06/11/2025
የአላሙራ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል አገልግሎት አሰጣጥ በተሻለ ሁኔታ ላይ እንደሚገኝ ተጠቃሚ የሆኑ የህብረተሰብ ክፍሎች ገለጹ
******************************************
ይህ የተገለጸው የአላሙራ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል የ2018 በጀት ዓመት 1ኛ ሩብ ዓመት የህዝብ ውይይት መድረክ ባደረገበት ወቅት ነው።
የሆስፒታሉ ስራ አስኪያጅ አቶ ዮስፍ ዮሄ በንግግራቸው ሆስፒታሉ በሚሰጠው ዘርፈ ብዙ አገልግሎት ከፍተኛ ቁጥር ያለው የህብረተሰብ ክፍል ተጠቃሚ ስለመሆኑ ገልጸዋል።
በዚህ ረገድ በሆስፒታሉ ቀደም ሲል ሲሰጥ የነበረውን አገልግሎት በማስቀጠልና አዳዲስ አገልግሎቶችን በማስጀመር ከፍተኛ ውጤት የተመዘገበበት መሆኑንም አቶ ዮሴፍ ገልፀዋል።
ሆስፒታሉ በየጊዜው ከሕብረተሰብ የሚነሱ ጥያቄዎችን በአግባቡ ምላሽ መስጠት የሚያስችለውን መድረክ መፍጠሩ ለአገልግሎቱ ውጤታማነት አመላካች እንደሆነም ነው ኃላፊው ያስረዱት።
ከሐዋሳ ከተማ ጤና መምሪያ የህክምና አገልግሎቶች ዳይሬክተሬት ዳይሬክተር አቶ ወ/ሰንበት ዳንኤል የሆስፒታሉ ዕድገት እየጨመረ የመጣውን የህብረተሰብ ክፍል በማስረዳት እየሰጠ ያለውን አገልግሎት ለቀጣይም በችግሮቹ ዙሪያ ጠንክሮ መስራት ይጠበቃል ብለዋል።
ሆስፒታሉ ቀደም ብሎ ከህብረተሰቡ ይነሱ የነበረውን ቅሬታዎችን በመፍታት የህክምና መገልገያ መሣሪያዎችን በመሟላት የተሻለ አገልግሎት ለህብረተሰቡ እየሰጠ መሆኑን አቶ ወ/ሰንበት ተናግረዋል።
ተሳታፊዎቹ እንደገለጹት የሆስፒታሉን አገልግሎት አሰጣጥ ከጊዜ ወደ ጊዜ ለውጥ እያሳየ እንደመጣና በተለይም የህክምና ባለሙያዎች ለህሙማን በሚያደርጉት እንክብካቤ ምስጋናቸውን አቅርበዋል።
በዚህ ረገድ በሆስፒታሉ የተጀመሩ የህንፃ ግንባታዎች ተጠናቀው አገልግሎት እንዲሰጡ፣ የአልተራሳውንድን አገልግሎትን ጨምሮ በሌሎች ላይ ጥረት እንዲደረግ ጠቁመዋል።