Beder Traditional Medicine Center-በድር ባህላዊ የህክምና ማዕከል

  • Home
  • Ethiopia
  • Bahir Dar
  • Beder Traditional Medicine Center-በድር ባህላዊ የህክምና ማዕከል

Beder Traditional Medicine Center-በድር ባህላዊ የህክምና ማዕከል ከሱዳናዊው አባታችን በወረስነው ልምድ እና ትምህርት በአሏህ ፍቃድ ፈውስ እየሰጠን እንገኛለን።

07/12/2020

ታቢዓ ድግምተኛዋ የኢብሊስ ልጅ...@
________________________________
ታቢዓ ከኢብሊስ ሴት ልጆች አንዷ ስትሆን የሰው ልጆችን ማለትም ሴቶችን አዛ በማድረግ ራሷን የጠመደች እርኩስ እና ድግምተኛ ፍጥረት ናት።
ታቢዓ ሴቶችን(እህቶቻችንን) አዛ የምታደርግበት ዋነኛ መንገድ ወንድ ልጆች ሲረገዙ ፅንሶችን በማጨናገፍ እና ህፃኑ ልክ እንደተወለደ አንቃ በመግደል ነው።
ታቢዓ በመባል ከሚታወቁት የኢብሊስ ልጆች በዋነኝነት ይህን ተግባር ከሚፈፅሙት አንዷ ﺃﻡ ﺍﻟﺼﺒﻴﺎﻥ / የልጆች እናት በመባል ትታወቃለች።
ይህች ኡመ ሲብያን/የልጆች እናት ተብላ የምትታወቀው የኢብሊስ ልጅ ዘውትር ወንድ የፀነሱ ሴቶችን እየተከተለች ፅንሱን ታጨናግፋለች። ይህን የምትፈፅመውም እሷ ሴት እንጂ ወንድ ልጅን ለመውለድ ባለመታደሏ ወንድ በሚፀንሱ ሴቶች ቅናት ስለሚያድርባት ነው።
ይህች እርኩስ አንዳንዴም ህፃናት ያለ ጠባቂ ረጅም ሰዐት ብቻቸውን ሲያሳልፉ ሰርቃ የመውሰድ አባዜም አለባት።
አብዝሀኛውን ግዜ በዚህች አይነቷ የኢብሊስ ልጅ የተጠቁ ሴት እህቶች/እናቶች በተለያዩ ሁኔታዎች ታቢዓ የተባለችውን ጠላታቸውን ሊመለከቱ ይችላሉ።
ለምሳሌ፦ታቢዓ ሴቶቻችን በሚተኙ ግዜ በህልም አማካይነት በጥቁር ሴት ተመስላ እየመጣች ታስጨንቃቸዋለች።ወይም በጥቁር እንስሳ ተመስላ በመምጣት ሆዳቸውን ትደበድባለች። ያን ህልም ሲመለከቱ ሴቶቹ ፅንስ የፀነሱ እንደሆን አብዝሀኛውን ግዜ ፅንሱ የመጨናገፉ እድል የሰፋ ነው።
ይህች ታቢዓ የተባለች ሩሃኒይ የተጠናወተቻቸው ሴቶች የሚከተሉት ምልክቶች ይታይዋታል፦
1፦በእርግዝና ግዜ ከባሏ ጋር መነጫነጭ።
2፦በተደጋጋሚ ሁኔታ ታቢዓ በህልም እየመጣች እንደ ጥቁር ሴት እና እንደ አስፈሪ እንስሳ ሆና ቅዠት መፍጠር እና መሳደብ።
3፦ከስጋ ዘመድ በህልም መገናኘት(ጂማዕ ማድረግ)
4፦የሰንበር እና የቁርጥማት ስሜት...
5፦የወር አበባ ያለ ግዜው መፍሰስ
6፦ያለ በቂ ምክንያት መጨናነቅ እና ማልቀስ።
7፦የፅንስ መጨናገፍ፣ የፅንስ መሞት፣ በወሊድ ግዜ የህፃኑ መሞት እና የልጆች ከተወለዱ በኋላ ድንገት መሞት።
# መፍትሄው
ያው ንፅህና ከራስ ይጀምራል አይደል ሚባለው በሀገሬው ወግ!!! እኮ ስለዚህ መጀመርያ ቤቶቻችንን ከየትኛውም አይነት የሸይጣን ዝርያ ሱረቱል በቀራን ቤት ውስጥ በመቅራት እናፀዳዋለን።
በመቀጠልም ሩቅያ የተቀራበትን ውሀ መጠጣት እና በርዞ መታጠብ።በወይራ ዘይት ላይ ሱረቱል ጂንን(ቁል ኡሂያ) ቀርቶ ዘይቱን መቀባት።
የታጠብንበትን እጣቢ ወደ ሽንት ቤቶች እና ወደ ቆሻሻ ስፍራ እንዳይፈስ መጠንቀቅ ለተቀራበት የሩቅያ አያ ክብር ነው።
ማሳሰብያ፦ቤቶቻችንን ከቆሻሻ መንፈሶች ለማፅዳት ሴት እህቶቻችን ሱረቱል በቀራን የማይችሉ እንደሆን ወንዶች ልትቀሩበት ይገባል።እህቶቻችን ጌጦቻችን ናቸው'ና እንንከባከባቸው!!!

06/10/2020

እራሶትንም ሆነ ቤተሰቦን በዚክር ይከላከሉ @
1ኛ. ታማሚዎች ጠዋትና ማታ እራሳቸውን የሚፈውሱበት ጊዜ፤
2ኛ. በሚተኙበት ጊዜ፤
3ኛ. ዘይትና ውሃ በሚደባበሱበት ወቅት፤
4ኛ. በትፍታ በዘይተዘይቱን በውሃና በማር ላይ ሲቀሩ፤
መደረግ የሚገባቸው ውዳሴ (ዚክር) እና ዱአዎች የሚከተሉት ናቸው:–
ﺑِﺴْﻢِ ﺍﻟﻠﻪ ‏( ﺛﻼﺛًﺎ ‏) ، ﺃَﻋُﻮﺫُ ﺑِﺎﻟﻠﻪِ ﻭَﻗُﺪْﺭَﺗِﻪِ ﻣِﻦْ ﺷَﺮِّ ﻣَﺎ ﺃَﺟِﺪُ ﻭَﺃُﺣَﺎﺫِﺭُ . ‏( ﺳﺒﻊ ﻣﺮﺍﺕ ‏) ‏( 66 ‏) .
ﺃَﺳْﺄَﻝُ ﺍﻟﻠﻪَ ﺍﻟْﻌَﻈِﻴﻢَ ﺭَﺏَّ ﺍﻟْﻌَﺮْﺵِ ﺍﻟْﻌَﻈِﻴﻢِ ﺃَﻥْ ﻳَﺸْﻔِﻴَﻚ . ‏( ﺳﺒﻊ ﻣﺮﺍﺕٍ ‏) ‏( 52 )
ቢስሚላህ (ሶስትጊዜ) አዑዙ ቢላሂ ወቁድረቲሂ ሚን ሸሪ ማ አጂዱ ወኡሐዚሩ፤ (ሰባት ጊዜ) በማለት የታመመን
ቦታ በእጅ በመያዝ መቅራት፤
ትርጉም ( ካጋጠመኝ ሸርና ከምፈራውም ሁሉ በአላህ ሥም በችሎታው እጠበቃለሁ) ማለት ነው፤
ﺑِﺴْﻢِ ﺍﻟﻠﻪِ، ﺃَﻋُﻮﺫُ ﺑِﻜَﻠِﻤَﺎﺕِ ﺍﻟﻠﻪِ ﺍﻟﺘَّﺎﻣَّﺔِ ﻣِﻦْ ﻏَﻀَﺒِﻪِ ﻭَﻋِﻘَﺎﺑِﻪِ ﻭَﺷَﺮِّ ﻋِﺒَﺎﺩِﻩِ، ﻭَﻣِﻦْ ﻫَﻤَﺰَﺍﺕِ ﺍﻟﺸَّﻴَﺎﻃِﻴﻦِ، ﻭَﺃَﻥْ ﻳَﺤْﻀُﺮُﻭﻥِ ِ
አዑዙ ቢከሊማቲላሂ ታማቲ ሚን ገደቢሂ ወዒቃቢሂ ወሚን ሸሪ ዒባዲሂ ወሚን ሐመዛቲ ሸያጢኒ አን የሕዱሩኒ፤
ትርጉም ፦ ከአላህ ከቁጣው፤ ከቅጣቱ፤ ከባሪያው ሸሮች፤ በሰይጣናትም መጥፎ ጉትጎታና እንዳይቀርቡኝም፤ በአላህ
(በእውነትና በፍትሕ) ሙሉ በሆኑ ንግግሮቹ እጠበቃለሁ፤
 አዑዙ ቢከሊማቲላሂ ታማቲ ሚን ሸሪ ማ ኸለቅ፤
ﺃَﻋُﻮﺫُُ ﺑِﻜَﻠِﻤَﺎﺕِ ﺍﻟﻠﻪِ ﺍﻟﺘَّﺎﻣَّﺎﺕ ﻣِﻦْ ﺷﺮِّ ﻣَﺎ ﺧَﻠَﻖَ
ትርጉም፦ አላህ ከፈጠረው ሸር ሁሉ፤ በአላህ (በእውነትና በፍትሕ)ሙሉ በሆኑ ንግግሮቹ እጠበቃለሁ፤
 አዑዙ ቢከሊማቲላሂ ታማቲ ሚንኩሊ ሸይጣኒ ወሃማ ወሚን ኩሊ ዓይኒ ላማ ፤ትርጉም፦ ከሰይጣኖችና (እባብ ጊንጥ
ከመሳሰሉ) ከተናዳፊዎች፤ ጎጂ ከሆነ የሰው አይን፤ በአላህ ሙሉ በሆኑ ንግግሮቹ እጠበቃለሁ።
በዚህ ዱዓ ነብዩ ኢብራሂም (ሰላም ለነሱ ይሁንና) ልጆቻቸውን ኢስማዒልንና ኢስሃቅን ከሸር የሚጠበቁበት ነበር፤
ﺃَﻋُﻮﺫُُ ﺑِﻜَﻠِﻤَﺎﺕِ ﺍﻟﻠﻪِ ﺍﻟﺘَّﺎﻣَّﺎﺕ ﻛُﻠِّﻬُﻦَّ، ﻣِﻦْ ﺷﺮِّ ﻣَﺎ ﺧَﻠَﻖَ ‏( 62 ‏) .
ﺃَﻋُﻮﺫُ ﺑِﻮَﺟْﻪ ﺍﻟﻠﻪِ ﺍﻟْﻜَﺮِﻳﻢِ، ﻭَﺑِﻜَﻠِﻤَﺎﺕِ ﺍﻟﻠﻪِ ﺍﻟﺘَّﺎﻣَّﺎﺕِ ﺍﻟﻼَّﺗِﻲ ﻻ ﻳُﺠَﺎﻭِﺯُﻫُﻦَّ ﺑَﺮٌّ ﻭَﻻ ﻓَﺎﺟِﺮٌ، ﻣِﻦْ ﺷَﺮِّ ﻣَﺎ ﻳَﻨْﺰِﻝُ ﻣِﻦَ ﺍﻟﺴَّﻤَﺎﺀِ ﻭﺷَﺮِّ ﻣَﺎ ﻳَﻌْﺮُﺝُ ﻓِﻴﻬَﺎ، ﻭَﺷَﺮِّ ﻣَﺎ ﺫَﺭَﺃَ ﻓِﻲ ﺍﻷَﺭْﺽِ ﻭَﺷَﺮِّ ﻣَﺎ ﻳَﺨْﺮُﺝُ ﻣِﻨْﻬَﺎ، ﻭَﻣِﻦْ ﻓِﺘَﻦِ ﺍﻟﻠَّﻴْﻞِ ﻭَﺍﻟﻨَّﻬَﺎﺭِ، ﻭَﻣِﻦْ َﻃﻮﺍﺭِﻕ ﺍﻟﻠَّﻴْﻞِ ﻭَﺍﻟﻨَّﻬَﺎﺭِ ﺇﻻَّ ﻃَﺎﺭِﻗًﺎ ﻳَﻄْﺮُﻕُ ﺑِﺨَﻴْﺮٍ، ﻳَﺎ ﺭَﺣْﻤَﻦ
አዑዙ ቢከሊማቲላሂ
ታማቲ፤ አለቲ ላ ዩጃዊዙሁነ በሩን ወላ ፋጂሩ፤ ሚን ሸሪ ማ ኸለቀ፤ ወበረአ ወዘረአ፤ ወሚን
ሸሪ ማየንዚሉ ሚነ ሰማኢ፤ ወሚን ሸሪ ማ የእሩጅ ፊሃ፤ ወሚን ሸሪ ዘረአ ፊል አርዲ፤ ወሚን ሸሪ ማ የኽሩጁ ሚንሃ፤
ወሚን ሸሪ ፊተኒ ለይሊ ወነሃሪ፤ ወሚን ሸሪ ኩሊ ጠዋሪቂ ኢላ ጣሪቀ የጥሩቁ ቢኸይሪ ያ ረሕማኑ፤
ትርጉም፦ ፃዲቅም ሆነ አመፀኛ በማይጥሳቸው (በእውነትና በፍትሕ) ሙሉ በሆኑ የአላህ ንግግሮች፤ ከፈጠራቸው
ካሰማራቸው (አውሬ) እና ካበቀለው ሸር፤ ከሰማይ ከወረደ ሸርና ከሚወጣም ሸር፤ በምድርም ላይ ከተዘራ ሸር፤
ከምድርም

30/09/2020

@@@የአይነናስ የቡዳ ምልክቶች@@
1.መክሳት
2.በቤተሰብ የሌለ የፊት ቡጉር
3.የቆዳ መላላጥ
4. የፊትና ሰውነት መቁሰል
6.የትዳር አለመሳካት ። ወንድ ከሆነ ማግባት መፍራት ሴት ከሆነች ትዳር መራቅ ወይም ትዳር ይርቃቸዋል።
7.ሰው ፊት ማውራትና መናገር መፍራት። ነገሮችን እንደ ከዚህ ቀደም በድፍረት ማድረግ አለመቻል።
8.በተዋወቁት ሰው ሁሉ መጠላት። ጥሩ ስራ ሰርቶ ምስጋና ቢስ መሆን።
9.የብብት የ ፊንጢጣ መቁሰል መላላጥ።
10.ሰውን አለማመን መጠራጠር።
11. በእንቅልፍ ልብ ጥርስ ማንገጫገጭ
12. ከንፈር መብላት
13. ሰውነት ማሳከክ / ሰውነት አብጦ አብጦ መፈንዳት
14. በጣም ሰውነት መሞቅ እና ድንገተኛ ማንቀጥቀጥ
15. እንዲህ እንዲህ ቦታ ያምራል የተባልነው ቦታ የእመም ስሜት መኖር
16. ዝምብሎ መነጫነጭና ማልቀስ መፈለግ
እና የመሳሰሉት በጥቂቱ ናቸው
እነኚህ ምልክቶች ከ6 በላይ ከላይ ከተገኘቦት ምልክቶች አሉብን ማለት ነው።
እነኚህ ምልክቶች ከ 20 ምልክቶች ከ ዶክተር አቡ ፈርሀን መጣጥፍ ውስጥ የተወሰዱ ናቸው።
@@@ህክምናው @@@
በራስ የሚደረግ ህክምና
አዘውትሮ ሱራ አል ኢኽላስን ጥዋት ጥዋት 3 ግዜ መቅራት ።
ሱራ አል ናስን 7 ግዜ ጥዋት መቅራት
ወደ አላህ መመለስ እና ሶላት ዚክር እና ኢባዳ ላይ መበርታት
ይህን አድርገው መፍትሄ ካጡ በስልክ ቁጥራችን ደውለው ያናግሩን በድር መንፈሳዊ ህክምና ባህርዳር

30/09/2020

# የተረጨ # ድግምት # መገለጫዎቹ
ﺍﻋﺮﺍﺽ ﺍﻟﺴﺤﺮ ﺍﻟﻤﺮﺷﻮﺵ
መገንዘብ ያለብን፦
የሚረጭ ሲሕር እንደ ሁኔታው፣እንደ ጠባዩና አኳኅኑ ታይቶ ስለሚረጭ በቅጽል ስሙ ያኳኋን ድግምት ይሰኛል። ለምን ቢባል ባብዛኛው ሲሕር አድራጊው ግለሰብ ፍላጎት በተደራጊው ሁኔታና ቦታ ላይ የተመሠረት በመሆኑ ነው።
በአብዛኛው ድግምቱ ሊሰራበት በተፈለገው ግለሰብ ቤት በር ወይም ሱቅ በር አልያም ግለሰቡ ያልፍበታል በተባሉ መንገዶች ላይ ነው የሚረጨው።
የቤቱ ውስጠኛውና የውጩ ግድግዳ ክፍል፣
በልብሶች ላይ፣
በአልጋ ላይ፣
በሚመቸው መልኩ ሳሒሩ ጠንቋዩ ባዘዘው መሠረት የተለያዩ ሽርኪያት የሆኑ መነባንቦችን እያነበነበ ድግምቱን ከአፈር ወይም ከውሃ አልያም ከሌሎች ነገሮች በመቀላቀል ይረጨዋል።ከውሃ ከሚቀላቀለው ይልቅ ከአፈር የሚቀላቀለው ትንሽ የከፋና ጠንከር ያለ ነው።
ታድያ አላህ ሊፈትነው የፈለገውን ግለሰብ በሲሕሩ ይጠቃል ።ለአካላዊና መንፈሳዊ ጉዳትም ይዳረጋል። በሚገጥመው ነገር የታገሰ።ወደ ጌታው የተጠጋ መፍትሄውን ያቀርብለታ።
መገለጫዎቹን እነሆ፦
1-የታችኛው የእግር ክፍል ከፍተኛ የሆነ ሕመም መሰማት።
2-ከጉልበት በታች በአለው ክፍል በጣም የማቃጠልና የመጋል ወይም በተቃራኒው በጣም የመቀዝቀዝና የመብረድ ስሜቶች መስተዋል።
3-እግር ላይ ወይም ታፋ ላይ ወደ ጥቁርነት ያደላ አረንጓዴ ወይም ሰማያዊ የሆነ ትናንሽ ሽፍታ የመሰሉ ነገሮች መውጣት። ምልክቱ በፍጥነት ይከስምና ይበቅላል ይወገድና ይመለሳል
4-አንዳንዴ እግር ላይ ጎልቶ የሚሰማ የደም ስር ትርታ መሰማት።
5-ቁርአን በምንቀራበት ወቅት ጉልበት ላይና ታችኛው የእግር ክፍል የመነፋፋትና የማበጥ ነገሮች መታየት።
6-እግር ላይ እብጠት አልያም እጢ መከሰት በዚህም የተነሳ ከፍተኛ ህመም መሰማት። ወይም እከክ ዓይነት በሚመስል መልኩ በከፍተኛ ሁኔታ በማሳከክ እያበጠ በመፈንዳት መክሰም እንደገና መመለስ።
7-የተረጨው ሲሕር የነካውን የአካል ክፍል በሙሉ ሙቀት ወይም ቅዝቃዜ እየተሰማው በህመም ይሰቃያል
በዚህም የተነሳ መጥፎ ስሜት ስለሚሰማው ደስተኛ አይሆንም ።
8-አብዛኛው የተረጨ ድግምት (በሲሕረል መርሹሽ )በሳይንሱ የሕክምና ዘዴ ምንም መፍትሄ አይኖረውም። በብዛት ከእግር ጀምሮ እስከ ታፋ መገጣጠሚያ ድረስ በሚሰሙ የህመም ስሜቶች ነው መገለጫዎቹ የሚለዩት።
ህመሙ አንዳንዱ የውስጥ እግሩ ሌላው እስከ ቁርጭምጭሚቱ ገሚሱ እስከ ጉልበቱ አንዳንዱ እስከ ታፋ መገጣጠሚያው ድረስ ከፍተኛ ህመም፣ማቃጠል፣ማሳከክና መብላት ስሜቶች ይሆናል።
9-የተለያዩ ምልክቶች በድንገት መታየትና መክሰም በአጋጣሚ መሰማትና መጥፋት እንደገና መመለስ የዚህ ዓይነቱ ምልክቶች የሚከሰት ከሆነ የተረጨ ሲሕር መገለጫ መሆኑን በቀላሉ እንረዳለን።
10-በተረጨ ሲሕር የተጠቁ ግለሰቦች የሚያዩት ሕልሞች አስቀያሚና አስፈሪና ነው። በዚህ ዓይነቱን አስቀያሚ፣ አስቸጋሪ፣ረባሽ፣ አስደንጋጭና አስፈሪ የሆነ ሕልሞችን እንዲመለከቱ የሚደረጉት አካላችን በሰረጹ በድግምቱ በተወከሉ ጂኞች አማካይነት መሆኑን መገንዘብ ይገባናል።
11-በንቃተ ህሊና ሳለን ቤት ውስጥና ከቤት ውጭ ያልሆኑ የተመሰሉ አልያም ብዥ የሚሉብን ነገሮችን መመልከት ለምሳሌ፦ ቤት ውስጥ በኖርማል ሁኔታ እንደምናያቸው ነፍሳት ማለትም እንደ ጉንዳን ፣በረሮ ና ትላትል ሁሉ በመምሰል ደመቅ ሰብሰብ በዛ ባለ አኳኋን መታየት ወዲያው ግን ወደ እውነተኛ ገጽታቸው መመለስ።አልያም ሙሉ በሙሉ መሰወር።
12-በቤቱ ግድግዳ፣ጣሪያና በቤቱ ውስጥ ታማሚው ብቻ የሚያደምጠው ሰቅጣጭ የሆነ የጩኸት ድምጾች። እምብዛም ያልተለመዱ ሠላም የሚነሱ ምክንያታቸው ያልታወቀ አላማቸውን መለየት የሚያዳግቱ መገለጫዎ

23/09/2020

የሲህር ምልክቶች
በጥቂቱ
1.የእይታ መዛባት። በራሪ ነገሮችን በአይን ማየት ። ለሰው የማይታዩ ነገሮችን መመልከት።
2. በህልም አብዝቶ አይጦችን ጦጣና እባቦችን መመልከት።
3. ለሰው የማይሰሙ ለኛ ብቻ የሚሰሙ መንሾካሾኮችን መስማት። ሰው ያላለው ነገር ግን ሰው ያለው የሚመስል መልእክቶችን ድንገት መስማት።
4.እራስን ማጥፋት መመኘት። ነገሮች ሁሉ ሲያማሩን መፍትሄው ወደራስ ማጥፋት ይሄዳል።
5. በሰውነት አንድ ቦታ ብቻ ለይቶ ማመም።
6. ከፍሎ የሚይዝ የራስ ህመም።
7.ሳምንቱን ወሩን ሙሉ ጥሩ ዜና አለመስማት። ጥሩ ነገር ብንሰማ ሁሉ አለመደሰት ማዘን።
8. በህል አያትን ወይም የሞተን ሰው መላልሶ ማየት አመድ ላይ መቆም።
9.ለሊት በተኙበት መጮህ ። የሚያስጠላ የተቆራረጡ ህልሞችን ማየት።
10. የሽንት መሽተት። ውሀ ቢጠጡ መድሀኒት ቢወስዱ የሽንት ሽታ መኖር። ልብ ይበሉ ይህ ከህክምና ጋር የሚያገናኘው ችግርንም አመላካች ነው
ህክምናው
በግል ወደ አላህ መቃረብና ቁርአንን አዘውትሮ መቅራት። መስገድ። አያተል ኩርሲ መቅራት። ይህ ካልሆነ ግን ሩቃ ማስቀራት ወይም በካሴት ቀርፆ ማዳመጥ

የኩላሊት ጠጠር ለማሟሟት ምንማድረግ እንዳለብን ብዙዎቻችን ላንገነዘብ እንችል ይሆናልእስቲ ይህንን ተግብሩከሥራ ሥር ዘሮች የሚመደበው ዝንጅብል በሻይመልክ በማዘጋጀት ለጉንፋንና ተያያዥነት ላላ...
06/09/2020

የኩላሊት ጠጠር ለማሟሟት ምን
ማድረግ እንዳለብን ብዙዎቻችን ላንገነዘብ እንችል ይሆናል
እስቲ ይህንን ተግብሩ
ከሥራ ሥር ዘሮች የሚመደበው ዝንጅብል በሻይ
መልክ በማዘጋጀት ለጉንፋንና ተያያዥነት ላላቸው ችግሮች መፈወሻ ሲውል ይስተዋላል። ይሁን እንጂ ዝንጅብል ከዚህ
ባለፈ በርካታ ጠቀሜታዎች አሉት።
ከነዚህም በመተንፈሻ አካል ላይ ለሚከሰቱ የጤና እክሎችና በሽታዎች ማከሚያነት በመዋል በተፈጥሮው ጥገኛ ህዋሳትን፣ ቫይረስን፣ ባክቴሪያዎችንና
ለሰውነት መቆጣትና ሽፍታ መንስኤ የሆኑ ነገሮችን መዋጋት
የሚችል የሆነ ፍቱን ንጥር ሲሆን ከዚህም ባለፈ በርካታ የጤና ጠቀሜታዎች ያሉት መሆኑ ባለንበት ዘመን ገበታ ላይ
የማይታጣ አስፈላጊው ነገር ሆኗል።
በቪታሚን ሲ፣ በማግኒዥየምና በሌሎች አስፈላጊ ማዕድናት
የበለጸገው ዝንጅብል፥ አካላችን በሽታን የመከላከል አቅሙን በማዳበር፣ከህመም ቶሎ ለማገገም፣ የምግብ መፈጨትን ለማስተካከል፣ አስምን ለመከላከልና ለመዋጋት እጅግ አስፈላጊውና ወሳኝ ነው። ከዚህም በላቀ መልኩ ለተስተካከለ የልብ ስርአት፣ አደገኛ የሆነን ኢንፍሉዌንዛን
ለመዋጋት ብሎም ለማጥፋት ፣ የጡንቻ ህመምን ለማስወገድ፣
ለምግብ መንሸራሸር ሥርዓት፣ ለተስተካከለ
የኦክስጅን ዑደት ከፍተኛ አስተዋጽኦ አለው።
ከላይ ከተዘረዘሩት ብዙዎሽ ከሚያውቁት ጠቀሜታዎች
ለየት ያለ ጠቀሜታ።
የኩላሊት
ጠጠርን ማሟሟት፣ ጉበትን ማጥራትና ማጽዳት እንዲሁም
ለካንሰር አጋላጭ የሆኑ ህዋሶችን መግደል
ይህን ጠቀሜታ የጎላው በመሆኑ ፈጥነን እንጠቀም።
• # ሁለት_ብርጭቆ ውሃ
• # ግማሽ የሻይ ማንኪያ በደንብ የተፈጨ ዝንጅብል
( ለጋው ቢሆን ይመረጣል)
• # ግማሽ የሻይ ማንኪያ ተፈጭቶ የደቀቀ እርድ
# እነዚህን_ውህዶች_ከ7 -10 # ደቂቃ_በማፍላት_ማዘጋጀት
• # በወለላ_ማር_በማጣፈጥ_መጠቀም
አለብን

06/09/2020

ታቢዓ ድግምተኛዋ የኢብሊስ ልጅ...
________________________________
ታቢዓ ከኢብሊስ ሴት ልጆች አንዷ ስትሆን የሰው ልጆችን ማለትም ሴቶችን አዛ በማድረግ ራሷን የጠመደች እርኩስ እና ድግምተኛ ፍጥረት ናት።
ታቢዓ ሴቶችን(እህቶቻችንን) አዛ የምታደርግበት ዋነኛ መንገድ ወንድ ልጆች ሲረገዙ ፅንሶችን በማጨናገፍ እና ህፃኑ ልክ እንደተወለደ አንቃ በመግደል ነው።
ታቢዓ በመባል ከሚታወቁት የኢብሊስ ልጆች በዋነኝነት ይህን ተግባር ከሚፈፅሙት አንዷ ﺃﻡ ﺍﻟﺼﺒﻴﺎﻥ / የልጆች እናት በመባል ትታወቃለች።
ይህች ኡመ ሲብያን/የልጆች እናት ተብላ የምትታወቀው የኢብሊስ ልጅ ዘውትር ወንድ የፀነሱ ሴቶችን እየተከተለች ፅንሱን ታጨናግፋለች። ይህን የምትፈፅመውም እሷ ሴት እንጂ ወንድ ልጅን ለመውለድ ባለመታደሏ ወንድ በሚፀንሱ ሴቶች ቅናት ስለሚያድርባት ነው።
ይህች እርኩስ አንዳንዴም ህፃናት ያለ ጠባቂ ረጅም ሰዐት ብቻቸውን ሲያሳልፉ ሰርቃ የመውሰድ አባዜም አለባት።
አብዝሀኛውን ግዜ በዚህች አይነቷ የኢብሊስ ልጅ የተጠቁ ሴት እህቶች/እናቶች በተለያዩ ሁኔታዎች ታቢዓ የተባለችውን ጠላታቸውን ሊመለከቱ ይችላሉ።
ለምሳሌ፦ታቢዓ ሴቶቻችን በሚተኙ ግዜ በህልም አማካይነት በጥቁር ሴት ተመስላ እየመጣች ታስጨንቃቸዋለች።
ወይም በጥቁር እንስሳ ተመስላ በመምጣት ሆዳቸውን ትደበድባለች።
ያን ህልም ሲመለከቱ ሴቶቹ ፅንስ የፀነሱ እንደሆን አብዝሀኛውን ግዜ ፅንሱ የመጨናገፉ እድል የሰፋ ነው።
ይህች ታቢዓ የተባለች ሩሃኒይ የተጠናወተቻቸው ሴቶች የሚከተሉት ምልክቶች ይታይዋታል፦
1፦በእርግዝና ግዜ ከባሏ ጋር መነጫነጭ።
2፦በተደጋጋሚ ሁኔታ ታቢዓ በህልም እየመጣች እንደ ጥቁር ሴት እና እንደ አስፈሪ እንስሳ ሆና ቅዠት መፍጠር እና መሳደብ።
3፦ከስጋ ዘመድ በህልም መገናኘት(ጂማዕ ማድረግ)
4፦የሰንበር እና የቁርጥማት ስሜት...
5፦የወር አበባ ያለ ግዜው መፍሰስ
6፦ያለ በቂ ምክንያት መጨናነቅ እና ማልቀስ።
7፦የፅንስ መጨናገፍ፣ የፅንስ መሞት፣ በወሊድ ግዜ የህፃኑ መሞት እና የልጆች ከተወለዱ በኋላ ድንገት መሞት።
# መፍትሄው
ያው ንፅህና ከራስ ይጀምራል አይደል ሚባለው በሀገሬው ወግ!!! እኮ ስለዚህ መጀመርያ ቤቶቻችንን ከየትኛውም አይነት የሸይጣን ዝርያ ሱረቱል በቀራን ቤት ውስጥ በመቅራት እናፀዳዋለን።
በመቀጠልም ሩቅያ የተቀራበትን ውሀ መጠጣት እና በርዞ መታጠብ።በወይራ ዘይት ላይ ሱረቱል ጂንን(ቁል ኡሂያ) ቀርቶ ዘይቱን መቀባት።
የታጠብንበትን እጣቢ ወደ ሽንት ቤቶች እና ወደ ቆሻሻ ስፍራ እንዳይፈስ መጠንቀቅ ለተቀራበት የሩቅያ አያ ክብር ነው።
ማሳሰብያ፦ቤቶቻችንን ከቆሻሻ መንፈሶች ለማፅዳት ሴት እህቶቻችን ሱረቱል በቀራን የማይችሉ እንደሆን ወንዶች ልትቀሩበት ይገባል።እህቶቻችን ጌጦቻችን ናቸው'ና እንንከባቸው__

የውሀ ሰፋሪ ጅኖች ሲህር (የመሪድ ቤተ ዘመዶች)እነኚህ ጅኖች እንደስማቸው ውሀ ሰፋሪ የተባሉበት ምክንያት በፈሳሽ መልክ የሚሰሩ ሲህሮች ላይ ስለሚዘወትሩ ነው፡፡ አንድ ሰው በመጠጥ ላይ ውሃ ...
06/09/2020

የውሀ ሰፋሪ ጅኖች ሲህር (የመሪድ ቤተ ዘመዶች)
እነኚህ ጅኖች እንደስማቸው ውሀ ሰፋሪ የተባሉበት ምክንያት በፈሳሽ መልክ የሚሰሩ ሲህሮች ላይ ስለሚዘወትሩ ነው፡፡ አንድ ሰው በመጠጥ ላይ ውሃ ሚሪንዳ ኮካ እና የሚጠጡ ነገሮች ላይ በሙሉ ሲህር ሲሰራ እነኚህ ጅኖች ናቸው ሲህሩ እንዲሰራ የሚያደርጉት እነኚህ ጅኖች ለሲህሩ እገዛ ይላካሉና በዚያም ምክንያት ውሀ ሰፋሪ የሚል መጠርያ አላቸው ፡፡ ምልክታቸው፡፡
1.ውሃ ባይጠጡም ሆዶት መንቦጫቦጭ ልክ ውሀ እንደያዘ፡፡
2.ውሃ ማስታወክ ፡፡ ውሀ ሲባል ንፁህ ውሃ ሳይሆን ምግብ ያልያዘውን ፈሳሽ ማስታወክ፡፡
3.የሆድ እብጠት ፡፡ ይህ እብጠት በቀላሉ በመጀመር ሴት ከሆነች አርግዛ ነው የሚል ስያሜ ሲያሰጣት ወንድ ከሆነ ደግሞ እንደ ቦርጭ ይቆጠራል፡፡ በአልትራ ሳውንድም ሲታይ ከፈሳሽ ውጭ ምንም አይነት ምልክት አያሳይም፡፡
4.የአንጓ ቁርጥማት፡፡ ይህ እግር እጅ አንጓዎችን እየተከተለ ይቆረጣጥማል፡፡
5.የአፍንጫ መዘጋት፡፡ ይህም ማሽተት እስከማይችሉበት ድረስ አፍንጫቸው ይዘጋል፡፡ ብሎም ሲናፈጡ እጅግ የደረቀና ከደም ጋር የተቀላቀለ ንፍጥ ይወጣል፡፡
6. ከልክ ያለፈ ድብርት፡፡ ይህ መለያ የሆነ ምልክት ነው፡፡ ከነኚህ ምልክቶች ጋር የድብርት ምልክት ከኖረ በቀጥታ የዚህን ጅን ሲህር ጥቃት አመላካች ነው፡፡
7.የእንቅልፍ ማጣት፡፡ ልክ ምሽት ሲቀርብ አይን ፍጥጥ ብሎ ማደር ፡፡ እንቅልፍ ከአንድ ወይም ከሁለት ሰአት ውጭ መተኛት አለመቻል፡፡
ለዚህም ህክምና ምልክት የሚታይቦት ከሆነ
1.ሲተኙ በሱና መተኛት
2.ከእንቅልፎ ሲባንኑ ዱአ አድርገው መተኛት
3.አያተል ኩርሲ መቅራት

እንዳትወልድ የሚሰራ ሲህር (ልጅ እንዳያገኙ የሚደረግ ሲህር)ይህ በሴቶች ላይ እንደሚታየው ሁሉ በወንዱ ላይ ይታያል፡፡1.የስፐርም ማነስ ፡፡ ከዚህ በፊት ልጅ እንኳ ቢኖረው አሁን ግን መውለድ...
06/09/2020

እንዳትወልድ የሚሰራ ሲህር (ልጅ እንዳያገኙ የሚደረግ ሲህር)
ይህ በሴቶች ላይ እንደሚታየው ሁሉ በወንዱ ላይ ይታያል፡፡
1.የስፐርም ማነስ ፡፡ ከዚህ በፊት ልጅ እንኳ ቢኖረው አሁን ግን መውለድ አይችልም ምክንያቱም እስፐርም ሴል ስለሚያንስ፡፡
2. የወሲብ ድክመት ልክ ሚስቱ ጋር ሲዘጋጅ ብልቱ ይዝለፈለፋል፡፡ ከሌላ ሴት ጋር ግን ቢሆን ሁሉንም ለመፈፀም ያስችለዋል፡፡
3.የአፍ ሽታ ይኖረዋል፡፡ ይህም ሚስት እንድትሸሸው ያደርገዋል፡፡
4.ሀይለኛ የራስ ምታት አለው፡፡ ይህ ራስ ምታት ጁምአና ሰኞ ላይ ይብሳሉ፡፡
5.ሰውን ማመን አይችልም ፡፡ ሁሉንም እኔ አውቃለሁ ይላል፡፡ ይህም ከማንም ጋር ህይወቱን በቀላሉ እንዲገፋ አያደርገውም፡፡
6.ሚስትን መጠራጠሩ አይቀርም ሚስትም እንዲጠራጠራት የሚያደርገው ሲህሩ ነው፡፡
7.እጅግ በሚገርም መልኩ 78 በመቶዎቹ ሴቶቻቸው ሚስቶቻቸው ልጅ ይወልዳሉ ነገር ግን ልጆቹ የነርሱ አይደሉም የባሎቻቸው አይደሉም ሌላ ጋር ይወሰልታሉ፡፡ ይህም ከባልየው ግፊትና ቀናተኝነት ባህሪ ለመላቀቅ የሚመርጡ ናቸው፡፡
8.የእስፐርም ሴሉ ሙሉ ለሙሉ ውሀ ይሆናል ምንም አይነት እስፐርም ሴል የለውም፡፡
ለዚህም ህክምና ምልክት የሚታይቦት ከሆነ
1.ሲተኙ በሱና መተኛት
2.ከእንቅልፎ ሲባንኑ ዱአ አድርገው መተኛት ለበለጠ መረጃ ከህክምና ጣቢያችን መጠው መናገር ይችላሉ

25/06/2020
25/06/2020

Address

Bahir Dar

Telephone

+251918769590

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Beder Traditional Medicine Center-በድር ባህላዊ የህክምና ማዕከል posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Practice

Send a message to Beder Traditional Medicine Center-በድር ባህላዊ የህክምና ማዕከል:

Share