (Radiation therapy) በየቀኑ መደረግ ይኖርበታል፡፡ ባንጻሩ ግን በማስቴክቶሚ ቀዶ ጥገና ሕክምና ሙሉ ጡት ተቆርጦ ስለሚወጣ የካንሰሩ መጠን ይቀንሳል፡፡ ነገር ግን ጡት Eንደገና የመስራት ወይም ያለመስራት ውሳኔ የበሽተኛዋ ምርጫ ይሆናል፡፡ ምርቁዙ Aንስተኛና ትንሽ የጡት ካንሰር ያላቸው በሽተኞች የቀዶ ጥገና Aማራጫቸው ላምፔክቶሚ ሲሆን ግን በራሳቸው የግል ፍላጎትም ሆነ ምክንያት የማስቴክቶሚ ቀዶ ጥገና Eንዲደረግላቸው ሊመርጡ ይችላሉ፡፡ ሐኪምዎ ስለሁለቱም የቀዶ ጥገና ሕክምና Aማራጮችና ያላቸውን መልካምና Aስከፊ ይዘት ሊያስረዳዎ ይችላል፡፡ ለጥቂት ሴቶች ጡታቸውን Eንዳለ ማቆየት Aስፈላጊ Eንደሆነ በጣም ያምናሉ፡፡ Eንዳንድ ሴቶች ደግሞ ሕክምና የሚወስደውን ጊዜና የሚሰጠውን የጨረራ (Radiation) ሕክምና Eንዲሁም በቀረው የጡት ቲሹ ላይ ተመልሶ ሊያስከትል የሚችለው ካንሰር በማሰብ ጡታቸውን ማቆየት Aስፈላጊ Eንደሆነ ይረዳሉ፡፡
Aንዳንዴ ከላምፔክቶሚ የቀዶ ጥገና በኋላ ሐኪሞች ሌላ ብዙ ተጨማሪ ሪክሲዥን (Reexcision) ቀዶ ጥገና ያዛል፡፡ በዚህ ቀዶ ጥገና ቀድሞ በላምፔክቶሚ የወጣውን የካንሰር Eጢ Aካባቢ የነበረውን ካንሰራማ ቲሹ ለማውጣትና ለማስወገድ የሚደረግ Aሰራር ነው፡፡

ለስኩዋር ታማሚዎች ተስማሚ የአመጋገብ ስርዓት ምን ማሙዋላት ይኖርበታል??
29/04/2017

ለስኩዋር ታማሚዎች ተስማሚ የአመጋገብ ስርዓት ምን ማሙዋላት ይኖርበታል??

23/04/2017
23/04/2017

አጣዳፊ ተቅማጥና ትውከት በሽታን የሚያስከትለው ችግር ምንድነው ? እንዴትሰ መከላከል ይቻላል?
የአተት ምልክቶች ምንድናቸው ?
በበሽታው የተያዘ ሰው በተደጋጋሚ አጣዳፊ ተቅማጥና ትውከት ይኖረዋል፡፡ በዚህም የተነሳ የሰውነት ፈሳሽና ጠቃሚ የሆኑትን ንጥረ ነገሮች መጠን ያዛባል፡፡ በተጨማሪም
• አጣዳፊ መጠነ ብዙ የሆነ ውኃማ ተቅማጥ
• ትውከትና ቁርጥማት
• የአይን መስርጐድ
• የአፍና የምላስ መድረቅ
• እንባ አልባ መሆን
• የሽንት መጠን መቀነስ
• የቆዳ ድርቀትና መሸብሸብ በመጨረሻም ከፍተኛ የሆነ የሰውነት ድርቀት በማስከተል ህመምተኛው በወቅቱ ካልታከመ ለሞት ሊያበቃው ይችላል፡፡
በአተት የተያዘ ሰው ከሰውነቱ ብዙ ፈሳሽ ስለሚወጣ በሽተኛው የሰውነት ድርቀት /Dehydration/ ያስከትልበታል፡፡ ይህ ሁኔታ ደግሞ በአተት የተያዘው ሰው በአጭር ጊዜ ራሱን እንዲስት ያደርገዋል፡፡ ከዚህ በተጨማሪ አፋጣኝ የሕክምና ዕርዳታ ካላገኘ በበሽታው የመሞት አጋጣሚው ሃምሳ ከመቶ /5ዐ%/ ነው፡፡ ነገር ግን አስፈላጊው የሕክምና ዕርዳታ ከተደረገለት የመሞት አጋጣሚው ከአንድ ከመቶ /1%/ ወይም ከዚያ በታች ማድረግ ይቻላል፡፡
በሽታውን መለያ መንገዶች
1. ምልክቶቹን በማየት
2. በላብራቶሪ ሊረጋገጥ ይችላል፡፡
ህክምናው
• የወጣውን ፈሳሽ መተካት ዋናውና ቅድሚያ የሚሰጠው ነው
• እንደ ተዋህሲያኑ አይነት በባለሙያ የሚሰጥ ህክምናን ተግባራዊ ማድረግ
መከላከያና መቆጣጠሪያ መንገዶች
• መፀዳጃ ቤት መገንባትና በአግባቡ መጠቆም
• ምግብን በሚገባ አብስሎ መመገብ
• በውኃ ኬሚካል የታከመ ውሃን ለመጠጥ መጠቀም ወይም ውኃ አፍልቶና አቀዝቅዞ መጠጣት
• ምግባችንን ዝንቦች እንዳያርፉበት ማድረግ፣
• የምንጠቀመው ውሃ ጎርፍ ከማይገባበትና ቦታ እና የእግር ንክኪ የሌለው ማድረግና የውሃ አረንጓዴ ካልፈጠረ አካባቢ መሆኑን ማረጋገጥ፣
• በየሜዳው አለመጸዳዳት፣
• የበሰለ ምግብን የማይጠቀሙት ከሆነ ሸፍኖ ማስቀመጥ፣
• በበሽታው ከተያ ሰው የሚወጡ ፈሳሾችን በባዶ እጅ አለመንካት፣ ከነኩ ወዲያውኑ በንጹህ ውሃ መታጠብ፣
• እጅን በውኃና በሳሙና /በአመድ በደንብ አጥርቶ መታጠብ፣
• ለዝንቦች መራቢያ የሚሆኑ ስፍራዎችን ማጥፋት፣
 ከመጸዳጃ ቤት መልስ
 ምግብ ከማዘጋጀት በፊት
 ምግብ ከማቅረብ በፊት
 ምግብ ከመመገብ በፊት
 ሕጻናትን ካጸዳዱ በኋላ
 ህጻናትን ጢት ከማጥባት በፊት
 በበሽታዉ የተያዙ ሰዎችን እነክብካቤ ከደረጉ በኃላ
ማንኛውም ከቤት የሚወጣ ደረቅ ወይም ፈሳሽ ቆሻሻ አካባቢን ወይንም ውኃን እንዳይበክል በአግባቡ ማስወገድ፡፡ ምልክቱ የታየበት ህመምተኛ ፈጥኖ ወደ ህክምና ተቋም በመምጣት ሊታከም ይገባል፡፡

Address

T. Roosevelt Street, Mexico Square
Addis Ababa

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Synergy Healthcare Consultancy Ethiopia/ሲነርጂ የውጪ ሃገር ህክምና አገልግሎት posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share

Share on Facebook Share on Twitter Share on LinkedIn
Share on Pinterest Share on Reddit Share via Email
Share on WhatsApp Share on Instagram Share on Telegram

Category