20/03/2022
እንኳን ደስ አላችሁ እንኳን ደስ አለን!
=========================
በዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ የንግስት እሌኒ መሀመድ መታሰቢያ ኮምፕሬሄንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል በህግ ማስከበር ዘመቻ ላበረከተው አስተዋጽኦ የዋንጫ እና የምስጋና ምስክር ወረቀት ተበርክቶለታል።
ሆስፒታሉ በኢትዮጵያ በተደረገ የሕግ ማስከበር ዘመቻ፤ የሕብረ ብሔራዊ አንድነት ዘመቻ ጉዳት ለደረሰባቸው ዜጎች የተቀናጀ የሕክምና አገልግሎት በመስጠት ሕይወትን የመታደግ እና የኃይል አባዥነት ሚናን በማበርከት በተፈጸመ ሙያዊ አስተዋጽኦ ሽልማቱ እንደተበረከተ ተጠቁሟል።
በተያያዘ ዜና የንግስት እሌኒ መሀመድ መታሰቢያ ኮምፕሬሄንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል በፌዴራል ጤና ሚኒስቴር በተደረገ አጠቃላይ የአፈጻጸም ግምገማ ተፈላጊውን ሙያዊ ፥ ድርጅታዊ እና ሌሎች መስፈርቶችን ማሟላቱ ተረጋግጦ በዛሬው ዕለት የብቃት ማረጋገጫ ምስክር ወረቀት እንደተበረከተለት ይታወቃል።
ሆስፒታሉ በ2013 ዓ.ም በአጠቃላይ የስራ አፈፃፀም ባሳየው ብቃት ከኤ.ፌ.ዴ.ሪ ጤና ሚኒስቴር እና ከደ/ብ/ብ/ሕ/ክ/ መንግስት ጤና ቢሮ የተለያዩ የገንዘብ፣ የዋንጫና የዕውቅና ሰርትፍኬት ማግኘቱ የሚታወስ ነው።
የመረጃ ምንጫችን የንግስት እሌኒ መሀመድ መታሰቢያ ኮምፕሬሄንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ሕክምናና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ ቺፍ ኤክስክዩቲቭ ዳይሬክተር የሆኑት ዶ/ር አያኖ ሻንቆ ናቸው ሲል የዘገባው የዩኒቨርሲቲው ህዝብ ግንኙነት እና ዓለም ዓቀፍ ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ነው።
ቀን መጋቢት 10/2014 ዓ.ም
Let Your Light Shine in the Society!
ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለመግኘት፣
ድረ ገጽ:- www.wcu.edu.et
ፌስቡክ:-Wachemo University-WCU
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
ዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ