01/08/2023
ታላቅ አማራዊ ንቅናቄ ጥሪ፤ ለመላው አማራ ሕዝብ!
የአማራ ሕዝብ ላለፉት አመታት በከፍተኛ መሳደድ፣ መፈናቀል እና ጅምላ ግድያ ላይ ይገኛል። ነገር ግን ነብልባሉ የአማራ ፋኖ ባደረገው አስደናቂ ተጋድሎ የአማራ ሕዝብ አንገቱን ቀና አድርጎ መሄድ ጀምሯል፤ በልበ ሙሉነት እኔ አማራ ነኝ! እኔ ፋኖ ነኝ ማለት ጀምሯል። የአማራ ሕዝብ ተጋድሎም ተጠናክሮ ቀጥሏል። ይቀጥላል‼️
እየተዋደቀ ለሚገኘው የአማራ ሕዝብ የቁርጥ ቀን ልጅ ፋኖ እኛ ምን አድርገናል ብላችሁ አስባችሁ ታውቃላችሁ?
የአማራ ወጣቶች ማሕበር ለመላው የአማራ ሕዝብ ከሊቅ እስከ ደቂቅ የሚከተለውን እንድናደርግ የከበረ ጥሪውን ያስተላልፋል፦
በመጪው ዕረቡ ዕለት በተመሳሳይ ሰዓት (ከቀኑ 10:00 ሰዓት ) በቤታችን፣ በስራ ቦታችን፣ በመዝናኛ ቦታዎች ፣ በመንገድ ላይ ወዘተ ሁላችን በአንድ ላይ በመነሳት "እኔ ፋኖ ነኝ!!" የሚል ታላቅ ህዝባዊ ንቅናቄ ተዘጋጅቷል።
አፈፃፃሙ ሁሉም በእያለበት በተናጠል ሆነ በጋራ በመሆን እጃችን ቸብ! ቸብ! በማድረግ በጭብጨባ እኔ ፋኖ ነኝ ማለት ይኼንን በተንቀሳቃሽ ምስል በማስቀረት በማህበራ ሚዲያ ማለትም በፌስቡክ፣ በቴሌግራም፣ ቲክቶክ፣ ዩቱዩብ ወዘተ በማጋራት እንዲሁም ለተለያዩ የአማራ የሚዲያ ተቋማት እና ባለሞያዎች ማጋራት ነው። በዚህ ታላቅ አማራዊ ንቅናቄ ሁሉም እንዲሳፍ ጥሪያችን እናስተላልፋለን።
ይህ ወሳኝ ተግባር የአማራ ፋኖ እየከፈለ ከሚገኘው የደም መስዕዋትነት አንፃር እጅግ ቀላሉ ነው። ስለሆነም ለዚህ ቀላል ነገር ግን ታላቅ አማራዊ ንቅናቄ ሁላችንም ከዛሬ ጀምሮ እንድንዘጋጅ የአማራ ወጣቶች ማህበር ለተከበረው የአማራ ህዝብ ጥሪያችንን እናስተላልፋለን ።
በመጨረሻም "ፋኖነት" ከተሰኘው የጌትነት ይርሳው ድንቅ መፅሃፍ የተገኘውን ስንኝ እየጋበዝን ሁሉም ለተደረገው ጥሪ ተግባራዊነት እንበርታ እንላለን።
ይቅርብሽ ነሐሴ በጭቃ እንዳትወደቂ
እንዳትመጭ ሰኔ ጥሩ ቀን ዕወቂ
ፋኖ ከጠራሽ ግን መስከረም ዝለቂ።
ፋኖ ገና ገና ፋኖ ገና ገና
የነሐሴው መብረቅ የሐምሌው ደመና።
ቋንቋ ይለመዳል ድሮም መግባቢያ ነው
ታሪክ ሚወረስ ግን ከአያት ቅድመ አያት ነው።
አንገት ደፍቶ መኖር ከመሰለው ሞኝ
እኔስ የጀግና ዘር የነፍጠኛ ነኝ።
እኔስ በውሻዎች ስፈራ ስፈራ
እኔስ በቀበሮ ስፈራ ስፈራ
ነብሩ ደረሰልኝ አቤት የአምላክ ሥራ።
ድል ለአማራ ፋኖ ‼️
ድል ለአማራ ህዝብ‼️
የአማራ ወጣቶች ማህበር