18/08/2024
በሽታ መከላከል እና ቅድመ ምርመራ
■ ጥራቱን የጠበቀ የጤና እንክብካቤ ሁለት መሰረታዊ ነገሮች ኣሉት፡፡ እነሱም፤
1. ኣሁን ለታመመ በኣግባቡ ማከም እና
2. ለወደፊት ለሚመጣ የጤና መዛባት የሚቀንስ ኣግባብ ያለው ቅድመ መከላከል ናቸው፡፡
》 ቅድመ መከላከሉ በጣም ጠቃሚ የሆነ ልምድ ሲሆን ኣጠቃላይ የጤናችን ሁኔታ በጣም ያሻሽላል፡፡
》 በኣጠቃላይ ኣንድ ሰው ዕድሜው 49 ዓመት እና ከዛ በታች ከሆነ እና የቆየ በሽታ ከሌለው በየ 3 ዓመቱ፤ 50 ዓመት እና ከዛ በላይ ከሆነ ደግሞ በየዓመቱ የጤና ምርመራ እንዲያደርግ ይመከራል፡፡
■ የልብ እና ደም ሥር በሽታ መከላከል
》 ዕድሜያቸው 20 ዓመት እና ከዛ በላይ ለሆኑ ታካሚዎች በየ 3 ወይም 5 ዓመት ምን ያክል ለልብ እና ደም ሥር በሽታ ተጋላጭ እንደሆኑ በስሌት መሰራት ኣለበት፡፡
》 ለልብ እና ደም ሥር በሽታ የሚያጋልጡ ግን ደግሞ ልንከላከላቸው የምንችል ዋና ዋናዎቹ የሚከተሉት ናቸው፡፡
》 ኣመጋገብ
》 ሲጋራ ማጨስ
》 ደም ግፊት
》 ኮሌስትርል
》 ውፍረት
》 የኣካል እንቅስቃሴ እና
》 ስኳር በሽታ ናቸው፡፡
■ ደም ግፊት
》 ኣንድ ሰው 18 ዓመት ሲሞላው ደም ግፊት መለካት መጀመር ኣለበት፡፡
》 40 ዓመት እና ከዛ በላይ ከሆነ በየዐመት፤ 18 እስከ 39 ዓመቱ ከሆነ ደግሞ በየ 3 ወይም 5 ዓመት መለካት ኣለበት፡፡
■ ኮሌስትሮል
》 ኣንድ ሰው ከ 17 እስከ 21 ዓመት ጀምሮ ቢያንስ ኣንድ ጊዜ ኮሌስትሮል መለካት ኣለበት፡፡
》 ኮሌስትሮሉ ጥሩ ሆኖ ግን ደግሞ ተጋላጭ ከሆነ ማለት ግፊት፤ ስኳር፤ የሚያጨስ ወይም ደግሞ በቤተሰብ ካለው ኮሌስትሮሉ በድጋሚ ለወንዶች 25 ዓመት ላይ ለሴቶች ደግሞ 35 ዓመት ላይ መሰራት መጀመር ኣለበት፡፡
》 ተጋላጭ ካልሆኑ ግን ለወንዶች 35 ዓመት ላይ ለሴቶች ደግሞ 45 ዓመት ላይ መጀመር ኣለበት፡፡
》 ኮሌስትሮሉ ምንም ማስተካከያ የማያስፈልግበት ደረጃ ከሆነ 65 ዓመት እስኪሞላው መየ 5 ዓመት መመርመር ኣለበት፡፡
ውፍረት
》 ሁሉም ታካሚዎች Body Mass Index (BMI) መለካት እና ጤናማ ክብደት እንዲኖራቸው ምክር መሰጠት ኣለባቸው፡፡
የኣካል ብቃት እንቅስቃሴ
》 ሁሉም ታካሚዎች በሳምንት ቢያንስ ለ150 ደቂቃ ያክል የኣካል ብቃት እንቅስቃሴ እንዲኖራቸው ምክር ማግኘት መቻል ኣለባቸው፡፡
■ ስኳር
》 ደም ግፊት ወይም ኮሌስትሮል እና ከ 35 እስከ 70 ዓመት BMI 25 kg/m2 ከሆነ የስኳር ምርመራ እንዲያደርግ ይመከራል፡፡
■ ካንሰር መከላከል
》 ኣጠቃላይ ስለ ካንሰር መከላከል የሚሰጡ ምክሮች የሚከተሉ ናቸው፡፡
》 ሲጋራ ማጨስ ማስወገድ
》 የኣካል ብቃት እንቅስቃሴ ማደረግ
》 ጤናማ ክብደት እንዲኖረን ማድረግ
》 ፍራፍሬ፤ ኣትክልት፣ እና ጥራጥሬ ማዘውተር እና ትንሽ ቅባት ያለው ምግብ መብላት እና
》 ኣልኮል መጠጥ መቀነስ
■ የካንሰር ቅድመ ምርመራ
■ የጡት ካንሰር
》 የጡት ካንሰር ቅድመ ምርመራ ከ 40 ዓመት ጀምሮ ማሞግራፊ (Mammography) በተባለ የጡት ራጅ በየ 1 ወይም 2 ዓመት እንዲደረግ ይመከራል፡፡
■ የማህፀን በር ካንሰር
》 የማህፀን በር ካንሰር ቅድመ ምርመራ ለሁሉም ከ 21 እስከ 65 ዓመት ሴቶች Pap test በሚባል ምርመራ በየ 3 ዓመት እንዲደረግ ይመከራል፡፡
■ የትልቁ እንጀት ካንሰር
》 የትልቁ ኣንጀት ካንሰር ቅድመ ምርመራ 45 ዓመት እና ከዛ በላይ ለሆኑ ሰዎች Colonoscopy በሚባል መሳርያ እንዲደረግ ይመከራል፡፡
■ የሳንባ ካንሰር
》 ለሳንባ ካንሰር ተጋላጭ የሆኑ ሰዎች በየዓመቱ ትንሽ ጨረር ባለው CT Scan ምርመራ እንዲያደርጉ ይመከራል፡፡
■ የኣባላዘር በሽታ መከላከል
■ ሄፓታይቲስ ቢ
》 ኣንድ ሰው 18 ዓመት እና ከዛ በላይ ከሆነው ቢያንስ ኣንድ ጊዜ ሄፓታይቲስ ቢ ምርመራ እንዲያደርግ ይመከራል
ሄፓታይቲስ ሲ
》 ከ 18 እስከ 79 ዓመት ያሉ ሰዎች ቢያንስ ኣንድ ጊዜ ሄፓታይቲስ ሲ ምርመራ ማድረግ ኣለባቸው፡፡
■ ኤች. ኣይ. ቪ እንፌክሽን
》 ኣንድ ሰው 75 ዓመት እስኪሞላው በየጊዜው የኤች. ኣይ. ቪ ምርመራ ማድረግ ኣለበት፡፡
■ ቂጥኝ (Syphilis)
》 ተጋላጭ የሆነ ሰው የቂጥኝ ምርመራ ማድረግ ኣለበት፡፡
ዶ/ር ተስፋይ ተ/ሃይማኖት ኣሰፋ
የውስጥ ደዌ ስፔሻሊስት