13/11/2025
በወቅታዊ ሄሞራጅክ ፈቨር ( Hemorrhagic Fever ) በሽታ ቅድመ ጥንቃቄን አስመልክቶ የባለድርሻ አካላት ውይይት ተካሂዷል =============
በሽታውን አስመልክቶ የኢፌዴሪ ጤና ሚንስቴርን ጨምሮ የተለያዩ ባለድርሻ አካላት በትኩረት እየተከታተሉ ቢሆንም ተቋማዊ የጥንቃቄና የዝግጅት ሥራዎችን ለመሥራት አስቻይ ውይይት ተካሂዷል ።
-------
ዶክተር ወኪል ወልዴ ፦ በምክትል ፕረዚዳንት ማዕረግ የወላይታ ሶዶ ዩኒቨርስቲ ጤና ሳይንስና ሕክምና ኮሌጅ ኮምፕርሄንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ቺፍ ኤክስኪዩቲቭ ዳይሬክተር ፥ የሕብረተሰብ ጤና ስጋት ሲከሰት ከተለያዩ ባለድርሻ አካላት በትኩረትና በቅንጅት የሚሰራ ቢሆንም እንደተቋም ቅድመ ዝግጅት ሥራዎችን መሥራት ወሳኝ ነው ብለዋል ።
ዶክተር አክለው ፤ አስፈላጊውን ግብዓት ለማሟላት (PPE) ፣ የግንዛቤና የጥንቃቄ ሥራዎች በትኩረት እንዲሰሩ አቅጣጫ አስቀምጠዋል ።
በውይይቱ የሁሉም ሕክምና ትምህርት ክፍል ኃላፊዎች፣ ሕክምና አገልግሎት ዳይሬክተሮች እንዲሁም ሌሎች ባለድርሻ አካላት ተሳትፈው በጋራ መግባባት የቅድመ ዝግጅት ሥራዎች እየተሰሩ ይገኛሉ ።
ኮሙኒኬሽንና ሕዝብ ግንኘነት
ሕዳር 04/2018 ዓ.ም