13/03/2024
⚡️ሰላም ሁላችሁም! በምዕራቡ ዓለም ተወዳጅነት እያገኘ ያለ የቻይና ባህላዊ ሕክምና!
📒 ስለ “Acupuncture” (አኩፓንክቸር) እንነጋገር!
🗒አኩፓንክቸር በሰውነትዎ (በቆዳዎ) ላይ የተወሰኑ ነጥቦችን ማነቃቃትን ያካትታል፣ ብዙውን ጊዜ ቀጭን መርፌዎችን በማስገባት ማለት ነው
📒 አኩፓንክቸር በመርፈዎቹ ላይ የኃይል ግፊትን፣ ጨረርን ወይም ዝቅተኛ የኤሌክትሪክ ፍሰትን በመጠቀም ሊከናወን ይችላል
📛 በአኩፓንክቸር ላይ የሚደረግ ጥናት እስካሁን በታየው በጣም አስቸጋሪ ነው፣ ነገር ግን የዓለም ጤና ድርጅት (WHO) ከታች ለተዘረዘሩት ሁኔታዎች መጠቀም እንደሚቻል ይመክራል (አንዳንዶቹ በጠንካራ የጥናት ውጤቶች የተደገፉ ሲሆኑ ሌሎቹ ደግሞ ተጨማሪ ጥናቶች የሚያስፈልጉአቸው ናቸው)
👉የካንሰር ህመም ስሜቶችና ምልክቶች
👉ድብርት
👉በተለያየ ምክንያት የሚመጣን የህመም ስቃይ ስሜት
👉የወር አበባ ጊዜ ከባድ የህመም ስሜት
👉ራስ ምታት
👉ከቀዶ ጥገና በሁአላ ለሚከሰት የህመም ስሜት
🦺 አኩፓንክቸር በአጠቃላይ ደህንነቱ የተጠበቀ ቢሆንም፣ የሰለጠነ ባለሙያ ማግኘት በጣም አስፈላጊ ነው።
🤔የጎንዮሽ ጉዳቶች እንደ ራስ ምታት ወይም የማዞር ስሜት አይነት ያሉትን ያካትታል፣ አልፎ አልፎ ራስን መሳት ሊከሰት ቢችልም በአብዛኛው ቀላል ናቸው
📨 አኩፓንቸር የጤና ጠቀሜታዎች ያሉት አስደናቂ ልምምድ ነው፣ ነገር ግን በጥንቃቄ እና በማስተዋል መቅረብ በጣም አስፈላጊ ነው።
⁉️ አኩፓንክቸር ሞክረው ያውቃሉ? ተሞክሮዎን ያጋሩን!
🌺💡 ጤና ‘ማ ይኑርዎት! https://ln.run/m6-5j
ስለጤናዎ ምን ማወቅ ይፈልጋሉ? ዶክተርዎን ይጠይቁ 👉 https://ln.run/m6-5j
እዚህ ይከታተሉን 👉 https://ln.run/pRw3d