Dr.Tizazu Alemu

Dr.Tizazu Alemu ✅የማህፀን እና ፅንስ ስፔሻሊስት
👉 አዲስ ሕይወት ሆስፒታል (ሃያ ሁለት)
👉 ☎️ 0982851688
👉Empowering Women's Health, One Visit at a Time

🔴 የፅንስ የጀርባ(የህብለሰረሰር ) ክፍተትን መከላከል ይቻላል?👉 በእርግዝና ወቅት በቂ ፎሊክ አሲድ መውሰድ አብዛኛዎችን የህብለሰረሰር ክፍተትን መከላከል ይቻላል። 👉 ይህን ችግር ለመከላከል...
03/10/2025

🔴 የፅንስ የጀርባ(የህብለሰረሰር ) ክፍተትን መከላከል ይቻላል?

👉 በእርግዝና ወቅት በቂ ፎሊክ አሲድ መውሰድ አብዛኛዎችን የህብለሰረሰር ክፍተትን መከላከል ይቻላል።

👉 ይህን ችግር ለመከላከል አንዲት ሴት ከማርገዟ በፊት ፎክ አሲድ ወይም ፎሊክ አሲድ ያለው ፕሪናታል ቫይታሚን በየቀኑ መውሰድ መጀመር ይኖርባታል።

👉 ከእርግዝና በፊት የሚወሰድበት ምክንያት አንዲት ሴት እርጉዝ መሆኗን በምታውቅበት ጊዜ የአከርካሪ እና የነርቭ ስርዓት መገንባት ከጀመረ በኃላ በመሆኑ ነው።

👉 የሚጥል መድኃኒቶች የሚወስዱ ሴቶች ተጨማሪ እና መጠኑ ከፍ ያለ ፎሊክ አሲድ መውሰድ ይኖርባቸዋል ምክንያቱም እነዚህን መድኃኒቶች በሰውነት ውስጥ ያለውን የፎሊክ አሲድ መጠን ዝቅ ሊያደርጉ ስለሚችሉ ነው።

19/09/2025

🔴 እርግዝና ከሚጠበቀው 40 ሳምንት በላይ ሲዘገይ መደረግ ያለበት

👉 ብዙ ነፍሰጡር እናቶች ከ 37-40 ሳምንታት መካከል ባለው ጊዜ ይወልዳሉ።

👉 ሆኖም ከ5-10% የሚሆኑት ሴቶች እስከ 42 ሳምንት እርግዝናቸው ይቀጥላል፤ ይህም ቀኑ ያለፈ እርግዝና ብለን እንጠራዋለን።

🔴 ስለእነዚህ የእርግዝና ጊዜ ማወቅ አስፈላጊ የሆነው ለምንድን ነው?

👉 የፅንስ የምግብ እና ኦክስጅን ምንጭ የሆነው የእንግዴ ልጅ ተግባር ከ 41-42 ሳምንታት በኋላ ማሽቆልቆል ይጀምራል።

👉 የእንሽርት ውሃ ፈሳሽ መጠን መቀነስ ይጨምራል ይህም ፅንስ እትብት ላይ ጫና መፍጠር ይጀምራል።

👉 የፅንስ ሆድ ውስጥ እያለ ሞት ቀስ በቀስ ከ41 ሳምንት በኃላ ይጨምራል፤ ይሄውም ከ1 -2 የሚሆን የፅንስ ሞት 40 ሳምንት ላይ ከ1000 እርግዝና የሚከሰት ሲሆን ከ41 ሳምንት በኃላ ወደ 2-3 ከ1000 እርግዝናዎች ከፍ ይላል።

👉 የፅንስ ኪሎ መጨመር እና በወሊድ ጊዜ የትከሻ ከማህፀን በቀላሉ አለመውጣት አደጋን መጨመር እና በኦፕሬሽን የመውለድ እድል ከፍ እንዲል ያደርጋል።

🔴 ከ40 ሳምንት በኃላ ስላለ እርግዝና ምን ይመከራል?

💥 ምንጭ 👉አብዛኛው አለም የተስማማባቸው የማህፀን እና ፅንስ ህክምና መመሪያዎች (ACOG እና RCOG)

👉 በየሳምንቱ ወይም በሳምንት ሁለት ጊዜ የአልትራሳውንድ ክትትል ማድረግ

1. የምጥ መርፌ በመስጠት እንዲወልዱ የሚመከርበት ጊዜ

👉 ከ41+0 -42+0 ሳምንት ላይ እንዲሰጥ ይመከራል ፤ ይህም የፅንስ ሆድ ውስጥ ሞትን የሚቀንስ ሲሆን በጥናቶች በኦፕሬሽን የመውለድ እድልን በተጋነነ ደረጃም አይጨምርም።

2. ምጥ በራሱ እስከሚጀምር መጠበቅ

👉 በቂ ክትትል እየተደረገ ፣ክትትል ላይ የፅንስ ጤናማነትን በበቂ ሁኔታ ከተረጋገጠ ምጥ መጠበቅ እንደአማራጭ ሊወሰድ ይችላል።

🔴 ከፍተኛ መረጃ ላይ የተመሰረቱ ጥናቶች ምን ይመክራሉ።

👉 41 ሳምንት ላይ ለእናቶች የምጥ መርፌ መስጠት እና እንዲወልዱ ማድረግ የፅንስ ሞትን እና ከወሊድ በኃላ የሚከሰትን ጊዜያዊ የልጅ የህመም ደረጃ እና ዘላቂ ጉዳትን ይቀንሳል።

👉 ከ41 ሳምንት በላይ ምጥ በራሱ ቢጀምርም በኦፕሬሽን የመውለድ እድል የምጥ መርፌ ከሚሰጣቸው በተጨባጭ ያነሰ አይደለም።

🔴 ለእናቶች መልእክት፦

👉 ከሚጠብቁት የመውለጃ ቀን በላይ የተወሰኑ ቀናት ቢዘገይ ጤናማ እንደሆነ ማወቅ ይኖርብዎታል ፤ ነገር ግን ከ40 ሳምንት በኃላ የክትትል ጊዜ ማሳለፍ የለብዎትም። እርግዝናዎ ከ41 ሳምንት በላይ ካለፈ ከሐኪምዎ ጋር ስለምጥ መርፌ አማራጭ ይነጋገሩ።

ዶ/ር ትዕዛዙ ዓለሙ: የማህፀን እና ፅንስ ስፔሻሊስት
☎️ 0982851688

🔴 የዓይነት 2  የስኳር በሽታ ለመቆጣጠር የሚያገለግል ሜትፎርሚን የስኳር መድሃኒት የኢንሱሊን በአግባቡ አለመስራት ባላቸው ሴቶች ላይ የእንቁላል መውጣት እና እርግዝና ያለመፈጠር ችግርን ሊያ...
04/08/2025

🔴 የዓይነት 2 የስኳር በሽታ ለመቆጣጠር የሚያገለግል ሜትፎርሚን የስኳር መድሃኒት የኢንሱሊን በአግባቡ አለመስራት ባላቸው ሴቶች ላይ የእንቁላል መውጣት እና እርግዝና ያለመፈጠር ችግርን ሊያሻሽሉ ይችላል።

👉 ከ ክሎሚፈን ሲትሬት ጋር ሲጣመር የማርገዝ እድልን በከፍተኛ ሁኔታ ይጨምራል።

👉 ይህ የመድሃኒት ጥምረት በተለይ ክሎሚፈን ብቻ ስኬታማ ላልሆኑ ሴቶች ጠቃሚ ነው።

☎️ 098 285 1688

🔴 የሴቶች ብቻ የመንፈስ ጭንቀት- የቅድመ የወር አበባ ችግር(Premenustral Dysphoric disorder)👉 ይህ በ 5% በሚሆኑ ሴቶች ላይ የሚከሰት እና ከወር አበባ ዑደት ጋር የተያ...
03/10/2024

🔴 የሴቶች ብቻ የመንፈስ ጭንቀት- የቅድመ የወር አበባ ችግር(Premenustral Dysphoric disorder)

👉 ይህ በ 5% በሚሆኑ ሴቶች ላይ የሚከሰት እና ከወር አበባ ዑደት ጋር የተያያዘ የተለየ የመንፈስ ጭንቀት አይነት ነው።

👉 የመንፈስ ጭንቀት ምልክቶች ከወር አበባ በፊት ባለው ሳምንት ውስጥ ይከሰታል።

👉 ከዚያም በፍጥነት ተሻሽለው ከወር አበባ በኋላ ባለው ሳምንት ወደ መደበኛው ጤንነት ይመለሳሉ።

👉 ይህ ችግር በአብዛኛዎቹ የወር አበባ ዑደቶቻቸው ላይ ይደጋገማል።

👨‍⚕️ዶ/ር .ትዕዛዙ (የማህፀን እና ፅንስ ስፔሻሊስት)
☎️ 0939011402
🏪 አዲስ ሕይወት ሆስፒታል(ሃያ ሁለት)

30/09/2024

Check out 👨‍⚕️ዶ/ር ትዕዛዙ ዓለሙ’s video.

🔴 በእርግዝና ወቅት ምን ያህል መመገብ አለብዎ?👉 ታዋቂው አባባል እርጉዝ በሚሆኑበት ጊዜ "ለሁለት ብይ" ነው።  👉 እውነታው ግን በእርግዝና ወቅት ከወትሮው መጠን በአንድ ጊዜ ሁለት እጥፍ ...
29/09/2024

🔴 በእርግዝና ወቅት ምን ያህል መመገብ አለብዎ?

👉 ታዋቂው አባባል እርጉዝ በሚሆኑበት ጊዜ "ለሁለት ብይ" ነው።

👉 እውነታው ግን በእርግዝና ወቅት ከወትሮው መጠን በአንድ ጊዜ ሁለት እጥፍ መመገብ አደገኛ እንደሆነ ታውቋል።

👉 ትክክለኛው "ለሁለት ብሎ በአንዴ ከመብላት" ይልቅ ሁለት ጊዜ መብላት ጤናማ እንደሆነ ማወቅ ይኖርብዎታል።

👉 እርግዝናዎ አንድ ፅንስ ከሆነ ፣ ከሶስት ወር ጀምሮ በቀን ተጨማሪ 340 ካሎሪ ያስፈልግዎታል።

👉 ያም ማለት የአንድ ብርጭቆ ወተት እና ግማሽ ሳንድዊች መጠን ያለው ተጨማሪ ምግብ ማለት ነው።

👉 እርግዝናዎ መንታ ከሆነ በቀን ወደ 600 ተጨማሪ ካሎሪዎች ማግኘት ይኖርብዎታል።

👉 እርግዝናው ሶስት ፅንስ ከሆነ በቀን 900 ተጨማሪ ካሎሪዎችን መውሰድ አለብዎት።

👨‍⚕️ዶ/ር .ትዕዛዙ (የማህፀን እና ፅንስ ስፔሻሊስት)
☎️ 0939011402
🏪 አዲስ ሕይወት ሆስፒታል(ሃያ ሁለት)

🔴 ከከባድ የወር አበባ ደም መፍሰስ ጋር እየታገሉ ነው? ✅ 💊 ''ትራኔክሳሚክ አሲድ'' የሚያስፈልግዎ መድሃኒት ሊሆን ይችላል!👉 ትራኔክሳሚክ አሲድ ከባድ የወር አበባ ደም መፍሰስን ለማከም ...
29/09/2024

🔴 ከከባድ የወር አበባ ደም መፍሰስ ጋር እየታገሉ ነው?

✅ 💊 ''ትራኔክሳሚክ አሲድ'' የሚያስፈልግዎ መድሃኒት ሊሆን ይችላል!

👉 ትራኔክሳሚክ አሲድ ከባድ የወር አበባ ደም መፍሰስን ለማከም በሐኪም የሚታዘዘ መድኃኒት ነው።

👉 በታብሌት መልክ የሚሰጥ ሲሆን የወር አበባ በሚጀምርበት ጊዜ በየወሩ የሚወሰድ እና ስቃይን በእጅጉ የሚያሻሽል ነው።

👉 ይህ መድሃኒት ደም ከረጋ በኃላ እንዳይፈርስ በማድረግ ከባድ የደም መፍሰስን ለመቀነስ ይረዳል።

🎯 ያስተውሉ፦ ለእርስዎ ትክክለኛ መድሃኒት መሆኑን ለማወቅ ሃኪም ያማክሩ። ✨

👨‍⚕️ዶ/ር .ትዕዛዙ (የማህፀን እና ፅንስ ሀኪም)
☎️ 0939011402
🏪 አዲስ ሕይወት ሆስፒታል

የሶስት ወር መርፌ የወሊድ መቆጣጠሪያ 👉 ከመጠቀምዎ በፊት የጎንዮሽ ጉዳቶችን ይወቁ👉 ሊያስታውሷቸው የሚገቡ አንዳንድ የጎንዮሽ ጉዳቶች 👉 መደበኛ ያልሆነ የወር አበባ ዑደት ወይም የወር አበባ...
28/09/2024

የሶስት ወር መርፌ የወሊድ መቆጣጠሪያ 👉 ከመጠቀምዎ በፊት የጎንዮሽ ጉዳቶችን ይወቁ

👉 ሊያስታውሷቸው የሚገቡ አንዳንድ የጎንዮሽ ጉዳቶች

👉 መደበኛ ያልሆነ የወር አበባ ዑደት ወይም የወር አበባ አለመኖርን ጨምሮ ለውጦች ሊያጋጥምዎት ይችላል።

👉 ለረዥም ጊዜ መጠቀም የአጥንት መሳሳት በተለይ በለጋ እድሜ መጠቀም የጀመሩ ሴቶች

👉 የክብደት መጨመር፡- አንዳንድ ተጠቃሚዎች በጊዜ ሂደት ክብደት መጨመር ያጋጥማቸዋል

👉 የስሜት መለዋወጥ ወይም ድብርት

👉 ከተቋረጠ በኋላ ከ6 ወር እስከ 1 ዓመት እርግዝናን ማዘግየት

👉 ራስ ምታት፣ ማቅለሽለሽ እና የጡት ህመም ሊያስከትል ይችላል።

👨‍⚕️ዶ/ር .ትዕዛዙ (የማህፀን እና ፅንስ ስፔሻሊስት)
☎️ 0939011402
🏪 አዲስ ሕይወት ሆስፒታል(ሃያ ሁለት)

የመካንነት መድሃኒት👉 ክሎሚድክሎሚድ (ክሎሚፊን ሲትሬት) የመካንነት መድኃኒት ነው። እንቁላል ከእንቁላል ከረጢት(Ovary) ውስጥ እንዲለቀቅ ያበረታታል, ይህም እንደ ፖሊሲስቲክ ኦቫሪ ሲንድረ...
31/07/2024

የመካንነት መድሃኒት👉 ክሎሚድ

ክሎሚድ (ክሎሚፊን ሲትሬት) የመካንነት መድኃኒት ነው።

እንቁላል ከእንቁላል ከረጢት(Ovary) ውስጥ እንዲለቀቅ ያበረታታል, ይህም እንደ ፖሊሲስቲክ ኦቫሪ ሲንድረም (PCOs) ችግር ላለባቸው ሴቶች ጠቃሚ ያደርገዋል።

⁉️ እንዴት ነው የሚሰራው፦

በተፈጥሮ በደም የሚዘዋወረውን የሴት ልጅ ሆርሞን (Estrogen) እንዳይሰራ በማድረግ እንቁላል የመለቀቅ እድልን ይጨምራል።

👉ጠቃሚ ነጥቦች፡-

- ማንኛውንም የእርግዝና መድሃኒት ከመጀመርዎ በፊት ሁል ጊዜ የጤና ባለሙያ ያነጋግሩ።

- ክሎሚድ መንትዮችን ወይም ሶስት የመፀነስ እድልን ይጨምራል።

- የጎንዮሽ ጉዳቶች፡ የአይን ብዥታ እና ኦቫሪያን ሃይፐርስሚሌሽን ሲንድረም (OHSS) ሊኖሩ ይችላሉ።

የአባላዘር በሽታ ምልክቶችን ይወቁ!1. ያልተለመደ ቁስለት ወይም እብጠት በብልትዎ ወይም በፊንጢጣዎ አካባቢ መኖር2. ከወንድ ብልት ወይም ከሴት ማህፀን የሚወጣ ያልተለመደ ፈሳሽ 3. ከእንብር...
30/07/2024

የአባላዘር በሽታ ምልክቶችን ይወቁ!

1. ያልተለመደ ቁስለት ወይም እብጠት በብልትዎ ወይም በፊንጢጣዎ አካባቢ መኖር

2. ከወንድ ብልት ወይም ከሴት ማህፀን የሚወጣ ያልተለመደ ፈሳሽ

3. ከእንብርት በታች የሆድ ህመም

3. በሽንት ጊዜ ምቾት ማጣት ወይም ማቃጠል ካጋጠመዎት የአባላዘር በሽታ ተያያዥ ምልክት ሊሆን ይችላል።

👉 Remember, early detection matters! Stay informed and take care. 💙 "

በእርግዝና ወቅት የሻያቲክ ነርቭ(Sciatica) ህመም በጣም ፈታኝ ሊሆን ይችላል።አጭር ማብራሪያ ይኸውና፡-Sciatica ከፍተኛ የሆነ  ህመም ከጀርባ ወይም ከመቀመጫ ይጀምር እና ወደ እግሮ...
28/07/2024

በእርግዝና ወቅት የሻያቲክ ነርቭ(Sciatica) ህመም በጣም ፈታኝ ሊሆን ይችላል።

አጭር ማብራሪያ ይኸውና፡-
Sciatica ከፍተኛ የሆነ ህመም ከጀርባ ወይም ከመቀመጫ ይጀምር እና ወደ እግሮች የሚሰራጭ የህመም አይነት ነው።
በእርግዝና ወቅት በሚከተሉት ምክንያቶች ይፈጠራል።

1. ክብደት መጨመር እና የሰውነት ፈሳሽ መጠን መጨመር
እነዚህ በዳሌው ውስጥ ሻይቲክ ነርቭ በሚያልፉበት ጊዜ ጫና ይፈጥራሉ

2. የማሕፀን(Uterus) ማደግ፡- በታችኛው አከርካሪ ላይ የሚገኘውን የሻይቲክ ነርቭ ሊጫን ይችላል።

3. የፅንስ አቀማመጥ፡- ከ7 ወር በኃላ የፅንስ ጭንቅላት ወደታች በመዞር በቀጥታ በነርቭ ላይ ሊያርፍ ይችላል።

የህክምና ምክሮች:

✅ በሙቅ ውሃ መታጠብ ወይም የሞቀ ውሃ በፎጣ ህመም የሚሰማ ቦታላይ ጫን ማድረግ

✅ ወገብን እና እና እግርን የመለጠጥ እንቅስቃሴዎች ማድረግ

✅ መዋኘት በነርቭ ላይ ያለውን ጫና ለመቀነስ ይረዳል

✅ የሆድ ቀበቶ መጠቀም

✅ ህመም ከሚሰማበት በተቃራኒው ጎን መተኛት።

👉 ያስታውሱ, sciatica ብዙውን ጊዜ ከወሊድ በኋላ ይሻሻላል።

Address

Addis Ababa

Telephone

+251941282829

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Dr.Tizazu Alemu posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Practice

Send a message to Dr.Tizazu Alemu:

Share

Share on Facebook Share on Twitter Share on LinkedIn
Share on Pinterest Share on Reddit Share via Email
Share on WhatsApp Share on Instagram Share on Telegram

Category