21/12/2021
በሕወሓትም በብልጽግናም ባለስልጣናት “ለሰላም ዕድል ለመስጠት” የሚል የጋራ ቋንቋ ተጀመረ።
ህወሓት በሊቀመንበሩ ደብረጽዮን ገብረሚካኤል (ዶ/ር) በኩል ለተባበሩት መንግሥታት በጻፈው ደብዳቤ ኃይሎቹ ወደ ትግራይ ክልል እንዲመለሱ ማዘዙን ገለጸ። ደብረጽዮን ገብረሚካኤል (ዶ/ር) ለመንግሥታቱ ድርጅት ትናንት እሁድ ታኅሣሥ 10/2014 ዓ. ም. ጻፉት በተባለው ደብዳቤ ላይ ኃይሎቻቸው ከትግራይ ክልል ውጪ ከነበሩባቸው አካባቢዎች “ለሰላም ዕድል ለመስጠት” ለቀው እንዲወጡ ማዘዛቸውን አመልክተዋል።
በሌላ በኩል የመንግስት ሚኒስትር የሆኑት ሬድዋን ሁሴን ከቱርኩ አናዶሉ ኤጀንሲ ጋር ባደረጉት ቆይታ፣ መንግስት ይህን የሚያደርገው ውስጣዊ ችግሮችን በሰላማዊ መንገድ ለመፍታት “ለሰላም ዕድል ለመስጠት” ነው ብለዋል።
በተጨማሪም በተባበሩት መንግስታት የኢትዮጵያ አምባሳደር አቶ ታዬ በትዊተር ገጻቸው እንዳሉት “ለሰላም ዕድል ለመስጠት” ሕወሓት ትጥቁን ይፍታ እንጂ እርቀ ሰላሙ ይጀመራል TPLF will disarm & be accountable to the full force of the law.The promise of peace is in reconciliation between all Ethiopians who respect and abide by the rule of law ብለዋል።
ሁለቱም የመንግስት ባለስልጣናት ሕወሓት ትጥቅ ከፈታ ወደ እርቀ ሰላም ( ድርድር) የማይኬድበት ምንም ምክንያት እንዳሌለ ጠቁመዋል።