06/01/2024
ሪህ (Gout Arthritis)
የሪህ ሕመም የሚከሰተዉ ዩሪክ አሲድ የተባለው ኬሚካል በአጥንት መገጣጠሚያዎች ውስጥ በሚከማችበት ወቅት ነው፡፡ ይህ ዩሪክ አሲድ የተባለው ኬሚካል የሚገኘውፕሮቲንን በዉስጣቸዉ ከያዙ ምግቦች ነው፡፡ የሪህ ችግር
አንድ ጊዜ ከጀመረ በኋላ የመከላከያ ዕርምጃዎችን ካልወሰድን የመመላለስ ባህርይም አለዉ፡፡ የአጥንት መገጣጠሚያዎች በተለይም በእግራችን የአውራ ጣት፣ በቁርጭምጭሚት፣በጉልበት፣በእጃችን
የክንድ እና የእጅ መገጣጠሚያዎች ላይ ተከማችቶ ይገኛል፡፡
የሪህ ህመም ስሜት ቀስቃሽ ሁኔታዎች
• ዉስጣዊ የሆኑ ህመሞች( የደም ግፊት መጨመር ፣ የስኳር በሽታ፣ ውፍረት ፣ዘላቂ የኩላሊት በሽታ)
• አልኮል መጠጦችን ማዘዉተር
• ፕሮቲን የበዛባቸው የምግብ ዓይነቶችን መመገብ (ስጋ፣ አሳ የመሳሰሉት)
• የሰዉነት ቁስለት
• ድካም
• ጭንቀት
• በሃኪም የታዘዘን የሪህ መድኃኒት ማቆም ናቸዉ፡፡
✔ የሪህ ህመም ምልክቶች ምንድን ናቸዉ፡፡
• ከአንድ ወይንም ከዛ በላይ በሆኑ መገጣጠሚያዎች ላይ የሚኖር ኃይለኛ የሕመም ስሜት፡፡
• የመገጣጠሚዎች ማበጥ፣ መቅላት እና የሙቀት መጠን መጨመር
• ትኩሳት መኖር
• ብርድ ብርድ ማለት ናቸዉ
ሪህ ተደጋግሞ እንዳይመጣ ምን ማድረግ ይገባል
• ፕሮቲን ያላቸውን ምግቦች በተለይም ቀይ የበሬ
ሥጋ፣አሳ፣እንቁላል፣የመሳሰሉት ምግቦች መቀነስ ወይንም ለጊዜው ማስወገድ፣
• ውሃ በብዛት መውሰድ፣
• የአልኮል መጠጦችን አለመጠጣት
የሪህ ህክምና ምንድነው?
1. የህመም ማስታገሻ መውሰድ (Anti pain እንደ diclofenac, ibuprofen, meloxicam and indomethacin
2. የኩላሊት ችግር ካለባቸው steroid መውሰድ
3. አዲስ ህመም ከሆነ colichine
4. የዩሪክ አሲድ መቀነሻ alloprinol
ከሁለት እስከ አራት ያሉት በሐኪም ትዕዛዝ የሚሰጡ ናቸው
በቤት ውስጥ ማድረግ ያለብን ነገሮች
1 .ከላይ ያየናቸውን ምግቦች አለመመገብ
2. እንቅስቃሴ ማድረግ
ካልታከሙት ምን ያስከትላል ?
1. ተደጋጋሚ የሚከሰት ሪህ
2. ከጊዜው በላይ የሚቆይ ሪህ
3. የሽንት ቧንቧ እና የኩላሊት ጠጠር
4. የኩላሊት ስራ ማቆም
5. ዘላቂ የሆነ የመገጣጠሚያ ህመም
በሽታው በምን ይታወቃል ?
1. በበሽታው ምልክቶችፕ
2. በደም ውስጥ ባለ የዩሪክ አሲድ መጠን
3. በራጅ ምርመራ
4. የመገጣጠሚያ አልትራሳውንድ
ይህ የሪህ በሽታ በሀገራችን በስፋት የሚገኝ ሲሆን በወንዶች ላይ በስፋት ይገኛል በጥናት ደረጃ በደንብ የተጠና አይደለም። ብዙዎች የሰውነታችን የመከላከል ህዋሶች በራሳቸው ህዋስ ላይ በሚፈጥሩት ችግር ከሚከሰተው ከሪማቶይድ (rheumatoid arthritis) ጋር ያመሳስሉታል ግን ምክንያታቸውም የበሽታ አፈጣጠር ሂደታቸውም ልዩ ነው ስለሪማቶይድ በሌላ ጽሑፍ እንመለሳለን።