ማያ መካከለኛ ክሊኒክ - Maya Medium Clinic - Dr Elias

  • Home
  • Ethiopia
  • Awassa
  • ማያ መካከለኛ ክሊኒክ - Maya Medium Clinic - Dr Elias

ማያ መካከለኛ ክሊኒክ - Maya Medium Clinic - Dr Elias የተሟላ ህክምና ከስብህና ጋር ‼️

"መቀመጥ አዲሱ ሲጋራ ማጨስ ነው" " Sitting the New Smoking"👉  ረዘም ያለ እና ተቀምጦ የመቆየት ባህሪ ከማጨስ ጋር ሲወዳደር በጤና ላይ አደጋ እንደሚያመጣ የሚያሳይ ነው። 👉...
02/11/2025

"መቀመጥ አዲሱ ሲጋራ ማጨስ ነው"
" Sitting the New Smoking"

👉 ረዘም ያለ እና ተቀምጦ የመቆየት ባህሪ ከማጨስ ጋር ሲወዳደር በጤና ላይ አደጋ እንደሚያመጣ የሚያሳይ ነው።
👉 ለረጅም ሰዓታት መቀመጥ የደም ዝውውርን ስለሚቀንስ፣ የኃይል አጠቃቀምን ስለሚቀንስ እና ሜታቦሊዝም ላይ አሉታዊ ተጽዕኖ ስለሚያሳድር እንደ የልብና የደም ቧንቧ በሽታ፣ የተወሰኑ ካንሰሮች እና ዓይነት 2 የስኳር በሽታ ወደ ከባድ የጤና ችግሮች ሊመራ ይችላል።

.....  ( )✅✅✅✅✅✅✅✅✅✅✅  ♦️♦️♦️♦️ ✅ #ኢንሱሊን ሰውነታችን ሰኳርን እንዲጠቀም ስለሚያደርግ በተለያዩ ምክንያቶች  #እጥረት ካጋጠመ ወይም   ከመብል የተገኘው ብዙ ስኳር ወደ ...
28/10/2025

..... ( )
✅✅✅✅✅✅✅✅✅✅✅

♦️♦️♦️♦️

✅ #ኢንሱሊን ሰውነታችን ሰኳርን እንዲጠቀም ስለሚያደርግ በተለያዩ ምክንያቶች #እጥረት ካጋጠመ ወይም ከመብል የተገኘው ብዙ ስኳር ወደ ሴሎች ( #ህዋሳት) ባለመግባቱ ምክንያት ደማችን ውስጥ ይቀራል።

✅በዚህ ጊዜ በደም ውስጥ ሊገኝ ከሚገባው በላይ በመሆኑ ስኳር አለ እንላለን።

✅በዚህ ላይ በመመስረት የስኳር ህመም አይነቶችን በአራት እንከፍላለን

1⃣አይነት 1( ): ከፍተኛ የኢንሱሊን እጥረት

2⃣ አይነት 2( : በዋነኝነት የኢንሱሊን ባግባቡ አለመስራትና መጠነኛ የኢንሱሊን እጥረት )

3⃣የእርግዝና ስኳር( ) አንዳንድ ሴቶች ላይ በእርግዝና ወቅት የሚታይ

4⃣በተለያዩ መድሃኒቶችና የቆሽት ህመሞች፣ ወዘተ.. የሚከሰት የስኳር ህመም፤

🅰 🅰🅰እዚህ ጋር ልብ ሊባል የሚገባው ጉዳይ ስኳር ደማችን ውስጥ በዝቶ መገኘቱ አይደለም ችግሩ!

⚠️ስኳርን ሰውነታችን በአግባቡ መጠቀም ባለመቻሉ ምክንያት ሰውነታችን ሃይል ማጣትና የኢንሱሊን እጥረቱ እጅግ የከፋ ከሆነ ( ) ረሃብ፣ብዙ እየበሉ መክሳት ይመጣል።

⚠️ ይህ ከመጠን ያለፈ ስኳር ወደየሰውነታችን ክፍል እየሄደ ደምስሮችን የማቁሰልና የማጥበብ፣አንዳንድ የሰውነታችን ክፍሎች ላይ መጣበቅና ከዛ ጋር በተያያዘ የሚደርሱ የሰውነት ጉዳት ማድረስ( ምሳሌ አይናችን በዚህ መልኩ ከሚጠቁት ነው )

ስኳር እንዴት ይታወቃል❓🤔🤔
🔘🔘🔘🔘🔘🔘🔘🔘🔘

የስኳር ህመም ምልክቶች

👉የማያባራ ውሃ ጥም፣
👉የማያባራ ብዙ ሽንት፤ቀንም ማታም፣
👉ብዙ መብላት፣
👉የሰውነት ክብደት እየቀነሰ መሄድ፣
👉የአፍ መድረቅ ናቸው።

⚠️ይሁን እንጂ type 2 DM ስለሆነና ይሄ አይነት ስኳር ደግሞ ምልክት ሳያሳይ ረጅም ጊዜ የመቆየት አዝማሚያ ስላለው እነዚህ ምልክቶች በሁሉም ታካሚ ላይ አይስተዋሉም።

⚠️ከዚህም የተነሳ አብዛኛው የስኳር ታማሚ ጉዳት ከደረሰበት በኋላ ወይም በአጋጣሚ በተደረገ ምርመራ ነው የሚታወቅለት።

ስለሆነም የአሜሪካ የስኳር ህመም ማህበር ( ) 2022 ለሚከተሉት የማህበረሰብ ክፍሎች ቅድመ ምርመራ እንዲደረግ ይመክራል።ይህም በበርካታ የጥናትና ምርምር ውጤቶች ላይ በመመስረት ነው።

⚠️ማንኛውም ዕድሜው ከ45 ዓመት በላይ የሆነ፣
⚠️በእርግዝና ወቅት ስኳር የታየባቸው፣
⚠️HIV ያለባቸው፣
⚠️ሰውነት ክብደት ያላቸውና(>25kg/m2) ተጨማሪ አጋላጭ ሁኔታ ያላቸው ....
በየ የስኳር ቅድመ ምርመራ እንዲያደርጉ ይመክራል።

🔷ለመሆኑ ስኳር እንዳለ የሚጠቁሙ ምርመራዎች የትኞቹ ናቸው?🤔🤔

ክብር ለሳይንስ ይግባና ዛሬ እንደ ሽንት መቅመስ አስፈላጊ አይደለም😛😛

አራት አይነት ዋና ምርመራዎች

1⃣በባዶ ሆድ (8 ሰዓት ምግብ ሳይበላ) ተለክቶ( ): >/=126mg/dl ከሆነ

2⃣75 ግራም ደረቅ ስኳር ተበጥብጦ ከጠጡ ከ2 ሰአት በኋላ ተለክቶ( ): >/=200mg/dl ከሆነ

3⃣ከስኳር ጋር በ 3 ወር ውስጥ የተጣበቀ የሄሞግሎቢን መጠን በ%( ): >/=6.5% ከሆነ

4⃣በማንኛውም ሰዓት በተለካ ስኳር( ): >/=200mg/dl ከሆነና ከላይ የጠቀስናቸው ምልክቶች አብረው ስኳር አለ እንላለን።

በአጠቃላይ
👉ለስኳር ምርመራ ተመራጭ የሚሆኑት በባዶ ሆድ የሚለካውና የሦስት ወር ምርመራ ናቸው።

👉 አሁን ላይ በእርግዝና ላይ የሚመጣ ስኳርን ለመለየት ብቻ ነው የምንጠቀመው።

👉ሌሎች ተጨማሪ ደጋፊ ምርመራዎች
✅ : ስኳር በሽንት መውጣቱን ለማየት፣ ኬቶአሲድ መኖር አለመኖሩን ለማረጋገጥ
✅ : አይነት 1 ን ከአይነት 2 ስኳር ለመለየት
✅ ( ): ቆሽት ኢንሱሊን እያመረተ መሆን አለመሆኑን ለመለየት

👉ሌሎች ስኳር ሊጎዳቸው የሚችላቸው አካላትም ስኳር እንደታወቀ ደህንነታቸው መረጋገጥ ይኖርበታል።
✅የኩላሊት ምርመራ
✅የዓይን ምርመራ
✅የልብ ምርመራ
✅የስብ መጠን ምርመራ
✅የእግር ደምስር ጥበት ምርመራ ወዘተ መደረግ ይኖርበታል።

💉💉💉💊💊💊ህክምናውን ለማጠቃለል 💉💉💉💊💊💊

1⃣ከሕክምና አንፃር ሁለት አይነት ስኳር ነው ያለን።በኢንሱሊን የሚታከም ወይም በክኒን የሚታከም።

2⃣በክኒን ተሞክሮ እምቢ ካለ በኢንሱሊን የሚታከም ይሆናል።

3⃣ማንኛውም የስኳር ታማሚ ለተለያዩ ጉዳዮች ቀዶ ህክምናን ጨምሮ ጤና ማዕከል ተኝተው ሲታከሙ ስኳራቸው በኢንሱሊን የሚታከም ይሆናል። ክኒን የሚወስዱ ከነበረ ከሕክምና ማዕከል ሲወጡ በፊት የሚወስዱት ክኒን እንዲቀጥሉ ይደረጋል።

4⃣ኢንሱሊን በአጠቃላይ እስካሁን በመርፌ መልክ ብቻ ያለ እንጂ በክኒን መልኩ አልተዘጋጀም።ምክንያቱም ኢንሱሊን ቀላል መዋቅር ያለው ፕሮቲን በመሆኑ በጨጓራ በኩል ሲያልፍ ድራሹ ይጠፋል። ነገር ግን በዚህ ረገድ የተለያዩ አበረታች ምርምሮች እየተከናወኑ ስለሆነ በክኒን በኩል ሊመጣ ይችል ይሆናል።

5⃣ተጓዳኝ ችግሮች ካሉ በአግባቡ መታከም ይኖርባቸዋል።ምክንያቱም ስኳር ተጓዳኝ ህመሞችን ስለሚያባብስ እንደ ስብ መዛባት፣ልብ ህመም፣የደም ግፊት፣ የኩላሊት ችግር ወዘተ በየቀጠሮው ክትትል ሊደረግላቸው ይገባል።

በተረፈ የስኳር ህመም ብዙ ነገር ያለው በመሆኑ ከወሳኝ ነጥቦች ውጭ ያሉ ነገሮችን ከማብራራት እንቆጠባለን።

መልካም ጊዜ !
🍎🍎🍎🍎

  ( ) ❎❎❎❎❎❎❎❎❎❎❎በአሁኑ ወቅት: 👉422 ሚሊዮን የዓለም ሕዝብ ስኳር አለበት (በ1980 ይሄ ቁጥር 108 ሚሊዮን ገደማ ነበር!)👉በዓመት ከ>1.5 ሚሊዮን በላይ ለሆነ ሞት ምክንያት...
25/10/2025

( )


❎❎❎❎❎❎❎❎❎❎❎

በአሁኑ ወቅት:

👉422 ሚሊዮን የዓለም ሕዝብ ስኳር አለበት (በ1980 ይሄ ቁጥር 108 ሚሊዮን ገደማ ነበር!)

👉በዓመት ከ>1.5 ሚሊዮን በላይ ለሆነ ሞት ምክንያት ነው።

👉ከአደጋ ቀጥሎ ዋና የእግር መቆረጥ መንስኤ ነው።

👉ግንባር ቀደም የኩላሊት መድከም ምክንያት ነው።

👉ከሌሎች አጋር ህመሞች ጋር በመሆን (የደም ግፊት) ደም ስሮች እንዲጠቡና እንዲስተጓጎሉ ያረጋል።በዚህም በርካታ የሰውነት ክፍለች ይጐዳሉ።

👉ከሁሉ የሚበልጠው ጉዳይ ግን ይህንን ሁሉ የሚያደርገው የስኳር ህመም በአብዛኛው ምልክት አልባ ሆኖ ሳይታወቅ መቆየቱ ነው።

⚠️ለመሆኑ ስኳር ለምን ይከሰታል⁉️
🔘🔘🔘🔘🔘🔘🔘🔘🔘🔘

🟤አብዛኛው የምንመገባቸው የምግብ አይነቶች በካርቦሃይድሬት የበለፀጉ ናቸው።
🟤እንጀራ፣ዳቦ፣መኮሮኒ፣ሩዝ፣ፓስታ፣ድንች፣ኬክ፣ቸኮሌት ወዘተ በካርቦሃይድሬት የበለፀጉ ምግቦች ናቸው።

🟤አብዛኛው የዓለም ሕዝብ ከነዚህ ውስጥ አንዱን ሳይመገብ አይውልም።

🟤እነዚህ ምግቦች ከተበሉ በኋላ ወደጥቃቅን የካርቦሃይድሬት ደቃቅ ሞለኪዩሎች ይለወጣሉ።

🟤የሁሉም መጨረሻ ግን #ግሉኮስ ( #ስኳር) በመሆን ወደ ህዋሳት መድረስ ይሆናል።

🟤ህዋሳት ግሉኮስን( ) በመጠቀም ለህልውናቸው የሚያስፈልጋቸውን ሀይል ያገኛሉ።

🟤ግሉኮስ ወደ ህዋሳት ገብቶ የተፈለገውን ሀይል ያመነጭ ዘንድ አንድ #አስተናባሪ ያስፈልገዋል።

🟤ይሄ አስተናባሪም #ኢንሱሊን ( ) የሚባለው ነው።

🟤ኢንሱሊን ከቆሽት የሚመነጭ ቀላል መዋቅር ያለው ፕሮቲን ነው።

🟤ቆሽት ( ) ከኢንሱሊን ውጪ የተለያዩ ተግባር ያላቸውን ቅመም ኢንዛይሞችንና ሆርሞኖችን የሚያመርት ወሳኝ ክፍለ አካል ነው።

🟤አብዛኞቹ በቆሽት የሚመረቱ ቅመሞች ምግብ የሚያልሙ (የሚፈጩ) በመሆናቸው በተፈጥሮ እያንዳንዱ ቅመም ከተመረተ በኋላ ወደ ሚፈለግበት እስኪሄድ በየራሱ ከረጢት ተቋጥሮ ይቀመጣል።በተለያዩ ችግሮች ከተቋጠሩበት ከረጢት ከፈሰሱ ግን ራሱን ቆሽቱን ያሳርሩታል።

😜ምናልባት እናቶቻችን ቆሽቴን አታሳርረው ሲሉ ይሄ ገብቷቸው ይሆን❓🤫🤫

❇️ከስኳር አጠቃቀም ጋር በተያያዘ ሌላ የሚነሳው ክፍለ አካል #ጉበት ነው።

❇️ጉበት የተለያዩ የምግብ ንጥረ ነገሮችን ማቀነባበሪያና ማምረቻ ሆኖ ያገለግላል።

❇️በተጨማሪም የተለያዩ መድሃኒቶችን ጨምሮ ሌሎች ቆሻሻዎችን ላወጋገድ እንዲመቹ አርጎ ያበጃጃቸዋል።

❇️ብዙ ካርቦሃይድሬት ( ) ከተመገብን በኋላ ህዋሳት ከሚጠቀሙት የሚተርፈውን አቀነባብሮ #ግላይኮጅን( ) ወደሚባል የክፉ ቀን ስንቅ ለውጦ ያኖረውና ሰውነታችን በቂ ምግብ በማያገኝበት ወቅት ያን የተከማቸ ግላይኮጅን መልሶ ወደ ግሉኮስ ስኳር እየቀየረ ሴሎች እንዲጠቀሙት ያረጋል።

ይቀጥላል !!

  (  ):  ደምን ከልባችን ወደተለያዩ የሰውነት ክፍሎች  ለማድረስ በመጋቢ ደምስሮች (Arteries) ውስጥ የሚፈጠር የግፊት ሀይል ነው።  ( ): ከላይ የጠቀስነው የግፊት ሃይል ከተገቢው...
18/10/2025

( ):

ደምን ከልባችን ወደተለያዩ የሰውነት ክፍሎች ለማድረስ በመጋቢ ደምስሮች (Arteries) ውስጥ የሚፈጠር የግፊት ሀይል ነው።

( ): ከላይ የጠቀስነው የግፊት ሃይል ከተገቢው በላይ ከፍ ሲል ማለት ነው።

የደም ግፊት ወቅታዊ ምድብ የሚከተለውን ይመስላል።
የደም ግፊት ምደብ የላይኛው( ) የታችኛው( )

ተፈላጊ የደም ግፊት መጠን ( ) /=140/90 በተደጋጋሚ ከሆነ ታካሚው የህክምና ፍርሃት የወለደው ግፊት ( ) ሊኖረው ስለሚችል ቢቻል የ24 የደም ግፊት መለኪያ ተደርጎለት የግፊት ሁኔታው ሊጠና ይገባዋል። ካልሆነ ደግሞ ከ3-6 ወር ለሆነ ጊዜ ክትትል ይደረግለታል።

🔹 ቤት ውስጥ ራስን መለካት:

የሕክምና ሥፍራ ፍርሃት ወለድ ከፍተኛ ግፊት (White Coat Hypertension) ለመለየት ይረዳል።ብዙ ጊዜ ቤት ውስጥ የሚለካው ልኬት ከሕክምና ቦታ ዝቅ ያለ ነው።

🔹 24 ሰዓት የግፊት መጠን መለኪያ:

ይሄ አልፎ አልፎ ለተመረጡ ሕሙማን ብቻ የሚታዘዝ ሲሆን አለካኩም በታካሚው ክንድ ላይ ታስሮ በየ 20-30 ደቂቃው ሌሊትን ጨምሮ በቀን ከ50-100 ጊዜ ይለካል።የለካውንም አብሮ በተዘጋጀ ዲጅታል መሣሪያ ያስቀምጣል።ከዛ ወደኮምፒውተር ተገልብጦ በ24 ሰዓት ውስጥ ያለው የደም ግፊት ሁኔታ ይጠናል።

ከላይ በተገለፀው መልኩ የተለካ የደም ግፊት ውጤት ላይ ተመስርቶ ሀኪሙ ደም ግፊት አለ ወይም የለም የሚለውን ይወስንና ሕክምና ካስፈለገ የህክምናውን አይነት ይመርጣል።

😳ስለዚህ ከፍተኛ ደም ግፊት (Hypertension ) አለ የሚባለው መቼ ነው ⁉️

የተለያዩ አለካክ ዘዴዎች የተለያዩ ወሰን አላቸው።በነዚህ አለካኮች ዙሪያ የተለያዩ የህክምና ማህበራት የተለያየ፣ ነገር ግን ተቀራራቢ ወሰንን ይጠቀማሉ።በሰፊው የምንጠቀማቸው የህክምና ማህበራት ሰነዶች
♦️የአሜሪካ ልብ ማህበር/የአሜሪካ የስነ ልብ ኮሌጅ: (AHA/ACC )
♦️ የአውሮፓ የልብ ማህበር የአውሮፓ የደም ግፊት ማህበር(ESC/ESH)
♦️JNC (JOINT NATIONAL COMMITTEE)
በዚህ መሰረት ቀለል ያለው አመዳደብ የ ላይ ያለው ሲሆን

⚠️ በሐኪም ልኬት....>140/90 (የአሜሪካው ማህበር ACC/AHA 2017 130/80)
⚠️በቤት ልኬት ...135/85
⚠️በ24 ሰዓት ልኬት
✅የቀን አማካይ =135/85
✅የማታ አማካይ =120/80
✅የ24 ሰዓት አማካይ=130/80

እዚህ ላይ ልብ ሊባል የሚገባው ቁም ነገር
✅በኛ ሀገር ነባራዊ ሁኔታ በሕክምና ተቋም ስለሚለካ ሌሎቹ ለጊዜው አስፈላጊ አይደሉም።
✅የደም ግፊት ማህበራት ሰነዶች የተለያዩባቸው ነጥቦች ላይ ሐኪሞች ልምዳቸውንና ጥናቶችን እንዲሁም ሞያዊ ምክክር እየተከተሉ ይወስናሉ።
✅አንድ ሰው ከፍተኛ የደም ግፊት አለበት ከመባሉ በፊት ቢያንስ በተለያዩ 2-3 ጊዜያት ቢያንስ በሳምንት ያህል ልዩነት፣በእያንዳንዱ ጊዜ ሁለቴ ተለክቶ ከፍ ያለ እንደሆነ ነው።
✅በሁለት የተለያየ ጊዜ የታየው ልኬት ከ10mmHg በላይ ልዩነት ካሳየ ተጨማሪ ቀጠሮ ያስፈልጋል።

ከፍተኛ የደም ግፊት እንዴት ይታከማል⁉️
▪️▪️▪️▪️▪️▪️▪️▪️▪️▪️▪️

ዋናው ጉዳይ ነው።ከላይ የተጠቀሰውን የህሙማን ጥያቄ መመለስ።

ከፍተኛ የደም ግፊት መኖሩ ከተረጋገጠ ህክምናው የሚወሰነው በሚከተሉት ሁኔታዎች ላይ ነው
✅ዕድሜ
✅የጤና ሁኔታ (ተጓዳኝ ህመሞች መኖር ያለመኖር ለምሳሌ እንደ ስኳር፣የኩላሊት ህመም ወዘተ)
✅ የግፊት ልኬት መጠን

የደም ግፊት ሕክምና ሁለት አይነት ነው።

1⃣ያለ መድሃኒት የሚደረግ ክትትል
2⃣የመድሃኒት ሕክምና

1⃣ያለ መድሃኒት የሚደረግ ክትትል:
▪️▪️▪️▪️▪️▪️▪️▪️▪️▪️

ይሄ የህክምና አይነት በጣም የተጋነነ የደም ግፊት መጨመር ለሌላቸውና በግፊት ምክንያት የደረሰ ምንም ዓይነት አካላዊ ጉዳት ለሌላቸው መድሃኒት ከማስጀመር በፊት የሚመከር ያኗኗር ዘይቤ ለውጥ ላይ መሠረት ያረገ ነው።በርግጥ ለደም ግፊት ታካሚዎች ተባለ እንጂ ሁላችንም ልንከተለው የሚገባ ነው።

ጤናማ የአኗኗር ዘይቤ የሚከተሉትን ያካትታል( )

✅ጨው መቀነስ:

10/09/2025

ማያ መካከለኛ ክሊኒክ - Maya Medium Clinic - Dr Elias

👉ክሊኒካችን ክፍት ሆኖ ስራውን ከጀመረ እነሆ ድፍን ሁለት አመት ሞላው ። በዚህ ሁለት አመት ውስጥ ከጎናችን በመሆን ስትደግፉን ለነበራችሁና ፥ ክሊኒካችንን ምርጫ አድርጋችሁ አገልግሎት በማግኘት ላይ ያላችሁትን ሁሉ ከልብ እናመሰግናለን ።
🎉 ለመላው ኢትዮጵያውያን መልካም አዲስ ዓመት ይሁንላችሁ እያልን በ2018 ዓ.ም እናንተን በተሻለ ብቃት ለማገልገል የተዘጋጀን መሆኑን ስንገልፅ በታላቅ ደስታ ነው ።

👌 የተሟላ ህክምና ከስብዕና ጋር ‼️
አድራሻ ፡ ሎጊታ አሮጌው ስታድየም ጎን ከማውንቶሊቭ ት /ት ፊት ለፊት

29/08/2025

21/08/2025

(GERD)

14/08/2025

(Colonic Cancer)

‎   (Screening)‎👉  ?‎💐 የጠቅላላ ምርመራ ማለት ማንኛውም ሰው በየህድሜ ደረጃውና በፆታው በመፈረጅ የሚደረግ የአካል(Physical Examination)፤ የላቦራቶሪ(Laborator...
09/08/2025

‎ (Screening)

‎👉 ?
‎💐 የጠቅላላ ምርመራ ማለት ማንኛውም ሰው በየህድሜ ደረጃውና በፆታው በመፈረጅ የሚደረግ የአካል(Physical Examination)፤ የላቦራቶሪ(Laboratory) እና የኢሜጂንግ(Imaging) ምርመራ ነው ።

‎👉 ጠቀሜታው_ምንድነው?
‎ 💐 እንደ ዓለም ጤና ድርጅት (WHO) ዘገባ ፡ በዓለማችን ላይ ከሚከሰቱት ከሁለት ሦስተኛው በላይ የሚሆኑት ተላላፊ ያልሆኑ በሽታዎችን ቅድመ ምርመራ በማድረግና የአኗኗር ዘይቤን በማስተካከል ብቻ ማዘግየት እንዲሁም ማስቀረት ይችላል ።
‎ 💐 ስለሆነም አንድን በሽታ ወደኋላ መመለስ በማይቻልበት ደረጃ ስር ከመስደዱ በፊት ለማስቀረት (Screening) ጠቀሜታው ላቅ ያለ ነው ።

‎👉 ልንከላከላቸው የምንችላቸው በሽታዎች የትኞቹ ናቸው ?
‎ 1. የስኳር በሽታን
‎ 2. የደም ግፊትን
‎ 3. የኮሌስትሮልን
‎ 4. የካንሰርን
‎ 5. የጉበት በሽታዎችን
‎ 6. የልብ ድካምን
‎ 7. የኩላሊት በሽታን
‎ መከላከል ዋነኞቹ ናቸው ።

‎‼️በሀገራችን በአሁኑ ጊዜ እነዚህ ተላላፊ ያልሆኑ በሽታዎች በከፍተኛ ደሪጃና ፍጥነት እየተስፋፋ እንደሆነ ጥናቶች ያሳያሉ ። ለዚህም ምክንያቶቹ ፡
‎ 1. እነዚህ በሽታዎች ከመከስታቸው በፊት ብዙም ምልክት አለማሳየታቸው ነው
‎ 2. ማድረግ ባህላችን ዝቅተኛ መሆን
‎ 3. የመመርመሪያ መሳሪያዎቹ ተደራሽነት
‎ዋነኞቹ ምክንያቶች ናቸው ።

‎🎤 በማያ ክሊኒክ የቅድመ ሙሉ ምርመራ (Screening) ፡
‎ 👌እጅግ በተመጣጣኝ ዋጋ
‎ 👌 በውስጥ ደዌ ስፔሻሊስት የረጅም ጊዜ ልምድን የተላበሰ በቂ ምክርና ክትትል
‎ 👌 ሁሉም ጥቅሎች ፡ የደም ግፊት ፤ የክብደት፤ የልብ ምትና አተነፋፈስ ልኬትን ያካተተ
‎ 👌 በፍጥነትና ያለምንም መንገላታት
‎በሚከተሉት ጥቅሎች(Packages) ሙሉ ቀን ሳምንቱን በሙሉ አገልግሎት መስጠት ጀምረናል ‼️
‎ 💐 መሰረታዊ ( Basic) የምርመራ ጥቅል፡
‎ 💐 ሁሉን አዘል ( General) የምርመራ ጥቅል፡
‎ 💐 ፕሪምየም ( Premium) የምርመራ ጥቅል፡
‎☎️ በሚከተሉት ስልክ ቁጥሮች ያገኙናል
‎0912-76-53-78
‎0926-12-01-40
‎046-221-9123
‎አድራሻ ፡ ሎጊታ አሮጌው ስታድየም ጎን ከማውንቶሊቭ ት /ት ፊት ለፊት

05/08/2025

የከሰል ጭስ 🔥

  (Chemistry Tests) በማያ መ. ክሊኒክ...‼️ የተሟላ ህክምና ከስብህና ጋር ‼️አድራሻ ፡ ሎጊታ አሮጌው ስታድየም ጎን ከማውንቶሊቭ ት /ት ፊት ለፊት
04/08/2025

(Chemistry Tests) በማያ መ. ክሊኒክ...‼️

የተሟላ ህክምና ከስብህና ጋር ‼️
አድራሻ ፡ ሎጊታ አሮጌው ስታድየም ጎን ከማውንቶሊቭ ት /ት ፊት ለፊት

Address

ወልደ አማኑኤል ዱባለ ጎዳና
Awassa
01

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when ማያ መካከለኛ ክሊኒክ - Maya Medium Clinic - Dr Elias posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Practice

Send a message to ማያ መካከለኛ ክሊኒክ - Maya Medium Clinic - Dr Elias:

Share

Share on Facebook Share on Twitter Share on LinkedIn
Share on Pinterest Share on Reddit Share via Email
Share on WhatsApp Share on Instagram Share on Telegram