Assosa health center

Assosa health center this page is used to provide update information about Assosa health center in its service .it only u

በአሶሳ ጤና አጠባበቅ ጣቢያ እየተተገበረ ያለውን የቤተሰብ ጤና ቡድን ትግበራ ተሞክሮ ከባምባሲ ከተማ ከተወጣጡ የዘርፉ ተሳታፊዎች ከጤና ቢሮ ጋር በመሆን በአሶሳ ጤና ጣቢያ የልምድ ልውውጥ አ...
14/01/2023

በአሶሳ ጤና አጠባበቅ ጣቢያ እየተተገበረ ያለውን የቤተሰብ ጤና ቡድን ትግበራ ተሞክሮ ከባምባሲ ከተማ ከተወጣጡ የዘርፉ ተሳታፊዎች ከጤና ቢሮ ጋር በመሆን በአሶሳ ጤና ጣቢያ የልምድ ልውውጥ አደርጓል።

የጥንቃቀ መልክት ለአሶሳ እና አከባቢው ነዋሪዎች በሙሉዛሬ በቀን 20/04/2015ዓ/ም በደረሰን ጥቆማ መሰረት ስደተኞች ጎንድል ሰፈር አከባቢ ግዘ አልፎበት የተወገዱትን ፕላምፕነት እና ብስኩ...
29/12/2022

የጥንቃቀ መልክት ለአሶሳ እና አከባቢው ነዋሪዎች በሙሉ
ዛሬ በቀን 20/04/2015ዓ/ም በደረሰን ጥቆማ መሰረት ስደተኞች ጎንድል ሰፈር አከባቢ ግዘ አልፎበት የተወገዱትን ፕላምፕነት እና ብስኩት ነገሮችን አጥቦ መንገድ ላይ ለልጆች አምስት አምስት ብር ስሸጡ እጅ ከፍንጅ ይዘን ለፀጥታ አካላት አሳልፈን ልከናል።ምግቦቹን ከተመገቡት ህጻናት መካከል ሁለቱ ትውክያ እና ተቅማጥ ይዟቸው ወደ ጤና ተቋም ሂዶ እንድታከሙ ተደርጓል።ስለሆነም የማህበረሰቡን ጤና የምያውክ መሰል ድርግቶችን ከተመለከታችሁ ለምመለከተው መረጃ እንድትሰጡ እየጠየቅን ልጆች ነገም ገዝቶ እንዳይበሉ የቤተሰብ ምና ከፍተኛ መሆኑን እንገልፃለን።

በአሶሳ ጤና አጠባበቅ  ጣቢያ አንድነትን እና የጋራ ማህበራዊ ጉዳዮችን ለማጠናከር የሻይ ቡና ፕሮግራም እንድህ በደማቅ ሁኔታ ተካሂዷል ።
25/11/2022

በአሶሳ ጤና አጠባበቅ ጣቢያ አንድነትን እና የጋራ ማህበራዊ ጉዳዮችን ለማጠናከር የሻይ ቡና ፕሮግራም እንድህ በደማቅ ሁኔታ ተካሂዷል ።

01/11/2022
የአሶሳ ጤና አጠባበቅ ሰራተኞች የሻይ ቡና ፕሮግራም በማዘጋጀት የጋራ ማህበራዊ ጉዳዮችን በማጠናከር ዙርያ ሰፊ ውይይት አደርገዋል ።የውውቱ ተሳታፊዎች እንደገለጹት የጤና ስራ የቲም ስራ ከመሆ...
25/10/2022

የአሶሳ ጤና አጠባበቅ ሰራተኞች የሻይ ቡና ፕሮግራም በማዘጋጀት የጋራ ማህበራዊ ጉዳዮችን በማጠናከር ዙርያ ሰፊ ውይይት አደርገዋል ።የውውቱ ተሳታፊዎች እንደገለጹት የጤና ስራ የቲም ስራ ከመሆኑ ጋር ተያይዞ እንድህ አይነት መሰል ዝግጅቶች ባለሙያዎች ተቀራርቦ እና ተፋቅሮ እንድሰሩ ከፍተኛ ምና ስላለው በየወሩ በድፓርትመንት ደረጃ ቀጣይነት እንድኖረው ገልጸዋል ። ልዩነቶቻችንን በማጥበብ እና አንድነታችንን በማጠናከር ጤናማ የሆኔ ማህበረሰብን በማፍራት በተባበረ ክንዳችን የለማች እና የበለጸገች ሀገር ኢትዮጵያን የማየት ህልማችንን እውን እናደርጋለን ።

በአሶሳ ጤና ጣቢያ ከ IRC ጋር በመተባበር የአለም የእጅ መታጠብ ቀን በማክበር ጎን ለጎን ለባለሙያዎች የኮቪድ 19 ማጠናከርያ ላልወሰዱ  ክትባቱን በመከተብ አጠናቅቀዋል ።
14/10/2022

በአሶሳ ጤና ጣቢያ ከ IRC ጋር በመተባበር የአለም የእጅ መታጠብ ቀን በማክበር ጎን ለጎን ለባለሙያዎች የኮቪድ 19 ማጠናከርያ ላልወሰዱ ክትባቱን በመከተብ አጠናቅቀዋል ።

የአሶሳ ከተማ አሰተዳደር ጤና መምርያ በአሶሳ ጤና ጣቢያ የ2014 ዓ/ም የስራ አፈጻጸም ሪፖርት መነሻ በማድረግ የላቀ ውጤት ላስመዘገቡት ባለ ሙያዎች የማበረታቻ  ሽልማት አበርክተዋል ። የጤ...
14/10/2022

የአሶሳ ከተማ አሰተዳደር ጤና መምርያ በአሶሳ ጤና ጣቢያ የ2014 ዓ/ም የስራ አፈጻጸም ሪፖርት መነሻ በማድረግ የላቀ ውጤት ላስመዘገቡት ባለ ሙያዎች የማበረታቻ ሽልማት አበርክተዋል ። የጤና መምርያው ሀላፊ አቶ አንዋር ያስን እንደገለፁት ይህ የተሻለ አፈፃፀም በተቋሙ ሰራተኞች ከጥበቃ እሰከ ጽዳት ሰራተኞች የጋራ ትብብር ስለሆኔ ለሁሉም ላቅ ያለ ምሰጋናቸውን በማቅረብ ቀጣይ ከዝህ የበለጠ ውጠት እንደምመዘገብ በመተማመን አበረታቷቸዋል ።
የአሶሳ ከተማ አስተዳደር ብ/ፓ/ጽ/ሀላፊው አቶ ከማላድን አልፈኪ የግባዓት አቅርቦቱን ለማሻሻል ከግብረ ሰናይ ድርጅቶች ጋር በቅርበት በመስራት ለሎች የተቋሙን ችግሮች በጋራ ለመፍታት አመራሩ እና ባለ ድርሻ አካላት በቁርጠኝነት በቅርበት ድጋፈቸውን ማድረግ እንደምገባቸው ገልጸዋል።
መመሪያው ለባለሙያዎች የሰጠው ቦታ እና ክብር ለምቀጥለው ስራ መነቃቃትን የምፈጥር ስሆን ለዝህም ጤና ጣቢያው የተሰማውን ልባዊ ደሰታ እየገለጸ ለዝህ ሁሉ በጎ ስራ የመምርያውን ማናጅመንት አባላት እና ለመምርያው ሀላፊ አቶ አንዋር ያስን ላቅ ያለ ምስጋናን አቀርበዋል ።

Covid 19 QR code started at Assosa health center
05/10/2022

Covid 19 QR code started at Assosa health center

13/09/2022

አስደሳች ዜና ለአሶሳ እና አከባቢው ነዋርዎች በሙሉ
እንደምታወቀው ከዝህ ቀደም ለውጭ ሀገር በረራ እና ለ VIP ዎ የምያስፈልገውን የኮቪድ 19 QR ኮድ ሰርትፍከት ግደታ ከአድስ አበባ ብቻ ስወጣ እንደነበር ይታወቃል።ሆኖም ግን የማህበረሰቡን እንግልት ለመቀነስ ስባል ጤና ቢሮ ከጤና ምንሰተር ጋር በመተባበር በክልላችን አሶሳ ጤና አጠባበቅ እንደ ፖይለት ተመርጦ አገልግሎት መስጠት መጀመራችን ስናበስር በታላቅ ደሰታ ነው።
QR ኮዱን ለማሰራት ወደ ተቋማችን ስመጡ ማሟላት ያለባቸው ግደታዎች፡
1, ህጋዊ የሆኔ ማህተም ያለው የኮቪድ ሰርትፊከት
2,ፓስፖርት
3, ሃምሳ ብር የአገልግሎት ክፍያ
ይህ ተክኖሎጂ ልዩ የምያደርገው ዘመናዊ ድጅታል ስስተም ስሆን በኦንላይን ስስተም ውስጥ የምገባ ስሆን መረጃዎትን በቴለ ግራም፣ዋትሰ አፕ፣ በኢሜይል እና በለሎች ተክኖሎጂዎች በመውሰድ ከምሄዱበት ቦታ ላይ በቀላሉ scan በማስደረግ ማስነበብ ይችላሉ ።
ከእንግድህ የውጭ በረራ ዕቅድ ስኖረዎት ወደ አድስ አበባ ሂዶ ከማንገላታት ቀድሞ ያናግሩን።።እንግልትዎን ይቀንስሱ።።የሰማነው ላልሰሙት እናሰማ።።።።ለአገልግሎታችን ሰለምጎበኙን ከወድሁ እናመሰግናለን ።።።።።።።

11/09/2022

የተከበራችሁ ውድ የአሶሳ ጤና አጠባበቅ ጣቢያ
እንኳን ለአድሱ 2015 ዓ/ም በዓል በሰላም አደረሳችሁ ።
የተከበራች የጤና ባለሙያዎች እና የአስተዳደር ስራተኞች ፣ባለፉት አመታት ካጋጠሙን ፈተናዎች ተላቀን በዝህ አድሱ አመት በአድስ መንፈስ፣በአብሮነት በመተባበር እና በመተሳሰብ ማህበረሰባችንን ለማገልገል የተጣለብንን ሀላፍነት በላቀ ደረጃ መወጣት እንደምንችል በመተማመን ይህ አመት የሰላም፣የፍቅር፣የአብሮነት ፣የለውጥ እና የብልጽግና ጊዜ እንድሆንልን እየተመኘው መጪውን አመት እንድሁ አንዳችን ሳንወድቅ እና ሳንጎል በአንድነት እንድናከብር እንድሁም የተቀያየሜ ታርቆ፣ የተራራቀ ተቀራርቦ በፍቅር የወደፍት ጉዞአችን በአንድነት እንድንቀጥል ልባዊ ምኞተን በመግለጽ ለወድፍት ለምናሳልፈው ብሩህ ግዜ ከወድሁ በጤና ጣቢያችን ስም ምስጋናየን አቀርባለሁ።
መልካም አድስ አመት።።።።።።።

ሰላም ለሀገራችን ኢትዮጵያ ።።።።።ሰላም።።።።ሰላም።።።።
08/09/2022

ሰላም ለሀገራችን ኢትዮጵያ ።።።።።ሰላም።።።።ሰላም።።።።

በጣም ልትመሰገን የምትገባ ጠንካራ ወጣት አመራር።።።እንደምታወቀው የማህፀን በር ጫፍ ካንሰር ምርመራ ከተጀመረ ወድህ ብዙ ስራዎች ብሰሩም በምፈለገው መጠን እናቶች እየተመረመሩ አይደለም።።።ይ...
30/08/2022

በጣም ልትመሰገን የምትገባ ጠንካራ ወጣት አመራር።።።
እንደምታወቀው የማህፀን በር ጫፍ ካንሰር ምርመራ ከተጀመረ ወድህ ብዙ ስራዎች ብሰሩም በምፈለገው መጠን እናቶች እየተመረመሩ አይደለም።።።ይህንን የተገነዘበች አንድት ጠንካራ ወጣት የጓደኞቼ ጠንነት ለኔም ጠንነት ነው በማለት ግንዛቤ በመፍጠር እና በራስ ተነሳሽነት በመቀስቀስ ብዙ ሴቶች እንድመረመሩ በማድረጓ ላቅ ያለ ምስጋና እያቀረብኔ የሷን ተመሳለት በመከተል በተለይ በሴቶች ሰክተር የምትሰሩ ሰዎች የድርሻችሁን እንድትወጡ እንጠይቃለን ።
የማህፀን በር ካንሰር በአለም አቀፍ ደረጃ 604 000 የምሆኑ ሴቶችንበየ አመቱ የምያጠቀ እና 342,000 ሰዎች ለህልፈት ሲዳረጉ በ2020 በአለም አቀፍ ደረጃ ከሚከሰቱት ካንሰር አራተኛው ነው።
አዳድስ ከምጠቁት ሴቶች ውስጥ 90% የምሸፍኑት በመካከለኛ እና በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ላይ ያሉ ሀገራት ናቸው።
"""የእህቴ ህመም ለኔም ህመም ነው"""በግዜ በመመርመር እና በመታከም የእህቶቻችንን በማህፀን በር ጫፍ ካንሰር የምከሰተውን ህመም፣ስቃይ እና ሞት በጋራ እንከላከል ።።።።

Address

B/G/R/S, Assosa
Asosa

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Assosa health center posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share

Share on Facebook Share on Twitter Share on LinkedIn
Share on Pinterest Share on Reddit Share via Email
Share on WhatsApp Share on Instagram Share on Telegram