08/05/2024
ከመጠን በላይ የሆነ የአንጀት ጋዝ (excessive flatulence)
የሰው ልጅ በቀን ውስጥ እስከ 20 ጊዜ ድረስ ከአንጀቱ በፊንጢጣው አየር(ጋዝ ወይም ፈስ) ሊያስወጣ ይችላል፡ ብዛት ያለው ጋዝ ምክንያቶቹ ብዙ ናቸው
- የምግብ አለመስማማት/አለመፈጨትና አለመመጠጥችግሮች(food into and indigestion)
-የአመጋገብ ችግር: ሲጋራ ማጨስ፡ ከመጠን በላይ ማስቲካ ማኘክ፡ ስንውጥ ብዙ አየር ወደ ሆድ መግባት ችግር
- በአንጀት ውስጥ ከተለመደው በላይ የሆነ የባክቴሪያ እድገት
-ሌሎች የትላትልና የፈንገስ ኢንፌክሽን
- የአንጀት ቱቦ እብጠትና የአንጀት ኪስ(diverticulum) መፈጠርና ኢንፌክሽን
-የአንጀት ቱቦ ኢንፍላሜሽን(Irritable bowel syndrome), celiac disease
የሚከተሉት ምልክቶች ካሉ አደገኛ ምልክቶች ሊሆኑ ስለሚችሉ ወደህክምና መሄድ ያስፈልጋል
-ደም የቀላቀለ ሰገራ
-የሆድ ድርቀት ወይም ተቅማጥ
-የማያቋርጥ ማቅለሽለሽና ትውከት
-የክብደት መቀነስ
-ከበድ ያለ የሆድ ቁርጠት
-ተያያዠ የደረት ስር ውጋት
ከላይ የተገለፁት ምልክቶች ካሉ ሀኪምዎ የሚከተሉትና ሌሎች ተጨማሪ ምርመራወችን እንዳስፈላጊነቱ ሊያዝልዎት ይችላል
-የደምና የሰገራ ላቦራቶሪ
-የሆድ አልትራሳውንድ
-በካሜራ የታገዘ የአንጀት ቱቦ ምርመራ
-የፓቶሎጅ ምርመራና ሌሎችም
ሀኪምዎም ከላይ ባሉት ምርመራዎች ውጤት ተመስርቶ የሚከተሉትንና ሌሎች ያልተጠቀሱ ህክምናዎችን ሊያዝልዎ ይችላል
- የአመጋገብ ስርአት ማስተካከል (ብዙ ጋዝ የሚፈጥሩ ምግቦችን መቀነስ/ማስወገድ፣ የማይስማማዎትን/የማይፈጩ ምግቦችን ለይቶ መቀነስ/ማቆም፣ ስኳራማ ምግቦችን መቀነስ፣ የተጠበሱና ስብ የበዛባቸውን ምግቦች መቀነስ፣ ጋዝ ያላቸውን መጠጦች መቀነስ፣ በቂ ውሃ መጠጣትና የመሳሰሉት)፣ ለተጨማሪ ምክር ሀኪምዎን ወይም የስነ ምግብ ባለሙያን ያማክሩ
-የሚፈጠረውን ጋዝ የሚቀንሱ ወይም ከተፈጠረ በሗላ ለማስወገድ የሚያግዙ መድሀኒቶችን ሊያዝልዎት ይችላል( ምሳሌ simethicone, activated charcoal, lactase supplements etc)
ለበለጠ መረጃና ህክምና የውስጥ ደዌ የጨጓራና የአንጀት ህክምና ስፔሻሊስትን ያግኙ