13/10/2020
ጥናት ፦
በኮቪድ-19 ታሞ የሚያውቅ ሰው ቫይረሱ በድጋሚ ሊይዘው እንደሚችል አዲስ የወጣ ጥናት አመለከተ።
ትናንት ላንሴት መጽሄት ላይ የወጣው ጥናት ዩናይትድ ስቴትስ ኔቫዳ ግዛት ውስጥ አንድ የሃያ አምስት ዓመት ወጣት ሚያዝያ ወር ውስጥ ኮሮናቫይረስ ይዞት እንደገና ሰኔ ወር ላይ እንደያዘው አመልክቷል።
በሁለተኛው በጽኑ ታሞ ሆስፒታል መግባቱና ተጨማሪ ኦክሲጂን የሚያስፈልገው ደረጃ ላይ ደርሶ እንደነበር ጥናቱ አክሏል።
በዓለም 2 ጊዜ በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው የተረጋገጠው ሰዎች እስካሁና አምስት ብቻ ሲሆኑ የዩናያትድ ስቴትሱ የመጀመሪያ መሆኗ ታውቋል። (VOA)