Dilchora Hospital Dire Dawa

Dilchora Hospital Dire Dawa Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Dilchora Hospital Dire Dawa, Hospital, dire dawa, Dire Dawa.

 DilChora Hospital is a medical institution dedicated to providing quality patient care with
unrelenting attention to clinical excellence, patient safety and an unparalleled passion and
commitment to assure the very best healthcare for those we serve

ለድልጮራ ሆስፒታል ተገልጋዬች እንኳን ደስ አላችሁ።
13/02/2026

ለድልጮራ ሆስፒታል ተገልጋዬች እንኳን ደስ አላችሁ።

የድልጮራ ሆስፒታል አገልግሎቱን ይበልጥ ለማዘመን የሚያስችሉ ዘመናዊ የህክምና መሳሪያዎችን በልገሳ ተረከበየድልጮራ ሆስፒታል በአውስትራሊያ ከሚገኘው የፉትስክሬይ ሮታሪ ክለብ እና 'ሮታሪ ዶኔሽ...
09/02/2026

የድልጮራ ሆስፒታል አገልግሎቱን ይበልጥ ለማዘመን የሚያስችሉ ዘመናዊ የህክምና መሳሪያዎችን በልገሳ ተረከበ

የድልጮራ ሆስፒታል በአውስትራሊያ ከሚገኘው የፉትስክሬይ ሮታሪ ክለብ እና 'ሮታሪ ዶኔሽንስ ኢን ካይንድ' የተገኙ እጅግ ዘመናዊ የህክምና መሳሪያዎችን በዛሬው እለት በይፋ ተረክቧል።
​በዚህ ደማቅ የርክክብ ስነ-ስርዓት ላይ የድሬዳዋ አስተዳደር ከንቲባ ክቡር አቶ ከድር ጁሃር፣ ምክትል ከንቲባ ክቡር አቶ ሀርቢ ቡህ፣ የድሬዳዋ ጤና ቢሮ ኃላፊ ዶክተር ጽጌሬዳ ክፍሌ፣ የሆስፒታሉ ስራ አስኪያጅ ወይዘሮ ሙና ኢብራሂም እና ሌሎች ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል።
​የድሬዳዋ አስተዳደር ከንቲባ ክቡር አቶ ከድር ጁሃር ባደረጉት ንግግር፤ ለጋሾችን አመስግነው እንዲህ ያሉ ዓለም አቀፋዊ አጋርነቶች ለወደፊቱም ተጠናክረው ሊቀጥሉ እንደሚገባ እና የድሬዳዋ አስተዳደር መሰል የልማት አጋርነቶች እንዲስፋፉና ለጋሾችም ምቹ ሁኔታ እንዲፈጠርላቸው የሚቻለውን ሁሉ ለማመቻቸት ዝግጁነታቸውን ገልጸዋል።
​የድሬዳዋ ጤና ቢሮ ኃላፊ ዶክተር ጽጌሬዳ ክፍሌ በበኩላቸው፤ እነዚህ መሳሪያዎች በሆስፒታሉ የሚሰጠውን የህክምና አገልግሎት ጥራት ለማሳደግና የማህበረሰቡን የጤና ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ያላቸውን ፋይዳ አብራርተዋል።
​የሆስፒታሉ ዋና ስራ አስኪያጅ ወይዘሮ ሙና ኢብራሂም ባስተላለፉት መልዕክት፤ የተገኙት መሳሪያዎች ሆስፒታሉ ያለውን የአገልግሎት አድማስ ለማስፋት ትልቅ አቅም እንደሚፈጥሩ ገልጸዋል።ከዚህ አክለውም "እነዚህን እጅግ ጠቃሚ የሆኑ የህክምና መሳሪያዎች ለታለመላቸው አላማ ብቻ በማዋል የማህበረሰባችንን ጤና ለመጠበቅና ህይወት ለመታደግ ቃል እንገባለን" ሲሉ ሆስፒታሉ መሳሪያዎቹን በአግባቡ የመጠቀምና የመንከባከብ ኃላፊነቱን እንደሚወጣ አረጋግጠዋል።
​ይህ ግዙፍ ድጋፍ እጃችን እንዲደርስ በግንባር ቀደምትነት ለተሳተፉት ለአቶ ጃማ ፋራህ እና ለአቶ ዳዊት፣ ለአፍሪካ ቀንድ የህክምና መሳሪያዎችና ተንቀሳቃሽነት ፋውንዴሽን እንዲሁም በአውስትራሊያ ለሚገኘው የድሬዳዋ ከተማ እርዳታ እና ድጋፍ ማህበር በስነ-ስርዓቱ ላይ ላቅ ያለ እውቅና ተሰጥቷል።
​ልገሳው በእናቶችና ህጻናት ጤና እንዲሁም በተለያዩ የህክምና ዘርፎች ላይ የሚታየውን አገልግሎት ወደ ላቀ ደረጃ እንደሚያሸጋግር ተገልጾ፤ የርክክብ መርሃ-ግብሩ ተጠናቋል።

06/02/2026
Thanks a lot to all of our partners
29/01/2026

Thanks a lot to all of our partners

👉👉ድልጮራ ሆስፒታል ጥር 16/2018የፌዴራል ተቋማት ብልፅግና ፓርቲ የኢኮኖሚ ክላስተር ወጣቶች ክንፍ "የወጣቶች በጎ እይታ ለታላቋ ኢትዮጵያ "በሚል መሪ ሀሳብ በአስተዳደሩ የበጎ ፍቃድ አገ...
25/01/2026

👉👉ድልጮራ ሆስፒታል ጥር 16/2018

የፌዴራል ተቋማት ብልፅግና ፓርቲ የኢኮኖሚ ክላስተር ወጣቶች ክንፍ "የወጣቶች በጎ እይታ ለታላቋ ኢትዮጵያ "በሚል መሪ ሀሳብ በአስተዳደሩ የበጎ ፍቃድ አገልግሎቶችን እና አቅመ ደካሞችን ለመደገፍ እና የወጣቶችን አብሮነት ፣ወንድማማች እህትማማችነት እሴትን ለማጎልበት እንዲያስችል ታስቦ በዛሬውም እለት በጎነት በሆስፒታል በሚል መርህ በድልጮራ ሆስፒታል እና በኢትዪፈረንሳይ ትራውማ ሴንተር ለሚገኙ ታካሚዎች የተለያዮ የቁሳቁስ ድጋፍ ኣድርገዋል!!
ለዚህ ተግባር በሆስፒታሉ ስም እናመሰግናለን።🙏🙏🙏

የድልጮራ ሆስፒታል የአመራር ቦርድ የ2018 በጀት ዓመት የ6 ወራት የሥራ አፈጻጸም ግምገማ በዛሬው ዕለት 13/05/18 አካሂዷል። ግምገማው ሆስፒታሉ ለማህበረሰቡ የሚሰጠውን የጤና አገልግሎት...
21/01/2026

የድልጮራ ሆስፒታል የአመራር ቦርድ የ2018 በጀት ዓመት የ6 ወራት የሥራ አፈጻጸም ግምገማ በዛሬው ዕለት 13/05/18 አካሂዷል። ግምገማው ሆስፒታሉ ለማህበረሰቡ የሚሰጠውን የጤና አገልግሎት ጥራትና ተደራሽነት ይበልጥ ለማሳደግ ያለመ ነው።
በሪፖርቱ ከቀረቡ ዋና ዋና አሃዞች ባለፉት ስድስት ወራት በሆስፒታሉ
በተመላላሽ ታካሚዎች ክፍል (OPD)፦ 134,535 ለሚሆኑ ዜጎች አገልግሎት መስጠት ተችሏል።
በተኝቶ ታካሚዎች ክፍል (IPD)፦ 6640 ታካሚዎች ክትትልና ህክምና አግኝተዋል።
በድንገተኛ አደጋ ህክምና ክፍል (Emergency)፦ 9973 ለሚሆኑ ወገኖቻችን አስቸኳይ የህይወት አድን አገልግሎት ተሰጥቷል።
የሆስፒታሉ የአመራር ቦርድ በሪፖርቱ በቀረቡት ዝርዝር ተግባራት ላይ ሰፊ ውይይት ካደረገ በኋላ፣ ጥሩ አፈጻጸም የታየባቸውና ውጤታማ የሆኑ ስራዎች ይበልጥ ተጠናክረው እንዲቀጥሉ አቅጣጫ አስቀምጧል። በተለይም በሆስፒታሉ መጋዘን ክፍሎች ውስጥ ተግባራዊ የተደረገውን የካይዘን (Kaizen) አሰራር በአካል ተገኝቶ በመመልከት፣ የስራ ሂደቱን በማሳለጥ ረገድ ያለውን ፋይዳ ገምግሟል።
ከዚሁ ጎን ለጎን፣ ቦርዱ ክፍተት የታየባቸውን የስራ ዘርፎች በመለየት በቀጣይ መስተካከል በሚገባቸው ጉዳዮች ላይ አቅጣጫ አስቀምጧል። በተለይም የሆስፒታሉን ግቢ ለታካሚዎች ፅዱ፣ አረንጓዴ እና ምቹ የማድረግ ስራ በልዩ ትኩረት እንዲከናወን አስታውቋል።
የአገልግሎት አሰጣጥ ፍጥነትንና የደንበኞች እርካታን ይበልጥ ማሳደግ የሚቻልባቸውን መንገዶች በማሳለጥ የድልጮራ ሆስፒታልን የላቀ የህክምና ማዕከል ለማድረግ በቅንጅት እንደሚሰራ አረጋግጠዋል።

11/01/2026
08/01/2026
የሰንደቅ ዓላማ ቀን አከባበር በድልጮራ ሆስፒታል
13/10/2025

የሰንደቅ ዓላማ ቀን አከባበር በድልጮራ ሆስፒታል

Address

Dire Dawa
Dire Dawa

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Dilchora Hospital Dire Dawa posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Practice

Send a message to Dilchora Hospital Dire Dawa:

Share

Share on Facebook Share on Twitter Share on LinkedIn
Share on Pinterest Share on Reddit Share via Email
Share on WhatsApp Share on Instagram Share on Telegram

Category