Garee Isporti

Garee Isporti Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Garee Isporti, AIDS Resource Center, Harar.

07/02/2026
06/02/2026
06/02/2026
06/02/2026

የሰዉ ጠባይ ከአካታች ትርክት ይልቅ ቅራኔዎችን ማግነን ይወዳል፡፡

የሰዉ ልጅ ስላለዉ ሳይሆን ስለሌለዉ እንደሚጨነቀዉ ሁሉ በጋራ ድሉ ከመደሰት ይልቅ፤ በደሉ ያንገበግበዋል፡፡

ከሽልማት ይልቅ ነዉር እንዲዛመት፤ ከመልካም መዓዛ ይልቅ መጥፎ ሽታ እንዲሰፋ፤ ከሚበላ ዘር አረም እንዲበዛ፤ ከሁሉ አካታች ትርክት አሉታዊ ነጠላ ትርክት ይደምቃል፡፡

የአሉታዊ ትርክት ብዜት ሲጨምር የፓለቲካ ገበያ ይሠምራል፤ ከዚያም ጥቂቶች ለጥቂት ጊዜ የፓለቲካ ገበያዉን ይወሩታል፡፡

የመደመር መንግሥት ገጽ - 344

06/02/2026
03/02/2026

መንግስት ምርጫ ሰላማዊ፣ ፍትሐዊ፣ አካታች እንዲሁም ካለፈው በሁሉም መስፈርት የተሻለ እንዲሆን አበክሮ እየሰራ ነው -ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)

መንግስት ምርጫ ሰላማዊ፣ ፍትሐዊ፣ አካታች እንዲሁም ካለፈው በሁሉም መስፈርት የተሻለ እንዲሆን አበክሮ እየሰራ እንደሚገኝ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ገለጹ።

6ኛው የኢፌዴሪ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በተገኙበት 5ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 10ኛ መደበኛ ስብሰባ እያካሄደ ይገኛል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) በፌዴራል መንግሥት የ2018 በጀት ዓመት የ6 ወራት የሥራ አፈፃጸም ሪፖርት ላይ ከምክር ቤት አባላት ለሚቀረቡላቸው ጥያቄዎች ምላሽና ማብራሪያ በመስጠት ላይ ናቸው።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ፥ ምርጫን አስመልክቶ በሰጡት ማብራሪያ መንግስት ምርጫ ሰላማዊ፣ ፍትሐዊ፣ አካታች እንዲሁም ባለፈው ምርጫ በሁሉም መስፈርት የተሻለ እንዲሆን አበክሮ እየሰራ ነው ብለዋል።

ሰባተኛው አጠቃላይ ምርጫ ከባለፈው የተሻለ እንደሚሆን በውጤቱ መመልከት እንደሚገባ አመልክተዋል።

ፓርላማው ብዝሃ ድምጽ ሊኖረው ይገባል ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፥ ምርጫው ምክር ቤቱ ልዩ ድምጾች የሚሰሙበት አውድ ይፈጥራል ብለው እንደሚያምኑ ተናግረዋል።

ፓርማላው የአንድ ፓርቲ ድምጽ ከሆነ ለኢትዮጵያ እንደማይጠቅማት ጠቅሰው፥ ይህን እንዲቀየር እና በርካታ ድምጾች እንዲሰሙ መንግስት በትጋት እንደሚሰራ ተናግረዋል።

ልዩ ድምጾች ለመንግስት አልፎም ለኢትዮጵያ ትልቅ አቅም እንደሚሆኑ ተናግረዋል።

03/02/2026

በኢትዮጵያ ብሔራዊ ጥቅምን የማስከበር ፍላጎትና አረዳድ እየተሻሻለ መጥቷል - ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)

በኢትዮጵያ ልዩነት የማይገድበው ብሔራዊ ጥቅምን የማስከበር ፍላጎትና አረዳድ እየተሻሻለ መምጣቱን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ገለጹ።

6ኛው የኢፌዴሪ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በተገኙበት 5ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 10ኛ መደበኛ ስብሰባ አካሂዷል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የመንግሥትን የ2018 በጀት ዓመት የስድስት ወራት የሥራ አፈፃጸም ሪፖርት ላይ ከምክር ቤት አባላት ለቀረቡላቸው ጥያቄዎች ምላሽና ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡

ብሔራዊ ጥቅምን በሚመለከት በሰጡት ማብራሪያ እንደገለጹት፤ በኢትዮጵያ ብሔራዊ ጥቅምን የማስከበር ተግባቦት እየጨመረ መጥቷል።

በጫካ ሆነው ከመንግስት ጋር የታገሉ አንዳንድ አካላት ትግላቸው መልኩን ሲስት እና የባንዳ ጣልቃ ገብነት መኖሩን ሲመለከቱ የሃሳብ ለውጥ አድርገው የተመለሱ መኖራቸውን አንስተዋል።

ይህም ብቻ ሳይሆን ባሉበት ቦታ የብሔራዊ ጥቅም ጉዳይ ሲከሰት ለመንግስት በቂ መረጃ በመስጠት በጋራ የሚሰሩ ስለመኖራቸውም ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማብራሪያቸው ገልጸዋል።

በማንኛውም የልዩነት አመለካከት ውስጥ ቢሆኑም የኢትዮጵያን ብሔራዊ ጥቅምና ጉዳይ አሳልፈው የማይሰጡ አካላት እየተፈጠሩ መሆኑን ጠቁመዋል።

በኢትዮጵያ ጉዳይ ላይ የማይደራደሩ አካላት በሁሉም አካባቢዎች መኖራቸውን ገልጸው፤ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ጥቅምን በሚመለከት ያለው አረዳድ እየተሻሻለ መምጣቱን የሚያመላክትና የሚታይ ለውጥ እንዳለ የሚያሳይ ነው ብለዋል።

Address

Harar

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Garee Isporti posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share

Share on Facebook Share on Twitter Share on LinkedIn
Share on Pinterest Share on Reddit Share via Email
Share on WhatsApp Share on Instagram Share on Telegram