Debre Tabor Comprehensive Specialized Hospital

Debre Tabor Comprehensive Specialized Hospital Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Debre Tabor Comprehensive Specialized Hospital, Hospital, Debre Tabor.

በተቋቋመ በአጭር ጊዜ የአካባቢውንና የተቋሙን       ስም እየገነባ ያለው የደብረታቦር ዮኒቨርሲቲ የእግር ኳስ ቡድን 3ኛ በመውጣት የነሀስ መዳሊያ ተሸላሚና    ወደ የአማራ ሊጊ ገብቷል።
13/07/2023

በተቋቋመ በአጭር ጊዜ የአካባቢውንና የተቋሙን

ስም እየገነባ ያለው የደብረታቦር ዮኒቨርሲቲ የእግር ኳስ ቡድን 3ኛ በመውጣት የነሀስ መዳሊያ ተሸላሚና
ወደ የአማራ ሊጊ ገብቷል።

07/07/2023


==========
ከሀምሌ 19- 23/2015 ዓ.ም ጥበበ ግዮን ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ከእስራኤል ሐገር ከሚመጡ ከፍተኛ የቀዶ ህክምና ባለሞያዎች ጋር በመተባበር በዘመናዊ መሳሪያ የታገዘ ከፍተኛ የቀዶ ህክምና (Laparoscopic Surgery) አገልግሎት ይሰጣል::

አገልግሎት የሚሰጥባቸው ዘርፎች
------------------------------------------

1. የሐሞት ጠጠር ቀዶ ህክምና (Laparascopic cholecystectomy)

2. የጉረሮ ካንሰር እና ሌሎች የጉረሮ ህመሞች ቀዶ ህክምና (Esophageal disease and other related pathologies surgery)

3. የጨጓራ ካንሰር እና ሌሎች ተያያዥ የጤና ችግሮች ቀዶ ህክምና (Gastric cancer and other gastric pathologies surgery)

4. የቆሽት፣ የሐሞት ቱቦ እና የጣፊያ ቀዶ ህክምና (Hepatopancreaticobiliary surgery) እና

5. የአንጀት ካንሰር እና ተያያዥ የጤና ችግሮች ቀዶ ህክምና (Colorectal and other related diseases surgery) ናቸው::

ስለሆነም ችግሩ ያለባችሁ ህሙማን ወደ ሆስፒታሉ በመምጣት የአግልግሎቱ ተጠቃሚ ትሆኑ ዘንድ ጥሪያችንን እንሳተላልፋለን::

የጋራ ጥረት ለማኅበረሰብ ጤንነት!

ጥበበ ግዮን ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል

ባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ
to to !!!

04/07/2023

የብቃት ምዘና ፈተና ለምትወስዱ ጤና ባለሙያዎች በሙሉ
____________

የጤና ሚኒስቴር ከከፍተኛ የትምህርት ተቋማት በሜዲስን፤ ነርሲንግ፤ ጤና መኮንን፤ አንስቴዥያ፤ ፋርማሲ፤ ሜዲካል ላቦራቶሪ፤ ሚድዋይፈሪ፤ ዴንታል ሜዲስን፤ ሜዲካል ራዲዮሎጂ፤ ኢንቫይሮመንታል ሄልዝ፤ ፔዲያትሪክ ኤንድ ቻይልድ ሄልዝ፤ ሳይካትሪ ነርሲንግ፤ እና ኢመርጀንሲ ኤንድ ክሪቲካል ኬር ነርሲንግ ሙያዎች በመጀመሪያ ዲግሪ ተመርቀው የብቃት ምዘና ፈተና ለመውሰድ በመጠባበቅ ላይ ለሚገኙ የጤና ባለሙያዎች ፈተናው ሰኔ 30/2015 ዓ.ም ትምህርት ሚኒስቴር ከሚሰጠው የመውጫ ፈተና (Exit exam) ጋር በማቀናጀት የሚሰጥ መሆኑን እየገለፅን:-

1. የፈተናው አሰጣጥ ሂደት በኮምፒውተር ይሆናል።

2. የፈተናው መርሃግብር

- በ30/10/2015 ዓ.ም Nursing, Pharmacy, Public Health, Anesthesia, Medical Radiology Technology and Environmental Health, Medical Laboratory Science, Midwifery, Medicine, Dental Medicine, Pediatric and Child Health Nursing, Psychiatric Nursing and Emergency and Critical Care Nursing

3. እያንዳንዱ ተፈታኝ ከሚፈተንበት ቀን አንድ ቀን ቀደም ብሎ ማለትም ሰኔ 29/2015 ዓ.ም ከቀኑ በ 8፡00 ሰዓት በመፈተኛ ጣቢያ በመገኘት የቅድመ ፈተና መለማመጃ ጥያቄዎችን መስራትና፤ የመፈተኛ ክፍሉን መለየት ይኖርበታል።

4. የቅድመ ፈተና መለማመጃ ጥያቄዎችን ለመስራት፤ ወደ ፈተና የሚያስገባውን Username and Password እና የመፈተኛ ጣቢያ ለማወቅ የመረጣችሁብት ዩኒቨርስቲ ዋና ግቢ ከፈተናው አንድ ቀን በፊት ማለትም ሰኔ 29/2015 ዓ.ም በመገኘት ከጣቢያ አስተባባሪዎች ማግኘት ትችላላችሁ።

5. በፈተናው ዕለት ማንነታችሁን የሚገልጽ መታወቂያ (የቀበሌ መታወቂያ፣ ፓስፖርት፣ መንጃ ፍቃድ ወይም ሌላ በግልጽ የሚታይ ህጋዊ መታወቂያ) ይዛችሁ መገኘት ይኖርባችኋል፡፡

6. ከላይ ከተጠቀሱት ነገሮች ውጪ ምንም አይነት የኤሌክትሮኒክስ መሳሪያ (ስልክ፣ የእጅ ሰዓት፣ መነጽር (የተረጋገጠ የዕይታ ችግር ከሌለ በስተቀር)፣ ቦርሳ እና ሌሎች እቃዎች፣ ምንም አይነት ማጣቀሻዎች እንዲሁም ባዶ ወረቀቶች፣ ምግብ ወይም መጠጥ (የተረጋገጠ የጤና ችግር ከሌለ በስተቀር) ይዞ መግባት አይፈቀድም፡፡

7. ፈተናውን በድጋሚ ለምትወስዱ ተመዛኞች ወደ ፈተና ጣቢያ ስትመጡ ሲስተሙ የሚሰጠውን የፈተና መለያ ቁጥር (Registration No) QR code የያዘ ወረቀት /ስሊፕ/ print አድርጋችሁ መምጣት ይኖርባችኋል።

ተመዛኞች ስማቸው ከተጠቀሰበት ተቋም ውጪ በፍጹም ፈተናውን መውሰድ የማትችሉ መሆኑን እያሳሰብን ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር 0118275936/952 መደወል ይቻላል፡፡

17/06/2023
16/06/2023
የደ/ታ አጠቃላይ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል  #አራተኛው ሩብ አመት የሆስፒታሎች ድጋፋዊ ጉብኝት በመካነ እየሱስ የመጀመሪያ ሆስፒታል የተደረገ SSVከሶስቱ ሩብ አመት ጥሩ የሚባልና የተሳካ ነበር።...
13/06/2023

የደ/ታ አጠቃላይ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል #
አራተኛው ሩብ አመት የሆስፒታሎች ድጋፋዊ ጉብኝት
በመካነ እየሱስ የመጀመሪያ ሆስፒታል የተደረገ SSV
ከሶስቱ ሩብ አመት ጥሩ የሚባልና የተሳካ ነበር።አስፈላጊው
ትብብር ላደረጋችሁሉን እስታፍ ከልብ እናመሰግናለን።

Address

Debre Tabor

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Debre Tabor Comprehensive Specialized Hospital posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share

Share on Facebook Share on Twitter Share on LinkedIn
Share on Pinterest Share on Reddit Share via Email
Share on WhatsApp Share on Instagram Share on Telegram

Category