26/11/2023
ብቸኝነት አባዜ እና የጅን ጥቃት፡፡
ከኡስታዝ አቡ ፈርሃን መጣጥፍ ላይ የተወሰደ፡፡
አባዜ ሲል አጥኚው የተጠናወተን ግዜያዊ ማንነት መሆኑ ልብ ሊባል ይገባል፡፡ አንድ ሰው ደርሶ ብቸኝነት ደርሶ ከሰው መራቅን ከመረጠ ይህ አባዜ ከጀን ጋር የሚያገናኛቸው ነገሮች አሉ ፡፡ ብቸኝነት ችግርን ተከትሎ መጎዳትን ተከትሎ ስነ አእምሮ መረበሽን አስከትሎ የሚፈጠር ነው፡፡ ግና የዚህ ጅን ጥቃት ድንገታዊም አይደለም፡፡ ዝምታን ይመርጣል ታማሚው ከዛንም ወደ ብቸኝነት አለም ይዞት ይገባል፡፡ እስኪ ምልክቱን በክፍሎች ከፋፍለን አንድ በአንድ እንመልከት ታካሚዎችም በቀልብ ዶክተር ቻናል ላይ በተፈጠረላቸው እድል አማካኝነት ህክምናቸውን መከታተል ይኖርባቸዋል፡፡
ክፍል 2.
7. ሽንትቤት ለረጅም ሰአት መቀመጥ፡፡ እነኚህ ሰዎች በሽንትቤትነት ደረጃ ተጠቃሎ ይቀመጥ እን ሻወር ሲወስዱ በራሱ ከሰላሳ ደቂቃ በላይ ይቆያሉ፡፡ ከራሳቸው ጋር ምን እንደሚያወሩ ማወቅ አይቻልም ወይም ይከብዳል ግና እነኚህ ሰዎች በዋናነት ከሰው ተነጥለው መቀመጥ አላማቸው ስለሆነ ሽንትቤት ሻወር ቤትን ተመራጭ ያደርጉታል፡፡ በተዘዋዋሪም በጥናቱ ላይ እንዳየነው በሩቅያህ የደከመ ጅን እንደምንም ብሎ አዳክሞ ሽንትቤት ውስጥ በማስገባት እንዲያለቅሱ ያደርግና እዚያው ጉልበቱን ያጎለብታል፡፡ አላህም ይጠብቀን፡፡
8.ቅዠት፡፡ ይህንም የጅን ጥቃት ሰለባ የሆኑ ሰዎች ለየት ከሚያደርጋቸው ምልክቶች አንዱ ይህ ነው፡፡ ትንሽ እንዳሸለቡ ቅዠት ያሰቃያቸዋል፡፡ ቅዠታቸው ሲበዛ የቀን ቅዠት ይጀምራቸዋል፡፡ ይህን አሏህ ያንሳላችሁ ፡፡ ለሊት በጩቤ ስትወጉ መሰማት ስትሞቱ ህመሙን መረዳት ስትወድቁ ህመሙን ማወቅ ጮሆ መነሳት ይህ በነርሱ ላይ የሚታይ ሲሆን የቀን ቅዠት ደግሞ ድንገት ከተቀመጡበት ዘሎ በመነሳት ሰው መጉዳት መጮህ ማዛጋት ማጨብጨብ ምልክቶቹ ናቸው፡፡
9. እንቅልፍ ማብዛት፡፡ ቢተኙ የማይወጣላቸው ድካም የእንቅልፍ ስሜት አለ፡፡ በቀን መተኛት በማታ መተኛት ቁጭ ብለው ቁመው ተደግፈው መተኛት ይጀምራሉ፡፡ ይህ የበሽታውን የጅን ጥቃቱን መግነን አመላካች ነው፡፡ አሏህም ከዚህ ጥቃት ይጠብቀን፡፡
10.ኢማን ላይ ደካማ መሆን፡፡ ሰላት ላይ መድከም ሰላትን ማቆም መጀመር፡፡ ቁርአን አለመግራት ሊቀሩ ሲሉ ማዛጋት አይን ማቃጠል፡፡ ብሎም ሰላም ማጣት አመላካች ሲሆን ባስ ሲልም አዛን ሲል መናደድ መበሳጨት ይጨመራል፡፡
11.ከአስር ኋላ ከልክ ያለፈ ደስታ አልያም ከልክ ያለፈ ሃዘንና ፍርሃት፡፡ ይህ ከተፈጠረ ይህ ሰው ላይ ያለ ጅን ጉልበት ማግኘቱን አመላካች ሲሆን ወድያው እልባት ካልተወሰደም በሰውየው ቀን ተቀን ህይወት ላይ ጣልቃ መግባት ይጀምራል፡፡
12.ብቸኝነት ፡፡ በስተመጨረሻም ብቸኝነት፡፡ ከሰው ጋር ተቀምጠው ብቻቸውን እንደሆኑ መሰማት፡፡ የሰው መብዛት በፍፁም አያረካቸውም፡፡ እራሳቸውን እንደ ተጎጂ መቁጠር ከሰው መራቅን በሙሉ ይጀምራሉ፡፡
ኢስላማዊ ሸሪአዊ ህክምናዎችን በቀልብ ዶክተር ስር ባሉ ኡስታዞች እንደሚያገኙ ሊያውቁ ይገባል፡፡ ሁሌም ኡማውን በማገልገል ነጋ ጠባ የአላህን ውዴታ ከሚሹ ባሮች ነንና ይህን ብሎም ሌሎች አይነት ምልክቶች ካሉቦት ባፋጣኝ ያናግሩን እልባትም ያግኙ፡፡
https://t.me/Qallbdoc