06/02/2026
አምቡላንስ ፊት ለፊት ላይ “AMBULANCE” የሚለው ጽሑፍ ተገልብጦ (የመስተዋት ምስል ሆኖ) ለምን እንደሚጻፍ አስተውለው ያውቃሉ?
ከፊት ለፊታችን የሚመጣ አምቡላንስ ላይ ያለው ጽሑፍ ለምን ተገልብጦ እንደሚጻፍ ጠይቀው ያውቃሉ? መልሱ ቀላል ነው!
አንድ አሽከርካሪ በመኪናው የኋላ መመልከቻ መስተዋት (Rearview Mirror) በኩል ሲመለከት፣ በመስተዋቱ ባሕርይ የተነሳ ተገልብጦ የተጻፈው ጽሑፍ ተስተካክሎ ይታየዋል። ይህም አሽከርካሪው “አምቡላንስ” መሆኑን ወዲያውኑ ለይቶ እንዲያውቅና የሰከንድ ልዩነት ሳይፈጥር መንገድ እንዲለቅ ይረዳዋል።
ህይወትን እናስቀጥል!
☎️ +251 98 558 5888 | 8558
📍 ኢትዮ ቻይና ጎዳና ፣ ጎተራ ወንጌላዊት ህንጻ አጠገብ፣ ኢሻአል ህንጻ 3ኛ ፎቅ፣ አዲስ አበባ ፣ ኢትዮጵያ