OBGYN

OBGYN በማህፀንና ፅንስ ላይ ልዩ ልዩ መረጃዎችን ይሰጣል

05/09/2022

From next week......

10/10/2020

የማህፀን ጫፍ ካንስር በኢትዮጲያ እናቶችን በመግደል ከዋናዎቹ ውስጥ አንዱ ነው።
በሀገራችን ውስጥ በየዓመቱ ሆስፒታል ለህክምና መጥተው ሲመረመሩ ከ7000 በላይ ሴቶች የማህፀን ጫፍ ካንሰር ተጋልጠው ተገኝተዋል፡፡ ከነኚሁ ውስጥ ከ6000 በላይ የሚሆኑት በዛው ዓመት ይሞታሉ። ይህ ስሌት የሚያመለክተው ህመም ኖሯቸው ለመታከም ወደ ህክምና ማእከል የመጡትን ሴቶች ብቻ ነው።
የማህፀን ጫፍ ካንስር ምልክቶች
-በግንኙነት ጊዜ ወይም የወር አበባ ማየት ካቆሙ በኃላ በማህፀን ደም መፍሰስ
-ያልተለመደ የማህፀን ፈሳሽ
-ከተሰራጨም የታችኛው ክፍል የወገብ ወይም የሆድ ህመም
ነገር ግን የማህፀን ጫፍ ካንስር ምንም አይነት ምልክት ላይኖረው ይችላል ወይም ምልክት የሚያሳየው ከተሰራጨ በኃላ ሊሆን ይችላል። ከተሰራጨ ደግሞ ህክምና የለውም ወይም አስቸጋሪ ነው።ስለዚህ ቅድመ የማህፀን ካንስር ምርመራ ማድረግ ብቸኛው አማራጭ ነው።
ስለ ቅድመ የማህፀን ጫፍ ካንሰር ምርመራ….

የቅድመ የማህፀን ጫፍ ካንሰር ምርመራ ማለት አንድ ህመሙ ተከስቶ ከፍተኛ ደረጃ ከመድረሱ በፊት በማወቅ አስፈላጊውን ህክምና ወይንም ጥንቃቄ ማድረግ ማለት ነው፡፡

ምርመራው በተለይ ለማን የስፈልጋል?
1. እድሜዋ ከ21 ዓመት በላይ የሆነና ወንድ የምታውቅ
2. ከዚህ በፊት ተመረምራ ነፃ ከተባለች 3 ዓመት ያለፋት
3. የሰውነትን በሽታ የመከላከል አቅምን የሚያዳክሙ መድኃኒቶችን የምትወስድ ወይም የኤች አይ ቪ (HIV) ቫይረስ በደሟ ውስጥ ያለ።

ምርመራ ምን ይጠቅማል?
1. ካንሰር አለመኖሩን ማረጋገጥ
2. የቅድመ ካንሰር ምልክቶች ካሉ ባግባቡ ለመታከም
3. የተረጋገጠ ካንሰር ከተገኘ በወቅቱ ህክምናውን በመውሰድ ለመዳን
4. ውጤትን አውቆ አስፈላጊውን ጥንቃቄ ለማድረግ።
ምርመራው የት ይገኛል?
በሆስፒታሎችና አንዳንድ ጤናጣቢያዎች ላይ ይሰጣል ። የጤና ባለሙያ ቢጠይቁ የት እንደሚገኝ እና ምርመራው እንዴት እንደሚሰራ ይነግሮዎታል።

29/11/2019

!

ሴትየዋ ችግሯን ልታማክር ወደ ዶክተር ሄደች።
እኛም ሆስፒታል ደርሳ ለዶክተሩ እንዲህ አለችው
“ዶክተር እባክህ አንድ ችግር ገጥሞኛል።”
“ምን ገጠመሽ?”
“.…ከወለድኩ ገና አንድ አመት አልሞላኝም። ሆኖም ሌላ ልጅ አርግዣለሁ።
እኔ ደግሞ ተጨማሪ ልጅ በዚህ ወቅት እንዲኖረኝ አልፈልግም።”ትለዋለች ።

“እና ምን ልርዳሽ?” አላት

“ሆዴ ውስጥ ያለውን ልጅ ማስወረድ እፈልጋለሁ!” አለችው

ዶክተሩ ትንሽ አሰብ አደረገና “ለምን ከዚህ የተሻለ ሀሳብ አላቀርብልሽም?” ሲል ጠየቃት።

“ምን አይነት ሀሳብ?” ስትል ጠየቀችው ።

“አየሽ ይሄን ልጅ ከሆድሽ ለማስወረድ ሲሞከር ብዙ ችግር ውስጥ ትገቢያለሽ፣ ደም ይፈስሻል ልትሞቺ ወይም በቀጣይ ላትወልጂ የምትችይበት አጋጣሚም ሊፈጠር ይችላል።

ስለዚህ ይሄንን ሁሉ ችግር ከምታይ ለምን በእጅሽ ያቀፍሽውን ልጅ አንገድለውም?” አላት

ሴትየው በጣም አደነገጠች።

ዶክተሩ ግን ንግግግሩን ቀጠለ።
“አዎ! ለእናት እንደሆነ ሁሉም ልጅ እኩል ነው። ስለዚህ አንዱ መሞት ካለበት ሆድሽ ውስጥ ያለው ከሚሞት ይሄኛው የተወለደው ቢሞት ምንም ችግር ሳይገጥምሽ ሀሳብሽን ታሳኪያለች…” እያለ ምክረ ሀሳቡን መተንተን ጀመረ።

ሴትየዋ ግን በጆሮዋ የሚንቆረቆረው የዶክተሩ ሀሳብ ሳይሆን የአምላክ ማሳሰቢያ መሆኑን እያሰበች ለማስወርድ የዘረጋቻቸውን ሁለት እግሮቿን ሰብስባ ብድግ ብላ ተነስታ ክፍሉን ለቃ መውጣት ጀመረች።
.…ልጆቿን አንዱን በክንዷ ሌላውን በሆዷ እንደያዘች ወደ ቤቷ ተመለሰች።

👋አዎ! የተወለደም በሆድ ውስጥ ያለውም ቢሆን ለእናት ልጆቿ ሁሉ እኩል ናቸው!

(ፋሲል በቀለ እንግሊዝኛውን ለጥፎ ዴቭ ሐበሻ ተረጎመው)

ህጻናትን በውርጃ መግደል ወንጀልም ሀጢያትም ነው!

የዕለተ አርብ ውሏችሁ ያማረ ደስ የሚል ይሁንላችሁ !!!

ከእኛ ጋር ስለሆናችሁ እናመሰግናለን !!።

👍 Like እና Share በማድረግዎ ሁሌም ከእኛ አዳዲስ መረጃዎችን ያገኛሉ ።

25/02/2019

why hyperemesis is more common at 9th week? what happened blood PH of women with HEG,is it increase or decrease?

Address

GONDAR
Gonder
F2223

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when OBGYN posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share

Share on Facebook Share on Twitter Share on LinkedIn
Share on Pinterest Share on Reddit Share via Email
Share on WhatsApp Share on Instagram Share on Telegram