Awaash Magaalahe Xiinissok Qaafiyate Fenteeyna

Awaash Magaalahe Xiinissok Qaafiyate Fenteeyna "እኛ ማህበረሰባችን ውስጥ ነን "

BSC plan ተግባራዊ በማድረግ ውጤታማ ሰራተኛን መፍጠር የተቋማት ድርሻ ነው ፨፨፨በዛሬው ዕለት ከ ቀኑ 9 ሰዐት ጀምሮ በአዋሽ ጤና አጠባበቅ ጣቢያ ለ ሰራተኞች ውጤት ተኮር ሰራተኛና የተቋ...
05/01/2026

BSC plan ተግባራዊ በማድረግ ውጤታማ ሰራተኛን መፍጠር የተቋማት ድርሻ ነው ፨፨፨

በዛሬው ዕለት ከ ቀኑ 9 ሰዐት ጀምሮ በአዋሽ ጤና አጠባበቅ ጣቢያ ለ ሰራተኞች ውጤት ተኮር ሰራተኛና የተቋሙን ግብና ስትራቴጂ በተጠናከረ መልኩ ለማስቀጠል እንደ ክልል የተጀመረውን (BSC plan implementation ) አጠቃላይ የተቋሙን ሰራተኞች በመሰብሰብ ስልጠናውን ለ3 ተከታታይ ቀናት እንዲከታተሉ የተቋሙ ሀላፊ አቶ አሊ አደም ባሉበት አስጀምረዋል አክለውም አቶ አሊ አደም እንደ ተቋም የተጀመሩ የሪፎርም ስራዎችን በጋራ ድክመቶቻችንን እየለየን ጥንካሬያችን ላይ ደሞ ይበለጥኑ እየሰራን ተቋሙን ወደ ተሻለ ደረጃ ለማድረስ የጋራ ርብርብ እንደሚያስፈልግ ገልፀዋል ፨፨

የአዋሽ ጤና አጠባበቅ ጣቢያ ውጤት ተኮር አሰራር ( Bsc implementing ) ዝግጅቱን ጨርሶ ለ ስራ ሂደቶች ግንዛቤ የማስጨበጫ መድረክ ፨፨፨  በዛሬው ዕለት በአዋሽ ጤና አጠባበቅ ጣቢያ...
02/01/2026

የአዋሽ ጤና አጠባበቅ ጣቢያ ውጤት ተኮር አሰራር ( Bsc implementing ) ዝግጅቱን ጨርሶ ለ ስራ ሂደቶች ግንዛቤ የማስጨበጫ መድረክ ፨፨፨

በዛሬው ዕለት በአዋሽ ጤና አጠባበቅ ጣቢያ ከክልል ጤና ቢሮ በተሰጣቸው አቅጣጫ መሰረት እንደ ክልል የተጀመረውን የመንግስት ተቋማትን ውጤትን መሰረት ያደረገ የአሰራር ስርዓትን እንዲዘረጋ ሚዛናዊ በሆነ ዕይታ አስተሳስሮ ለመምራት ፣ የሚፈለገውን ውጤት ከበጀት ጋር አጣጥሞ ለመተግበር ፣ ስትራቴጂካዊ ግቦችን የመመዘን ሂደትን በማከናወን የውጤት ላይ የተመሰረተ የምዘና ስርዐት ተግባራዊ በማድረግ እንዲሁም ተቋሙ ተልዕኮውንና ግቡን ወደ ፈፃሚ አካላት በማውረድ የሚጠበቀውን ስኬት ለመቀዳጀት አስፈላጊውን ግንዛቤ ለ ተለያዩ የክፍል ስራ ሂደቶች የተቋሙ ሀላፊ አቶ አሊ አደም ግንዛቤ ሰጥተዋል አክለውም የተቋሙ ሀላፊ ስልጠናው ከ ሰኞ ጀምሮ ለሁሉም ባለሙያ የሚሰጥ ሲሆን አስፈላጊውን ዝግጅት እንዲያደርጉ አስገንዝበዋል ፨፨፨

 #እኛ ማህበረሰባችን ውስጥ ነን ፨፨በዛሬው ዕለት የ አዋሽ ጤና አጠባበቅ ጣቢያ ባለሙያዎች የቤተሰብ ጤና ቡድን የቤት ለ ቤት ምርመራ በሱባህ ቀበሌ እናቶችም ህፃናትን በማከም ተገቢውን አገል...
30/12/2025

#እኛ ማህበረሰባችን ውስጥ ነን ፨፨

በዛሬው ዕለት የ አዋሽ ጤና አጠባበቅ ጣቢያ ባለሙያዎች የቤተሰብ ጤና ቡድን የቤት ለ ቤት ምርመራ በሱባህ ቀበሌ እናቶችም ህፃናትን በማከም ተገቢውን አገልገሎት በመስጠት ላይ ይገኛል ለማህበረሰባችን አስፈላጊውን ህክምና ቤታቸው በመሄድ ሙያዊ ግዴታችንን እንወጣለን ፨፨

ተቋማችንን ለተገልጋዮች ፅዱ እና ማራኪ ማድረግ የጋራ ግዴታችን ነው ፨፨፨
17/12/2025

ተቋማችንን ለተገልጋዮች ፅዱ እና ማራኪ ማድረግ የጋራ ግዴታችን ነው ፨፨፨

 #የህፃናትን ጤና መጠበቅና ማስተማር ከወላጆቻቸው በተጨማሪ የጤና ባለሙያ ግዴታ ነው ፨በዛሬው ዕለት የአዋሽ ጤና አጠባበቅ ጣቢያ ለህፃናት የጤና ትምህርት በትምህርት ገበታቸው ላይ በመስጠት ...
11/12/2025

#የህፃናትን ጤና መጠበቅና ማስተማር ከወላጆቻቸው በተጨማሪ የጤና ባለሙያ ግዴታ ነው ፨

በዛሬው ዕለት የአዋሽ ጤና አጠባበቅ ጣቢያ ለህፃናት የጤና ትምህርት በትምህርት ገበታቸው ላይ በመስጠት ፨፨

Qafár Rakaakayak Ayyunta Rakiibo Abta Qaafiyat Caabih Ayfaafih Kutbeh Buxah Saqalah Yan Gifta Idriis Macammad  Miraacisa...
07/12/2025

Qafár Rakaakayak Ayyunta Rakiibo Abta Qaafiyat Caabih Ayfaafih Kutbeh Buxah Saqalah Yan Gifta Idriis Macammad Miraacisa Erga Gabbî Rasuk Awash Magaalah Xiinissot Supervision Gufne Aben.

Tama Erga Awash Magaalah Xiinissok Qaafiyat Kutbeh Buxa Kee Magaalâ Xiinissok Gubat Geytimta Qaafiyat Fanteenanit Gufne Abeenim Tamixxige.

Tonnah Kaadu Ferey Takke Daqortik Temeeteh Tan Mihratleelah Gudgud Bicisak Social Insurance Caagid Kee National ID Caagidik Baxsale Hangi Akah Yaceenih Taamitan Inna Kee Qaafiyat Fanteenaani Saqolti Rakaakay Caddol Abbinos Gabbaaqih Kusaq Yan Waddiirah Akah Raaqe Wannah Innah Afkan Yomcowwe.

Ellê Cabol Yan Qaku Kee Gabul Wagsiisak Amô Gacsa Walal Abak Meqe Afkan Yaceenim Abeenim Tamixxige.

የሞዴል ቤተሰብ ምረቃ ፕሮግራም በአዋሽ ከተማ መስተዳደር   በጤና ኤክስቴሽን ፕርግራም መሰረት በጤና ኤእስቴሽን ባለሞያዎች ለጤና ልማት ሰራዊት (ሞዴል ቤተሰብ) የ18ቱን ፓኬጆችን ስልጠና ሲ...
28/11/2025

የሞዴል ቤተሰብ ምረቃ ፕሮግራም
በአዋሽ ከተማ መስተዳደር በጤና ኤክስቴሽን ፕርግራም መሰረት በጤና ኤእስቴሽን ባለሞያዎች ለጤና ልማት ሰራዊት (ሞዴል ቤተሰብ) የ18ቱን ፓኬጆችን ስልጠና ሲከታተሉ በመቆየታቸው በዛሬ ቀን ህዳር 19/2018ዓ/ም ሞዴል ቤተሰብ ምረቃ ፕሮግራም ላይ በመድረሳቸው የሞዴልነት ስታንዳርዱን በማሟላታችሁ የእውቅናና ምስክር ወረቀት እውቅና የተበረከተላቸው ሲሆን። በዚ ህም መሰረት በፕሮግራም በደማቅ ሁኔታ ያለፈ ሲሆን
የጤና ኤክስቴንሽን ሥራ ላይ ትኩረት ተሰጥቶ እየተሰራ መሆኑን የገለጹት የአዋሽ ከተማ አስተዳደር ወኪል ሀላፊ የሆኑት አብዶ ኢብራሂም የጤና ኤክስተሽን ፕሮግራም ተጠናክሮ እንዲቀጥል እና የዛሬ ተመራቂ ሞዴል ቤተሰቦች ጋር በርካታ ሃላፊነት ስራዎች በመስጠትና በጤናው ዘርፍ ቀዳሚ አርበኛ እንደምትሆኑ አምናለው በማለት ምስጋናቸው አቅርበዋል::
የጤና ፅ/ቤት ወኪል አቶ ደርቤ መንግስቱ እና የ አዋሽ ጤና አጠባበቅ ጣቢያ ሀላፊ አቶ አሊ አደም የተገኙ ሲሆን ለተመራቂ ሞዴል እማወራዎችም የእንኳን ደስ አላቹ መልዕክት አስተላልፈዋል::

በዛሬው እለት የአዋሽ ከተማ መስተዳደር አገልግሎት ጽ/ቤት ሀላፊ እንጂነር አብዶ ኢብራሂም በተቋማችን ተገኝተው ባደረጉት ጉብኝት ያለብንን የፕሪንተር ችግር ስንነግራቸው  በብር 118000 የሚ...
29/10/2025

በዛሬው እለት የአዋሽ ከተማ መስተዳደር አገልግሎት ጽ/ቤት ሀላፊ እንጂነር አብዶ ኢብራሂም በተቋማችን ተገኝተው ባደረጉት ጉብኝት ያለብንን የፕሪንተር ችግር ስንነግራቸው በብር 118000 የሚገመት ፕሪንተር ድጋፍ አድርገውልናል ኢንጂነር አብዶ ኢብራሂምን ለሰጡን ፈጣን ምላሽ እና ድጋፍ በአዋሽ ጤና አጠባበቅ ስም ምስጋናችንን እናቀርባለን::

በዛሬው ዕለት በአዋሽ ጤና አጠባበቅ ጣቢያ ከ አዳማ ባስመጣናቸው 5 እውቅ ስፔሻሊስቶች ለከተማው 500 የሚሆን ማህበረሰብ አገልግሎት ሲሰጡ ቆይተዋል ለዚህም ተቋሙ ለኡዋሽ ጄነራል ሆስፒታል ም...
25/10/2025

በዛሬው ዕለት በአዋሽ ጤና አጠባበቅ ጣቢያ ከ አዳማ ባስመጣናቸው 5 እውቅ ስፔሻሊስቶች ለከተማው 500 የሚሆን ማህበረሰብ አገልግሎት ሲሰጡ ቆይተዋል ለዚህም ተቋሙ ለኡዋሽ ጄነራል ሆስፒታል ምስጋናውን ያቀርባል ።።

የ 2017 አመታዊ  የ ስራ ሪፖርት ግምገማ እና የ 2018 አመታዊ የስራ ዕቅድ ዝግጅት፨፨፨በዛሬው ዕለት የ አዋሽ ጤና አጠባበቅ ጣቢያ የ18  ዲፓርትመንት ሀላፊዎችም ከጠዋቱ 2 ሰዐት በተገ...
28/07/2025

የ 2017 አመታዊ የ ስራ ሪፖርት ግምገማ እና የ 2018 አመታዊ የስራ ዕቅድ ዝግጅት፨፨፨

በዛሬው ዕለት የ አዋሽ ጤና አጠባበቅ ጣቢያ የ18 ዲፓርትመንት ሀላፊዎችም ከጠዋቱ 2 ሰዐት በተገኙበት አመታዊ የስራ ሪፖርት ግምገማ እና ለ 2018 የስራ ዕቅዶችን የተቋሙ ሀላፊ አቶ አሊ አደም ባሉበት አስጀምረዋል ፣አክለውም የተቋሙ ሀላፊ የሪፖርት ግምገማው ለ 7 ቀናት የሚካሄድ ሲሆን በየ ዲፓርትመንቱ ያሉ ችግሮች ከስራው ጋር በተያያዘ ቀርቦ ለማህበረሰቡ የተሻለና ጥራት ያለው አገለግሎት ለመስጠትና ለ 2018 የተሻለ የስራ አፈፃፀሞችን ይበልጥ ለማድረግ እንሚረዳና ተቋሙም አስፈላጊውን ግምገማ አድርጎ ከጨረሰ በኋላ ክፍተት የታየባቸውን ዲፓርትመንቶች አስፈላጊውን ድጋፍና ክትትልም ለማድረግም ዝግጁ እንደሆነ ገልፀዋል ፨፨፨

የማህበረሰባችንን የውስጥ ትርታ እናዳምጣለን ፨፨፨በዛሬው ዕለት በ አዋሽ ጤና አጠባበቅ ጣቢያ ከሁሉም ቀበሌ የተውጣጡ የማህበረሰቡ ተወካዮች በሁሉም ቀበሌ የህዝብ ውይይት ( Conference ...
18/07/2025

የማህበረሰባችንን የውስጥ ትርታ እናዳምጣለን ፨፨፨

በዛሬው ዕለት በ አዋሽ ጤና አጠባበቅ ጣቢያ ከሁሉም ቀበሌ የተውጣጡ የማህበረሰቡ ተወካዮች በሁሉም ቀበሌ የህዝብ ውይይት ( Conference ) አድርገው ተቋሙ ላይ ማህበረሰቡ ባነሷቸው ጥያቄዎች ላይ ከ ህዝብ ተወካዮች ኮሚቴ ጋር ከጤና ጣቢያው ሀላፊ አቶ አሊ አደም ጋር ውይይት አድርገዋል አክለውም ኮሚቴው ከህዝቡ በተነሱ ጥያቄዎች ላይ ጤና ተቋሙ ካለበት ጥሩ ጎን ባሻገር ተያያዥ ክፍተቶቹም ስላሉ ክፍተቶችን በምን አይነት መልኩ መስተካከል እንደሚችሉ የጤና ተቋሙን ሀላፊ ጠይቀዋል አቶ አሊ አደም የህዝቡን ተወካዮች አመስግነው በተነሱ ጥያቄዎች ላይ ሰፋ ያለ ማብራሪያ በመስጠትና ተቋሙ ያለበትን ችግሮች በአስቸኳይ ለማስተካከልና የህዝቡን ጥያቄ ከዚሁ ኮሚቴ ጋር ሆነው ደረጃ በደረጃ እንደሚፈቱ ቃል ገብተዋል የአዋሽ ጤና አጠባበቅ ጣቢያ ከማህበረሰቡ ጎን ሆኖ አገልገሎቱን ለተገልጋዮች ምቹ እና ቀልጣፋ እንደሚያደርግ ተቋማችን ለ አዋሽ ህዝብ ጥሪውን ያስተላልፋል ፨፨፨

ለማህበረሰባችን የጤና ትምህርት ፨፨፨በዛሬው ዕለት ከ አዋሽ ጤና አጠባበቅ ጣቢያ የተውጣጡ ጤና ባለሙያዎች የጤና ኤክስቴንሽን ፕሮግራሙን ለመደገፍ በ3 ቀበሌዎች ላይ በእናቶችና ህፃናት , በክ...
10/07/2025

ለማህበረሰባችን የጤና ትምህርት ፨፨፨

በዛሬው ዕለት ከ አዋሽ ጤና አጠባበቅ ጣቢያ የተውጣጡ ጤና ባለሙያዎች የጤና ኤክስቴንሽን ፕሮግራሙን ለመደገፍ በ3 ቀበሌዎች ላይ በእናቶችና ህፃናት , በክትባት , በማህፀን በር ጫፍ ካንሰር ዙሪያ ማህበረሰቡን ሰብስበው ትምህርት ሰጥተዋል ለዚህ ፕሮግራም አስተዋጽኦ ላደረጉ የቀበሌ በጎ ፍቃደኞችን እንደ ተቋም ምስጋናችንን እናቀርባለን ፨፨፨፨፨

Address

Awash

Telephone

+251938664444

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Awaash Magaalahe Xiinissok Qaafiyate Fenteeyna posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share

Share on Facebook Share on Twitter Share on LinkedIn
Share on Pinterest Share on Reddit Share via Email
Share on WhatsApp Share on Instagram Share on Telegram