26/01/2026
በድንገተኛ እሳት አደጋ የተጎዱ ቤተሰቦችን ለመደገፍ የተደረገ ጥሪ
~~~~
👉አብረን እንቁም፣ አብረን ተስፋቸወን እንመልስ።
👉አቶ ማላ ሾኔ እና ወ/ሮ ዕድገት በአርባምንጭ ከተማ ወኃ ምንጭ ቀበሌ ኃይላንድ መንደር ከህብረት ለልማት ት/ቤት ወረድ ብሎ የሚኖሩ የከተማው ነዋሪዎች ሲሆኑ እሁድ በቀን 17/05/2018 ዓ/ም የቤተሰቡ አባላት ቤተክርስቲያን በሄዱበት ቤት ውስጥ በተከሰተው የእሳት አደጋ ምክንያት ቤታቸውን፣ ንብረታቸውን እና የዕለት ተዕለት መኖሪያቸውን በሙሉ አጥተዋል። የደረሰው አደጋ እጅግ የከፋ ነው። ስለሆነም ለወገን ደራሽ ወገን ነውና እንደረስላቸው።
👉እኛ እንደ ማህበረሰብ በመተባበር ትንሽ ትንሽ ብንሰጥ ታላቅ ለውጥ ማምጣት እንችላለን። የምናቀርበው ድጋፍ ገንዘብና ሌሎች አስፈላጊ የቤት ቁሳቁሶች ሊሆኑ ይችላሉ። ይህ ድጋፍ እንደገና ተስፋ እንዲያገኙ እና ሕይወታቸውን እንደገና እንዲጀምሩ ትልቅ ኃይል ይሆናል።
👉እባክዎ በልብዎ ያለውን ርኅራኄ በተግባር ያሳዩ፤ ዛሬ የምንሰጠው ድጋፍ ነገ የአንድ ቤተሰብ ሕይወት ሊቀይር ይችላል።
በጎነት ለራስ ነው።
አቶ ማላ ሾኔ ጉቼ
0913265547
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ
1000309933102