16/02/2026
የፋርማሲስቱ የፍቅር ደብዳቤ
[ Dispensary ቆሜ antibiotic ልትገዢ ለመጣሽው ልጅ....]
ዛሬ interpret የማደርግልሽ special prescription ምን ያህል እንደ narcotic እና psychotropic drugs ወድጄሽ addicted እንደሆንኩብሽ ለመግለጽም ጭምር ነው።
የኔ diazepam አንቺን ሳላስብ እንቅልፍ አልወስድክ አለኝ!! በእርግጥ tolerance እንደፈጠርሽብኝ ልንገርሽ አስብና አንደበቴ ይተሳሰራል ወይስ ketamine ልወጋና ልቀባጥርልሽ?? ደግሞ ከርቀት ሳይሽ በውበትሽ ተገርሜ atropine እንደተወጋ pt ዓይኔን የማፈጠው ነገርስ። ግን ምን ያደርጋል ከኩራትሽ የተነሳ የማሳልፈው nightmare የተሞላበት ሕይወት Efavirenz ነሽ እንዴ ብዬ እንድጠራጠር አድርጎኛል።
ፍቅርሽን በdonation ካልሰጠሽኝ በስተቀር እንደ ድህነቴ በprocurement purchase ላደርግሽ አልችልም። ደግሞ አንቺ ላይ invest ያደረኩትን reimburse የሚያደርገኝ ያለ እንዳይመስልሽ። አንቺ የኔ Brand ምን አለበት በኔ አቅም Afford ብትደረጊ አንቺ? ለእኔ እንደ promethazine 1st line እና potent እንደሆንሽ ነበር የማስበው፤ አንቺ ግን Antidote እንደሌለው Barbiturate toxicity ሆነሻል!!
ቢሆንም እንደ Digoxin ጠባብ therapeutic index የለኝም፤ በሰፊው Pencillin ልቤ እጠብቅሻለሁ ግን የማልደብቅሽ ነገር ቢኖር አንቺን በቀን QID ማሰቡ ታክቶኛል። endpoint እንደ ሌለው reaction እስከ መቼ Titrate ልታደርጊኝ አስበሻል?? የ Tubocurarine structure ማንበብ እራሱ እንዳንቺ አልታከተኝም።
ልቤን በኩራትሽ mortal and pestle sizun reduce፤ በንቀትሽ base እና በግልምጫሽ spatula levigate አድርገሽ ointment ካደረግሽኝ ሰነባብተሻል።
ከLeujocum aestivum የተገኘውን Galanthamine ካልወሰድኩ ስለምረሳ ይህንንም ፅፌልሻለሁ። Minimal Change disease(MCD) steroid sensitive እንደሆነ እኔም ላንቺ sensitive ሆኛለሁ ግን ከpoor prgnosis ጋር!!
ቆይ አንቺ ማነሽ?? ሰውስ 'እንደ Erythromycin መራራ ናት ትቅርብክ!' ለምን አለኝ?? ለምንድነውስ BBB Cross እያደረግሽ CNS Disturbance የምታመጭብኝ??
ወይ ደግሞ ልብሽን ስጭኝና Macerate አድርጌው ፍቅርን Extract ላድርግ.. ካንቺ ጋር ሆኜ የምኖረው QALY በእርግጥም አንቺ ከሌለሽበት ሕይወት ይሻላል።
አስቢበት እኔ Chiral ስለሆንኩ dosage form ቀይሬ ሌሎች ጋር መሄድ አያቅተኝም። አዎ አስቢበት እንደ TDF+3TC+ EFV ዕድሜ ልኬን ላስብሽ አልፈልግም። እኔ በcGMP ስለምመራ Flexible እሆንልሻለሁ።
አታስቢ ፍቅርሽን ከinfusion ወደ bolus ብትቀይሪው Red man syndrome አይፈጠርብኝም። የፍቅርሽ Bioavailabilty 100% እንደሆነ በዚሁ አጋጣሚ ልነግርሽ እወዳለሁ። ስለዚህ የኔ ፍቅር Updated, Recent and Reliable የሆነ Goal of Therapyሽን ንገሪኝና Treatment approach ወስኜ ላንቺ ያለኝን Pharmaceutical care ላሳይሽ።
ያንቺው አፍቃሪ: ከፋርማሲ