Dr.Hanan Pediatrics Speciality clinic ዶ/ር ሐናን የህፃናት ልዩ ክሊኒክ

  • Home
  • Ethiopia
  • Harar
  • Dr.Hanan Pediatrics Speciality clinic ዶ/ር ሐናን የህፃናት ልዩ ክሊኒክ

Dr.Hanan Pediatrics Speciality clinic ዶ/ር ሐናን የህፃናት ልዩ ክሊኒክ We understand the unique needs of our patients and their families so you can be confident your child is getting the best care possible. We Treat Kids Better.

18/01/2023

መልካም የጥምቀት በዓል!

Wishing You a Very Happy Epiphany!

06/01/2023

Wish You a Happy Ethiopian Christmas
( Melkam Gena).

10/09/2022

Wishing you a cheerful and blessed Ethiopian New Year.

08/07/2022

Eid Mubarak Everyone! Wishing you all the blessings, happiness & mercy of this joyous day.

01/05/2022

Eid Mubarak to you all! 🌙

23/04/2022

# እንኳን ለብርሃነ ትንሳኤው በሰላም እና በጤና አደረሳቹህ።በዓሉ፤የሰላም፣የደስታ እንዲሁም የበረከት እንዲሆንልዎ ከልብ እንመኛለን!!!

ዶ/ር ሐናን የህፃናት ልዩ ክሊኒክ

We Treat Kids Better!!!

01/04/2022

May this Ramadan bring the blessings for the entire humanity that we can walk on the way of peace and harmony! Happy Ramadan to everyone.

Dr.Hanan Pediatrics Speciality Clinic.
We Treat Kids Better!!!

11/01/2022

ልጅዎ በአግባቡ እያደገ መሆኑን እና አለመሆኑን አረጋግጠው ያቃሉ ❓️ ከሆነስ በምን አረጋገጡ ❓️
🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹

👉 አንድ ህፃን ከተወለደ/ች በኃላ በጥሩ ጤናና በተገቢ ሁኔታ በእንክብካቤ ከተያዘ/ ች ጊዜ ጠብቆ የአስተዳደግ ለውጦች ያመጣሉ ::

🤱 የብዙ እናቶችም ጥያቄም እነዚህ ዝግመተ ለውጦች መቼ መታየት እንደሚጀምሩ ፣ ለውጦች መቼ መታየት እንደሚጀምሩና ምን እንደሆኑ ነው፡፡

🔷 ለዛሬ በዚህ ርዕስ ለእናቶች ለማሳወቅ እንሞክራለን ፡፡ እነዚህ የዕድገት ለውጦች በአጠቃላይ
በ3 ከፍለን ልናያቸው እንችላለን፡፡

✔️ 1. የቋንቋ ዝግመተ ለውጦች
✔️ 2. የእንቅስቃሴ ዝግመተ ለውጦች
✔️ 3. የማህበራዊና እራስን የመግለፅ ዝግመተ ለውጦች

🛑 የመጀመሪያ 1 ወር ምን አይነት እድገት ያሳያሉ⁉️

🔹 የመጀመሪያ ወር ላይ ጨቅላ ህፃናት መሰረታዊ የሆኑና ከፍላጎታቸው ጋር የተያያዙ ቅጽበታዊ ድርጊቶችን
(Reflex) ማድረግ ይጀምራሉ፡፡
እነዚህም
🔘 የሰው ፊት ማየት ጥቁርና ነጭ ቀለም መምረጥ
🔘 አፍ መመጥመጥ መክፈትና
🔘ማንኛውም ነገር ወደ አፍ ሲጠጋ መጥባት
🔘 ጣትን ወይም ትንሽ ነገር ወደ እጅ ሲጠጋ መጨበጥ
🔘 ከፍ ያሉ ድምፆች ሲኖሩ አይን መጨፈን መደንገጥ

🛑 ከ 1-3 ወራት የ እድገት ለውጦች

🔹የሰው የፊት እንቅስቃሴ መመልከት
🔹 ዙሪያቸው ያለውን ነገር ማየት
🔹 ደማቅ ቀለሞች መምረጥ
🔹 "ኦ "/ "አ" የሚሉ ድምፆች ማውጣት
🔹 በተኙበት አንገትን ቀና ማድረግ
🔹 ትንንሽ እቃዎችን መያዝ
🔹 ድምፅ ወዳለበት ቦታ መዞር
🔹 የሚያውቁትን ፊት ሲያዪ ፈገግ ማለት
🔹 ለመጫወት መሞከር

🔸 ከ4 -7ወራት

🔺የህፃናቱ እጅና አይንን ያዋሀደ እንቅስቃሴ
🔺 በእጃቸው እቃ ይዞ ወደ አፍ መክተት
🔺 ለሰው መስጠትና ከእጅ ወደ እጅ ማዘዋወር ይችላሉ፡፡
🔺 ከጀርባ ወደ ሆድ መገልበጥ፤መቀመጥ
🔺 የለመዱትን ሰው ለይቶ መፈለግ
🔺 ጮክ ብሎ መሳቅ
🔺 ረጅም "ባ" ድምፆች ማውጣት
🔺 ቁጣ፤ደስታ ሀዘን የመሳሰሉት ስሜቶችን በድምፅ መለየት መቻል

⚠️ 🛑በዚህ ጊዜ መጠንቀቅ የሚገባው ሁሉንም እቃ ወደአፋቸው ስለሚልኩ ቆሻሻ ነገር እዳያስገቡና ወደ
አፍ ገብቶ የአየር ቱቦን ሊዘጋ የሚችል ነገር እንዳይሆን መቆጣጠር ያስፈልጋል‼️

🔷 ከ 8-12 ወራት

✔️ ያለማንም እርዳታ ከተኙበት ቁጭ ማለት፤
✔️መዳህ ወይም በቂጣቸው መሳብ፤
✔️ሰውን ወይም እቃን ተደግፎ መቆም
✔️ አበባ እና ማማ ማለት መጀመር

🔷 ከ11-12 ወር

📌 ቀስ ብሎ በእግር መንቀሳቀስ
📌 በጣታቸው እቃን ማንሳት መቻል
📌 ቅርጾችን ማወቅና መፈለግ
📌 ተንቀሳቃሽ ነገሮች ላይ ትኩረት ማድረግ
📌 ሰው ያለውን ለመድገም መሞከር
📌 በእንቅስቃሴ አዎ እና አይ ማለት
📌 አንድ ወይም ሁለት ፣ቃል ማወቅ
📌 የእቃዎችን ስራ ማወቅ ለምሳሌ ማበጠሪያ፣ ማንኪያ
📌 የማያቁት ሰውን መፍራት /ማፈር
📌 እናት አባት አሳዳጊ ሲሄድ ማልቀስና መነጫነጭ

👉 በአጠቃላይ በመጀመሪያ 1 አመት ህፃናት ፈጣን ለውጥ ስለሚያመጡ እነዚህን ለውጦች ለመረዳት የሚችሉ
መጫዎቻዎች፣መፅሀፍቶችና የቴሌቪዥን ፕሮግራሞች መስጠት እንዲሁም በደንብ እንዲለምዱ በእርጋታና በፍቅር መጠበቅ ያስፈልጋል

🛑 ⚠️ እነዚህ ለዉጦች በግዜ ገደባቸዉ መታየት ካልቻሉ ወደ ጤና ተቋም አምጥቶ ማሳየት አስፈላጊ ነው‼️
ምንጭ:ዶ/ርመሐመድበሽር የህፃናት ሐኪም

🏥 በአካል ሆስፒታል መተው ለልጅዎ ሕክምና እና ምርመራ እንዲሁም የምክር አገልግሎት በህፃናት ስፔሻሊስት ሀኪም - ዶ/ር ፋሲልን ማግኘት ከፈለጉ በዝህ ስልክ ይደውሉ እና ቀጠሮ ያስይዙ
👇👇👇👇👇👇👇
☎️ 0929135785
☎️ 0984650912

👉 በስልክ/በ ቪዲዮ ማማከር ከፈለጉ ወደ 9394 ላይ ይደውሉ እና ቀጠሮ ያስይዙ ‼️

📢 እጅግ ጠቃሚ የህፃናት እና የቤተሰብ የጤና መረጃ በየቀኑ ለማግኘት የቴሌግራም ቻናላችንን Join ያርጉ እንዲሁም በፌስ ቡክ ይከታተሉን‼️
👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇

🔷 ቴሌግራም : t.me/doctorfasil

🔷 FB:fb.me/drfasilpediatrician

❤️ ጠቃሚ መረጃ ነው ብለው ካሰቡ ለሌላውም እንዲደርስ ያድርጉት

💙 ሃሳብ ጥያቄ ወይም አስተያየት ካለዎት ያድርጉ 🙏

09/01/2022

# የልጆች ኪንታሮት 🚼

የልጆች ኪንታሮት መንስኤው ምንድን ነው?

•የልጆች ኪንታሮት በሳይንሳዊ መጠሪያው Molluscum contagiosum ይባላል

•ኪንታሮት በማንኛዉም ሰዉ ላይ ሊወጣ ቢችልም በብዛት እድሜያቸው ከ1 እስከ 10 ዓመት ያሉ ልጆች ላይ ይከሰታል ፡፡

•መንስኤው ደሞ ፖክስ ቫይረስ በሚባል የቫይረስ አይነት የሚመጣ የቆዳ ኢንፌክሽን አይነት ነው።

☆የልጆች ኪንታሮት የትኛውም የሰውነት ቆዳ ላይ ሊወጣ ይችላል በብዛት ግን ፊት እጅ እና እግር ላይ ይወጣል ።

☆ሲወጣም ትንንሽ ክብ ክብ የሆኑ መሃላቸዉ ስርጉድ ያለ የቆዳ እባጮች ሲሆኑ በነጠላ ወይም በብዛት ሊወጡ ይችላሉ።

መተላለፊያ መንገዱስ ምንድን ነው?

~ በቀጥታ ከሰው ወደ ሰው በሚደረግ አካላዊ ንክኪዎች
~ በተጨማሪም በአልባሳት እና ፎጣዎች
~ ገላ መታጠቢያ ገንዳዎች
~ መጫወቻዎች ላይ ባሉ ንክኪዎች
~ ኪንታሮት ያለበት ሰው ቁስልን በመንካት
~ ኪንታሮት በመቧጨር ካንድ የሰውነት ክፍል ወደ ሌላ የሰዉነት ክፍል በመንካት ሊተላልፍ ይችላል።

# ሕክምና አለው?

☆የህፃናት ኪንታሮት ብዙ ጊዜ ያለምንም ህክምና በራሱ የሚጠፋ ነው

ሕክምና የሚያስፈልገውስ መቼ ነው?

▪︎ኢንፌክሽን ከያዘ
▪︎የፊት መልክን በጣም ካበላሸ
▪︎ መቅላት እና ከፍተኛ እብጠት ካመጣ
▪︎ ፈሳሽ ወይም መግል መሰለ ነገር ካለው
▪︎ በብልት ወይም በፊንጢጣ አከባቢ ላይ ከወጣ ሕክምና ሊያስፈልገው ይችላል

~የሕክምና አማራጮች ምን ምን ናቸው?

¤ አካላዊ ማስወገድ
¤ የተለያዩ ቅባት አይነቶች
¤ ክራዮቴራፒ (በፈሳሽ ናይትሮጅን በመጠቀም)
¤ ኪዉርቴጅ፣የጨረር ሕክምናና የመሳሰሉት....ናቸው

☆ማጠቃለያ!!!

⚠️ ቁስሎች ውስጥ ያለውን ፈሳሽ በእራስዎ ለማስወገድ መሞከር እና ማስወገድ ተገቢ አይደለም!!!

⚠️ ይህንን በማድረግዎ በቁስሎች ፈሳሽ አማካኝነት ኪንታሮቱን ሳያውቁ ወደ ሌላ የሰውነት ክፍሎች ሊያሰራጩ ይችላሉ!!

⚠️ ቆዳውን ሽፋን በመቧጨር እና በመክፈት የባክቴሪያ ኢንፌክሽን ሊያስከትሉ ይችላሉ !!!!!!

06/01/2022

እንኳን ለገና በዓል በሰላም አደረሳችሁ።

በዓሉ የሰላም፣ የጤና ፣ የፍቅር እና የደስታ እንዲሆንላችሁ ከልብ እንመኛለን!!!

መልካም በዓል!!!

ዶ/ር ሐናን የህፃናት ክሊኒክ።

18/11/2021
Ways to discipline your children 1.Remember, that your primary goals is to teach your children. 2. Align your expectatio...
17/11/2021

Ways to discipline your children

1.Remember, that your primary goals is to teach your children.
2. Align your expectations in reality.
3. Understand your child's learning style.
4. Take the time to meet your children when they are.
5. Talk to the part to the brain, what you actually listen (forehead).
6. You don't need to yell in order to learn.
7. Provide consequences.
8. Be consistent.
9. Use compassion.
10. Role model the type of self-discipline, that your child to have.

Following these 10 steps can change everything about the way you parent. If you like Dr. Conte's approach, be sure to check out his book: Zen Parent, Zen Chi...

Address

Shash Road
Harar
604

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Dr.Hanan Pediatrics Speciality clinic ዶ/ር ሐናን የህፃናት ልዩ ክሊኒክ posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Practice

Send a message to Dr.Hanan Pediatrics Speciality clinic ዶ/ር ሐናን የህፃናት ልዩ ክሊኒክ:

Share

Category