Primary Health Care Advocate - Ethiopia

Primary Health Care Advocate - Ethiopia - Health communication
- Increasing Awareness
- Improving our knowledge, perception, belief, Attitude and value
- Medical tourism
- Mental health/ Therapy

04/10/2024
04/10/2024
04/10/2024

ቋሚ ደጋፊ አባል በመሆን የልብ ሕሙማን ሕጻናትን ይርዱ!

እንደየአቅምዎ የማዕከላችን ቋሚ ደጋፊ አባል (Supporting Member) በመሆን በተመችዎት የክፍያ ጊዜ ሠሌዳ ድኅረ ገጻችንን በመጠቀም ካሉበት ቦታ ሆነው ቋሚ ድጋፍ ያድርጉ።

👉👉 www.members.chfe.org.et ላይ በአባልነት ይመዝገቡ።

ለበለጠ መረጃ +251977909090 በመስመር ወይም በዋትስ አፕ ይደውሉ።

የማዕከላችንን ድኅረገጽ ተጠቅመው ደጋፊ አባል እንዴት መሆን ይችላሉ? https://drive.google.com/file/d/12tZkd-67OIrcm_mSuf-08qL197Zxrcd7/view?usp=drivesdk



Connect with us
Facebook | Instagram | LinkedIn | TikTok | YouTube | Telegram

www.chfe.org.et

አንደኛ ደረጃ የአድሬናል ማነስ(Primary Adrenal Insufficiency) የሚከሰተው በአድሬናል እጢ ድንገተኛ ጉዳት (የአድሬናል ደም መፍሰስ) ወይም ቀስ በቀስ እያደገ በሚሄደው መጎዳ...
29/10/2022

አንደኛ ደረጃ የአድሬናል ማነስ(Primary Adrenal Insufficiency) የሚከሰተው በአድሬናል እጢ ድንገተኛ ጉዳት (የአድሬናል ደም መፍሰስ) ወይም ቀስ በቀስ እያደገ በሚሄደው መጎዳት እየመነመነ ሥር የሰደደ የአድሬናል እጥረት ያጋጥማል። ለምሳሌ፣ በራስ-ሰር(autoimmune) በሽታ ሁኔታዎች/ኢንዶክራይኖፓቲ፣ ኢንፌክሽን (ቲቢ፣ ሲኤምቪ፣ ሂስቶፕላዝማ)፣ የቫይታሚን B5 እጥረት ሊከሰት ይችላል።

አድሬናል የሚያመርታቸው ሆርሞኖች ባለመኖራቸው የተለያየ ምልክቶች ይታያሉ

• በመደበኛነት ለፀሀይ ብርሀን ያልተጋለጡ ቦታዎች ላይ ከፍተኛ ጥቁረት (ለምሳሌ የእጅ መዳፍ ፣ የአፍ ውስጥ እና የመራቢያ አካላት)
• ክብደት መቀነስ
• የምግብ ፍላጎት ማጣት
• ድካም፣ ድብርት፣ የጡንቻ ሕመም
• ድክመት፣የደም ግፊት መቀነስ
• የጨጓራ እና መሰል ምልክቶች ይታያሉ።

አብዛኛው የአድሬናል እጥረት ምልክቶች በግልፅ ላይታዩ ይችላሉ። በስትረስ ጊዜ ማለትም የቀዶ ጥገና(አነስተኛ ፕሮሲጀርን ጨምሮ እንደ ኢኔማ እና ኢንዶስኮፒ)፣ የአካል ጉዳት ፣ ኢንፌክሽኖች በአጠቃላይ የኮርቲሶል ፍላጎት ከፍ ባለበት ጊዜ ብቻ ይታያሉ። በፍጥነት ህክምና ካልተደረገም ወደ ሞት ሊያደርስ የሚችል ነው።

የደም ግፊቶን ይለኩ። ይከታተሉ። መድሀኒት አያቋርጡ።
17/05/2022

የደም ግፊቶን ይለኩ። ይከታተሉ። መድሀኒት አያቋርጡ።

29/04/2022

🧬ለድንገተኛ ልብ ድካም የመጀመሪያ ደረጃ እርዳታ

🧬 የማህፀን በር ካንሰርበኢትዮጵያ በየአመቱ 5ሺ ሴቶች በማህፀን በር ጫፍ ካንሰር በሽታ ህይወታቸውን ያጣሉ‼️የማህፀን በር ካንሰር በሽታ በአብዛኛው ሂውማን ፓፒሎማ(HPV) በተሰኘ ሻይረስ እ...
06/04/2022

🧬 የማህፀን በር ካንሰር

በኢትዮጵያ በየአመቱ 5ሺ ሴቶች በማህፀን በር ጫፍ ካንሰር በሽታ ህይወታቸውን ያጣሉ‼️

የማህፀን በር ካንሰር በሽታ በአብዛኛው ሂውማን ፓፒሎማ(HPV) በተሰኘ ሻይረስ እና በአይን በማይታይ ረቂቅ ተህዋስ ዋነኛ መተላለፊያው የግብረ ስጋ ግንኙነት ነው።በኢትዮጵያ የማህፀን በር ጫፍ ካንሰር በሽታ ከጡት ካንሰር ቀጥሎ በሁሉተኛ ደረጃ የሚገኝ ህመም ሲሆን በየዓመቱ ከ7 ሺህ በላይ ሴቶች የማህፀን በር ጫፍ ካንሰር እንደሚታይባቸው መረጃዎች ያመላክታሉ።

የበሽታውን አስከፊነት 80 በመቶ የሚሆነው ከ10 እስከ 20 ዓመት ድረስ ምልክት ሳያሳይ ቆይቶ የሚከሰት ነው።

በሽታውን ለመከላከል ክትባቱ ወደ ኢትዮጲያ ከገባ ሁለት አመት የሞላው ቢሆንም በአሁኑ ወቅት ግን በአለም አቀፍ ደረጃ እጥረት መኖሩን ተከትሎ ይህ ክትባት እድሜያቸው 14 አመት ለሞላቸው ታዳጊዎች ብቻ እየተሰጠ ይገኛል። በስድስት ወር ውስጥ ሁለት ጊዜ ክትባቱ ይሰጣል።

አስቀድሞ በሽታውን መከላከል እንዲቻል እድሜያቸው ከ15 እስከ 35 ያሉት ሴቶች ወደ ጤና ተቋማት በማቅናት የቅድመ ማህፀን ምርመራ ማድረግ ይኖርባቸዋል።

🔰የመጀመሪያ ህክምና እርዳታበአፋጣኝ እርዳታ ለሚያስፈልጋቸው የህመም አይነቶች መመሪያበሁሉም ሰው ቤት ሊኖር የሚገባ በአማርኛ እና በኦሮምኛ ቋንቋ የተዘጋጀ መፅሀፍ
18/02/2022

🔰የመጀመሪያ ህክምና እርዳታ
በአፋጣኝ እርዳታ ለሚያስፈልጋቸው የህመም አይነቶች መመሪያ
በሁሉም ሰው ቤት ሊኖር የሚገባ በአማርኛ እና በኦሮምኛ ቋንቋ የተዘጋጀ መፅሀፍ

🌀 #ሾተላይ - Rh factor   🔺 የእናት የደም አይነት Rh ኔጋቲቭ ከሆነና ባለቤትዋ Rh ፖዘቲቭ ከሆነ ነፍሰጡር በምትሆንበት ወቅት እርግዝናዋ የተለየ ክትትል ይፈልጋል፡፡ ምክንያቱም በ...
18/02/2022

🌀 #ሾተላይ - Rh factor

🔺 የእናት የደም አይነት Rh ኔጋቲቭ ከሆነና ባለቤትዋ Rh ፖዘቲቭ ከሆነ ነፍሰጡር በምትሆንበት ወቅት እርግዝናዋ የተለየ ክትትል ይፈልጋል፡፡ ምክንያቱም በእርግዝና ወቅት በማህፀን ካለዉ ልጅ ቀይ የደም ሴሎች/ህዋሶች የእንግዴ ልጁን አልፈዉ ወደ እርስዋ ደም ዉስጥ ሊቀላቀሉ ይችላሉ።
🔺 ነፍሰጡሯ Rh ኔጋቲቭ ከሆነች (ሾተላይ ካላት) የእስዋ የበሽታ መከላከያ ህዋሳት (ሴሎች) የልጁን የደም ህዋሳት እንደ ባዕድ ስለሚቆጥሯቸው እነዚህን የልጁን የቀይ ደም ሴሎች/ ህዋሳት ሊያጠፉ የሚችሉ መከላከያ አንቲቦዲዎችን/ ንጥረነገሮችን ሰዉነትዎ እንዲያዘጋጅ ያደርጋሉ፡፡
🔺 እነዚህ ሰዉነትዎ ያዘጋጃቸዉ የልጁን የደም ህዋሳት የሚፃረሩ አንቲቦዲዎች የእንግዴ ልጁን በማለፍ/በማቋረጥ በማህፀንዋ እያደገ ባለዉ ፅንስ ቀይ የደም ሴሎች ላይ ጉዳት ያደርሳሉ፡፡
🔺እናትየዋ ከዚህ በፊት አቅዳም ይሁን ሳታቅድ ዉርጃ ኖሯት የበሽታ መከላከል ህዋሶቿን ካለነቃቃች በስተቀር፤ አንቲቦዲዎቹን ለማዘጋጀት ጊዜ ስለሚያስፈልጋት የመጀመሪያ ልጇን ብዙዉን ጊዜ ያለ ምንም ችግር ልትወልድ ትችላለች፡፡ በሚቀጥሉት እርግዝናዎቿ ላይ ግን በተለይ የተረገዘዉ ልጅ Rh ፖዘቲቭ ከሆነ ችግር የሚፈጠር ስለሆነ በቂ ክትትል ማድረግ ይኖርባታል፡፡

📍ሾተላይን እንዴት መከላከል ይቻላል?
ሾተላይን ሙሉ በሙሉ በሚባል ደረጃ መከላከል ይቻላል፡፡ በእርግዝና ወቅት Rh- የሆኑ እናቶች ጥብቅ የእርግዝና ክትትል ማድረግ ይጠበቅባቸዋል፡፡ አር ኤች ኔጋቲቭ የሆኑ እናቶች የተለየ/ልዩ የሆነ ሮሆጋም/ አንታይ ዲ የሚባል ክትባት ይሰጣቸዋል፡፡ ይህ የሚሆነዉ የፅንሱ አባት ደም አር ኤች ፖዘቲቭ ከሆነ አሊያም የማይታወቅ ከሆነ ሲሆን መድሃኒቱ የሚሰጠዉ በሁለተኛዉ የእርግዝና ክፍለ ጊዜ (second trimester) ነዉ፡፡ የተወለደዉ ልጅ ደም ሲመረመር Rh ፖዘቲቭ ከሆነ እናትየዋ ድጋሚ ልጁ በተወለደ በጥቂት ቀናት ዉስጥ( በ72 ሰዓታት ዉስጥ) ለሁለተኛ ጊዜ የክትባቱን መርፌዉን ትወጋለች፡፡
እናትየዋ መድሃኒቱን የምትወጋዉ/ይህን መድሃኒት መዉሰድ የሚያስፈልግበት ዋና ምክንያት ልጇን ሊጎዳ የሚችለዉ አንቲቦዲ ሰዉነቷ እንዳያመርት ለመከላከል ሲሆን አር ኤች ኔጋቲቭ የሆኑ እናቶች መድሃኒቱን የግድ መወጋት ያለባቸዉ በሚከተሉት በአንዱ ወቅት ነዉ፡፡
• በእያንዳንዱ እርግዝና ወቅት
• ዉርጃ ካላቸዉ
• በእርግዝና ወቅት ሆዳቸዉ ላይ አደጋ ከተከሰተና
• በእረግዝና ክትትል ወቅት ከእንግዴ ልጅ ወይም ከሽርት ዉሃ ናሙና ከተወሰደ በኃላ ናቸዉ፡፡
📍Anti-D የምንለው ይህ መድሀኒት ዋጋው ውድ ቢሆንም በአንዳንድ የመንግስት ሆስፒታሎች ላይ በነፃ እየተሰጠ ይገኛል።

13/01/2022
 Alpha, Beta, Gama, Delta,Omicronልክ እንደ ማንኛውም ቫይረስ፣ SARS-CoV-2 ወረርሽኙ ከጀመረበት ጊዜ ጀምሮ በየጊዜው እየተለዋወጠ ነው። ቫይረሱ ራሱን መለዋወጡ ያልተጠ...
04/01/2022


Alpha, Beta, Gama, Delta,Omicron

ልክ እንደ ማንኛውም ቫይረስ፣ SARS-CoV-2 ወረርሽኙ ከጀመረበት ጊዜ ጀምሮ በየጊዜው እየተለዋወጠ ነው። ቫይረሱ ራሱን መለዋወጡ ያልተጠበቀ ነገር አይደለም። በደቡብ አፍሪካ ውስጥ ለመጀመሪያ ጊዜ የታየው እንደ ቤታ ያሉ ተጨማሪ ተላላፊ ዓይነቶች ቀደም ባሉት የኮሮና ቫይረስ ስሪቶች ያገገሙ ሰዎችን እንደገና የመበከል ችሎታ አላቸው ይሁን እንጂ የኮሮና ቫይረስ ክትባቶች በተወሰነ ደረጃ የመቋቋም ችሎታ ሊኖራቸው ይችላል። አሁንም፣ በቅርብ ጊዜ ጥቅም ላይ የሚውሉ ክትባቶች በኮሮና ቫይረስ ምክንያት ከሚመጡ ከባድ በሽታዎች ይጠብቃሉ።

አዲስ የቫይረሱ ተለዋጮች(Mutated Virus) ክስተት ለመቀነስ:-
⚡️ የኮቪድ-19 ክትባት ማግኘትን ጨምሮ የኢንፌክሽኑን ስርጭት ለመቀነስ እርምጃዎችን መውሰድ አዳዲስ ተለዋጮች እንዳይከሰቱ ለማድረግ ጥሩ መንገዶች ናቸው።
⚡️ክትባቶች ለከባድ ህመም፣ ሆስፒታል የመተኛት እና በኮቪድ-19 የመሞት እድልዎን ይቀንሳሉ።
⚡️ ዕድሜያቸው 18 እና ከዚያ በላይ ለሆኑ ጎልማሶች የኮቪድ-19 ማበልጸጊያ(Booster)ቢወስዱ ይመከራል።
⚡️የPfizer-BioNTech ኮቪድ-19 ክትባቶችን ከ16-17 አመት የተቀበሉ ታዳጊዎች ከመጀመሪያው የPfizer-BioNTech የክትባት ተከታታዮች ቢያንስ 6 ወራት ካለፉ ተጨማሪ መጠን ሊወስዱ ይችላሉ።
#እንከተብ

Address

AA
Jemo
1000

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Primary Health Care Advocate - Ethiopia posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Practice

Send a message to Primary Health Care Advocate - Ethiopia:

Share

Share on Facebook Share on Twitter Share on LinkedIn
Share on Pinterest Share on Reddit Share via Email
Share on WhatsApp Share on Instagram Share on Telegram