10/06/2025
የነፋስ መውጫ ፪ ደረጃ ት/ቤት የ10 I ተማሪዎች በዜግነት መምህራቸው በመ/ር ባይነሳኝ አካሌ በመመራት የዘርፌ አስፋው ፋውንዴሽን የዘለቄታ በጎ አድራጎት ድርጂትን ጎብኝተዋል።
በጉብኝታቸው መረዳዳት ፣ሀገርን መውደድ ፣ የሀገር ባለውለታ የሆኑትን አረጋዊያንን ማክበር እና ፍቅር መስጠት ምን ማለት እንደሆነ በንድፈ ሀሳብ ካገኘነው ዕውቀት በተጨማሪ ከዚህ ቦታ በመገኘት በተግባር ተምረንበታል በማለት ተማሪዎች አስተያየታቸውን ሰጥተዋል::