Wondimagegn Bassa

Wondimagegn Bassa Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Wondimagegn Bassa, AIDS Resource Center, Wolayta, Sodo.

16/09/2025
16/09/2025
የጠ/ሚኒስትሩ "የመደመር መንግሥት" መጽሐፍ ተመረቀ  | የጠ/ሚኒስትር  ዐቢይ አህመድ 4ኛ መፅሐፍ የሆነው  "የመደመር መንግሥት" በአዲስ ኢንተርናሽናል ኮንቬሽን ማዕከል ተመርቋል።"የመደመር...
16/09/2025

የጠ/ሚኒስትሩ "የመደመር መንግሥት" መጽሐፍ ተመረቀ

| የጠ/ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ 4ኛ መፅሐፍ የሆነው "የመደመር መንግሥት" በአዲስ ኢንተርናሽናል ኮንቬሽን ማዕከል ተመርቋል።

"የመደመር መንግሥት ዋነኛ ግቡ ኢትዮጵያን ለኢትዮጵያውያን ማስረከብ ነው" ተብሏል፡፡

መጽሐፉ በሦስት ዋና ዋና ክፍሎች፣ በ418 ገጾችና በ13 ምዕራፎች የተቀነበበ ነው፡፡

የፕላንና ልማት ሚኒስትር ዶ/ር ፍጹም አሰፋ ባቀረቡት የመጽሐፍ ዳሰሳ፤ “ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በመጽሐፋቸው እንደ አገር እንዴት ኋላ ቀረን የሚለውን ጉዳይ ፈትሸው፣ ህዝባችንን እንዴት ወደ ሁለንተናዊ ብልጽግና እናድርሰው የሚለውን መፍትሄ አስቀምጠዋል።” ብለዋል።

የጠቅላይ ሚኒስትሩ የምስራቅ አፍሪካ ጉዳዮች አማካሪ ጌታቸው ረዳ፣ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የፍልስፍና መምህር ዶ/ር ዳኛቸው አሰፋ እና ሌላው የፍልስፍና ምሁር ዘሪሁን ተሾመ በመጽሐፉ ዙሪያ ያላቸውን ምልከታ ለታዳምያን አካፍለዋል።

በምረቃ ሥነ ስርዓቱ ላይ ጠ/ሚ ዐቢይ አህመድ፣ ፕሬዚዳንት ታዬ አፅቀስላሴና ሌሎች ከፍተኛ የመንግሥት ባለሥልጣናት፣ የኪነጥበብና የሚዲያ ባለሙያዎች እንዲሁም ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።

16/09/2025
16/09/2025
16/09/2025
16/09/2025
15/09/2025
ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ንግድና ገበያ ልማት ቢሮ የተላለፈ መልዕክት‎‎መስከረም 5/2018 ዓ.ም ‎‎መንግስት ከመስከረም ወር ጀምሮ ለመንግስት ሰራተኞች ደመወዝ ጭማሪ ለማድረግ ማስታወቂያ ከማ...
15/09/2025

ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ንግድና ገበያ ልማት ቢሮ የተላለፈ መልዕክት

‎መስከረም 5/2018 ዓ.ም

‎መንግስት ከመስከረም ወር ጀምሮ ለመንግስት ሰራተኞች ደመወዝ ጭማሪ ለማድረግ ማስታወቂያ ከማስተላለፉ ጋር ተያይዞ በአንዳንድ ህገ-ወጥ ነጋዴዎች አለአግባብ የዋጋ ጭማሪ የማድረግ ሁኔታ በመታየቱ በክልሉ ሁሉም መዋቅሮች የዋጋ ማረጋጋት ግብረ-ሀይል ተቋቁሞ እንቅስቃሴ እየተደረገ መሆኑ ይታወቃል።

‎በግብረ-ሀይሉ የቁጥጥር እንቅስቃሴም ጥሩ ለውጦች እየታዩ ቢገኝም በ8034 ነጻ የስልክ መስመር ከህብረተሰቡ በደረሱ ጥቆማዎች በአርባ ምንጭ፣ ዲላ ፣ወላይታ ሶዶ ፣ሁምቦ እና ጂንካ ከተሞች በሚገኙ የንግድ ድርጅቶች ላይ የቤት አካራዮች ኪራይ በመጨመር ነጋዴዉ ያልተገባ ዋጋ ጭማሪ እንዲያደርግ የሚገፉ ሁኔታዎች እየተፈጠሩ መሆኑን የደረሱ አቤቱታዎች ያሳያሉ።

‎ስለሆነም የ12ቱ ዞኖችና የ3ቱ ሪጅዮ ፖሊስ ከተሞች ንግድ ከገቢ መዋቅር ጋር በመቀናጀት አካራዮችን የማወያየት እንዲሁም የአካባቢውን ሚዲያ በመጠቀም የንግድና ዘርፍ ማህበራት ምክር ቤት ፕሬዚዳንቶች መግለጫ እንዲሰጡ የማድረግና ከፍትህ ተቋም ጋር በመቀናጀት በህገ-ወጦች ላይ አስተማሪ እርምጃ እንዲወሰድ ጥሪ አቅርቧል።

ሸማቹ ህብረተሰብም ህገ-ወጥነትን ለመከላከል ይቻል ዘንድ በ8034 ነጻ የስልክ መስመር ጥቆማ በመስጠት አጋርነቱን እንዲያሳይም ቢሮው ይጠይቃል።

15/09/2025

Address

Wolayta
S**o

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Wondimagegn Bassa posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share

Share on Facebook Share on Twitter Share on LinkedIn
Share on Pinterest Share on Reddit Share via Email
Share on WhatsApp Share on Instagram Share on Telegram