የአፊያዎ ምርጫ በቀልብ ዶክተር

የአፊያዎ ምርጫ  በቀልብ ዶክተር Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from የአፊያዎ ምርጫ በቀልብ ዶክተር, Mental Health Service, جدة, السعودية, Jeddah.

በቤት ውስጥ ጅን ስለመኖሩ ምልክቶች!ከዶክተር አቡ ፈርሃን ጥናታዊ መጣጥፍ ላይ የተወሰደ፡፡እናንተ ሰዎች ሆይ በቤቶቻችሁ ስር ጅኖችን በምታስተውሉ ወቅት የሶስት ቀን ማስጠንቀቅያ ስጧቸው ያም ...
03/09/2022

በቤት ውስጥ ጅን ስለመኖሩ ምልክቶች!
ከዶክተር አቡ ፈርሃን ጥናታዊ መጣጥፍ ላይ የተወሰደ፡፡
እናንተ ሰዎች ሆይ በቤቶቻችሁ ስር ጅኖችን በምታስተውሉ ወቅት የሶስት ቀን ማስጠንቀቅያ ስጧቸው ያም ሸይጧን ከሆነ ከቤት ውስጥ አይወጣም ሙእሚን ጅን ከሆነ ግን ይወጣል፡፡ በናንተም ውስጥ ድንበር አላፊዎችን አሏህ አይወድምና የተባለውን ነብያዊ ሃዲስ አስታውስ፡፡ አሏህ ለሁሉም እኩሊታ ነው፡፡ ሁሉንም በእኩል የሚዳኝ ፍትሃዊ ጌታህ ነው፡፡ ቤትህ ውስጥ ሲህር ካለ በስቃይህ ለይ ጅን ካለ ግን በነኚህ ለይ፡፡
ክፍል 2
ምልክቶች
1.የተቃጠለ ነገር ማሽተት፡፡ ምሳሌ ክብሪት ሲቃጠል አይነት ሽታዎችን በተለምዶ ቤት ውስጥ በብዛት ማሽተት፡፡
2.ድንገት የበሮች ብርግድ ብሎ መከፈት አልያም በሃይል መዘጋት (የንፋስ ዝውውር ሳይኖር፡፡)
3.የሰው ድፅ የሚመስሉ መጣራቶች አልያም መንሾካሾኮች መኖር፡፡
4.ቤት ውስጥ ከሌላው ግዜ የበለጠ ጭቅጭቅና ጥል መኖር፡፡ በቤተሰብ ውስጥ በየቀኑ ጥል ፈጣሪዎች ናቸው፡፡
5.ቤት ውስጥ አባወራ አልያም ቤት የሚያስተዳድረው ሰው ኪሳራ ውስጥ መግባት
6.ከኋላ የሚከተለን ያለ አካል እንዳለ ስሜት መሰማት፡፡ ከኋላ ከበድ ያለ ትንፋሽ መስማት፡፡
፡-በቤት ውስጥ ያለ ጅን አስከፊ ሲሆን
7.ሴቷ ሚስት ብታረግዝም ቶሎ ቶሎ ያስወርዳታል፡፡
8.ህፃናት ወይም ጨቅላዎች ባልታወቀ ምክንያት ቶሎ ይሞታሉ፡፡ አልያም ሰውነታቸው ይበላሻል፡፡
9.በቤት ውስጥ ጅኑ እንደ ጥቁር ውሻ ሁኖ መታየት አልያም ድመት ሁኖ መታየት ብሎም እባብና ታይቶ የማይታወቅ ትልቅ ሸረሪት ሆኖ ብቅ ብሎ መጥፋት ይጀምራል፡፡
10.ቤት ውስጥ ድንገተኛ አስደንጋጭ ነገሮች ያደርጋሉ፡፡ ከባባድና ሰው መጣል የማይችላቸውን እቃዎች ይጥላሉ ፍሪጅ ይጥላሉ፡፡ በሮችን በሙሉ ይከፍታሉ፡፡ ብሎም ጣራ ይገነጥላሉ፡፡ መስታዎቶችን ይሰብራሉ፡፡
ከዚህ አይነት ሲህሮች በአሏህ ሃይል እንጠበቃለን፡፡ ከሸይጧን ጭፍሮችም ሸር እንዲሁ! በርሶ ላይ ማንኛውም አይነት ህመሞች ሲኖሩ በሲህርና በአለማዊ በሽታዎች ሲጠቁ አሏህም ካለ በኢስላማዊ እውቀት ብቁ የሆኑ የሩቅያህ ዶክተሮችን አለማዊ የሜዲካል ዶክተሮችን የሳይካትሪስት ዶክተሮችን ብሎም የሃዲስ ምሩቆችን እና የሸሪአ ምሩቅ ምሁሮችን ወደሚያገኙበት ወደ ቀልብ ዶክተር ቻናል በማምራት ዶክተር ወይም ኡስታዝ ብለው በማናገር ህክምናዎን በረሱል ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም መንገድ ብቻ ያግኙ፡፡ ለሁላችሁም ከልብ አፊያን ተመኘሁ ወሰላሙ አለይኩም ወራህመቱሏህ!!

https://t.me/Qallbdoc

በዶክተር አቡ ፈርሀንየወሲብ ደጋሚ ጅኖች ሲህር!!ይህ ሲህር በሴቶች ላይ እድሜ ከ 15 አመት ጀምሮ ለወንድ ከ 11 አመት ጀምሮ መድገም ይጀምራሉ፡፡ ድግምቱ በህፃናቱ ላይ አይስራ እንጂ የወደ...
01/09/2022

በዶክተር አቡ ፈርሀን
የወሲብ ደጋሚ ጅኖች ሲህር!!

ይህ ሲህር በሴቶች ላይ እድሜ ከ 15 አመት ጀምሮ ለወንድ ከ 11 አመት ጀምሮ መድገም ይጀምራሉ፡፡ ድግምቱ በህፃናቱ ላይ አይስራ እንጂ የወደፊት ሀይወታቸውን አሰናካይ ነው፡፡

ምልክቶቹ

ለሴቶች

1.ከወንድ ጋር በእጅጉ ልፍያ ይህም ወሲባዊነትን ያመላክታል፡፡ ይህን የወሲብ ጥማታቸውን ጋብ እንዲያደርግ ይረዳቸዋል፡፡

2.ለሊት ከመሐል እንቅልፍ ቀስቅሶ የወሲብ የፍትወተ ስጋ ምኞት ማስመኘትና እራስን ቢያንስ ከ5 ግዜ በላይ ማርካት፡፡

3.በህልም የሚገናኛት ሰው ማየት ይህን ሰው በአካል ሊያውቁትም ላያውቁትም ይችላል፡፡ ይህ ሰው ካልመጣ በእጅጉ መናፈቅ፡፡

4.በመቀመጫ ወሲብ የማድረግ ከፍተኛ ፍላጎት ፡፡ ባለቤትም ካላት በመቀመጫ የሚደረግን ወሲብ አዘውትሮ መምረጥ፡፡

5.አንድን ወንድ በምታይበት ወቅት በወሲብ ስሜት መመኘት የተፈጥሮ ሁኔታ ሆኖ ሳለ የነርሱ ግን በእጅጉ መፈታተንና ከዚያንም ከወሲብ ቡሃላ ድብርት መሰማት፡፡

6.አልፎ አልፎ ከፍተኛ የራስ ምታት በ መድሃኒት እንኳን የማይለቅ ራስምታት፡፡

7.ወንዶችን በሙሉ መጥላት ፡-ይህ የሚሆነው አልፎ አልፎ ነው በዚህ ግዜ ታድያ ሴቶችን ብቻ ነው የሚመኙት፡፡

ለዚህም ህክምና አንድ ብቻ ምልክት የሚታይቦት ከሆነ

1.ሲተኙ በሱና መተኛት

2.ከእንቅልፎ ሲባንኑ ዱአ አድርገው መተኛት

3.አያተል ኩርሲ መቅራት

ከነኚህ ውጭ ከምልክቶቹ ከ 4 በላይ ከታየቦት ሀራም ላይ በተደጋጋሚ ከመውደቅ ይጠበቁ ዘንድ ፈጥነው ያናግሩን፡፡

ቻናላችንን ለኡማው ያስተዋውቁ 👇
https://t.me/Qallbdoc

ማሰብያን የሚቆጣጠሩ የሲህር ምልክቶች ፡፡በኡስታዝ ዶክተር አቡ ፈርሃን፡፡ክፍል 1አልሃምዱሊላህ እነሆ አሏህም ብሎ እዚህ ደርሰናል፡፡ አላህ ምንግዜም አሸናፊ ነው፡፡ ከአላህም ጋር የተዋደደ የ...
31/08/2022

ማሰብያን የሚቆጣጠሩ የሲህር ምልክቶች ፡፡
በኡስታዝ ዶክተር አቡ ፈርሃን፡፡
ክፍል 1
አልሃምዱሊላህ እነሆ አሏህም ብሎ እዚህ ደርሰናል፡፡ አላህ ምንግዜም አሸናፊ ነው፡፡ ከአላህም ጋር የተዋደደ የርሱንም ጥበቃ የሚሻ ሰው በሙሉ በርሱ መንገድ ላይ ቀጥ ለጥ እስካለ ድረስ አሸናፊ ነው፡፡ እነሆ እናንተም የሚታይባችሁን ምልክቶች ቁብ በመስጠት እራሳችሁን በቁርአን አሸናፊ አድርጉ፡፡
1. የሙድ መለወጥ ወይም እጅግ በጣም ድብርትና ሞተራል የመሟት ስሜት፡፡ ይህ ስሜት ብቻ በአንድ ክፍል ውስጥ አስሮ ሊያውላቸው ይችላል፡፡
2. በአንድ ነገር ላይ ትኩረት ማድረግ አይችሉም፡፡ አንድ ነገር ላይ ሲባል ለምሳሉ በሂሳብ ላይ ወይም ወሬ ላይ እንኳ በአትኩሮት ማድመጥ አይችሉም፡፡ ወዲያው ወድያው ትኩረታቸው ከነገሮች ላይ ይነሳል፡፡
3.ቶሎ ቶሎ ይተነፍሳሉ፡፡ በአቬሬጅ የአንድ ሰው የመተንፈሻ እንቅስቃሴ ደቂቃ ውስጥ ከ 12-20 ሲሆን እነርሱ እስከ 30 ድረስ ሊተነፍሱ ይችላሉ፡፡ ይህ ህፃናትን አይጨምርም፡፡
4.አንድን ነገር ከመጠን በላይ መፍራት፡፡ ወይም እጅግ በጣም ፀፀተ መሰማት፡፡
በቃ ሰውን የማያስቀይም ነገር የሚያስቀይም ይመስላቸዋል፡፡ በሌላ ሁኔታው ደግሞ የዛሬ አምስት አመት የተናገሩህን አሁን ላይ ደውለውም ይሁን በአካል አንተ ጋር መጥተው አውፍ በለኝ ይሉሃል፡፡ ይህም ከልባቸው ልክ አሁን እንደተፈጠረ አይነት ስሜት ይሰማቸዋል፡፡ ሳምንት ወይም ጥዋት የተካሄደን ነገር አልቅሰው አፉታን ይጠይቃሉ፡፡ በሌላ በኩሉ ደግሞ ቢላ ወይ ዱላ ወይ ደግሞ አንድን ሰው አብዝተው ይፈራሉ፡፡ መድረስም መንካትም አይሹም፡፡
#ቀጣይ ምልክቶችንን ለማግኘት የቴሌ ግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ

በጅንም ይሁን በሲህ ልክፍት ለደረሰባችሁ በሙሉ፡፡ በቀልብ ዶክተር የቴሌግራም አድራሻ ቻናል ውስጥ በመግባት የኡስታዞችን ወይም የዶክተሮችን አድራሻ በመውሰድና ምልክቶቻችሁን በማስረዳት ህክምናችሁን መከታተል ትችላላችሁ፡፡

ቻናላችንን ለኡማው ያስተዋውቁ 👇
https://t.me/Qallbdoc

ህክምና ለማግኘት👇
https://t.me/freeeeeeeeeeeere

👆

ህክምና ለማግኘት👇
https://t.me/UstazulQallb

👆

አሽታሽ ሲህር፡፡ይህ ሲይዝ በቀላል መልኩ ነው ለመልቀቅ ግን እጅግ በጣም ፈታኝና አስቸጋሪ ነው፡፡ሲጀምር ምልክቶቹ፡፡1.አፌ ይሸት ይሆን፡፡ እያሉ በተደጋጋሚ መሞከር፡፡2.ሰውላይ መጥፎ ፊት ስ...
31/08/2022

አሽታሽ ሲህር፡፡
ይህ ሲይዝ በቀላል መልኩ ነው ለመልቀቅ ግን እጅግ በጣም ፈታኝና አስቸጋሪ ነው፡፡
ሲጀምር ምልክቶቹ፡፡
1.አፌ ይሸት ይሆን፡፡ እያሉ በተደጋጋሚ መሞከር፡፡
2.ሰውላይ መጥፎ ፊት ስናይ ከኛ ሽታ ጋር ማመሳሰል፡፡ ይህ የጅኑ ታክቲክ ነው፡፡ እያጠመዶት እንደሆነ አይርሱ፡፡
3.የለበሱት ሸሚዝ ቲሸርት ቀሚስ መሽተት፡፡ ይህም ገላዎን ቢያሸቱ አይሸትም ግን ልብሶ ይሸታል፡፡
4. የሌላው ሰው አፍ መሽተት፡፡ ሰው ከሩቅ ቢያወራዎትም ይሸቶታል፡፡
ሲቀጥል ከባባድ ምልክቶቹ ማለትም በጅኑ ቁጥጥር ከሆኑ ቡሃላ ያለው ምልክት
1.ሙሉ ለሙሉ ሰውነቶ መሽተት ይጀምራል ያም ለሰዎች የታወቀና የማይደበቅ ነው፡፡ ሽቶ ቢነሰንሱ እንኳ ከዚህ ሽታ አያመልጡም ፡፡
2.ብብት ጠረን እንዳለቦት ከተደጋጋሚ ሰው መስማት፡፡ ወይም ሰዎች አፍንጫቸውን መዝጋት አጠገቦ ሲደርሱ፡፡
3.የብልት ጠረን ይህ በወንዱም በሴቷም ላይ የባሰ ነው ፡፡ ምንም ቢታጠቡት ያለ አባላዘር በሽታ መሽተት ይጀምራሉ፡፡
4.የአፍ ሽታ ማስክ አድርገው ይተንፍሱ ፡፡ ይህ ሽታ ነው የርሶ እጅግ የሚሸት ሲሆን ከማስክ ውጭ ሰውን እንዴት እንደሚያውክ ይወቁ፡፡ ይህም ሲሆን ሚስዋክ እንኳ ቢይዙ መሽተቱን አያቆምም፡፡
5.ከመንጋጋ ስር ከአይን ወይ ከአፍንጫ ስር ጠጣር ድንጋይ መሳል ነገሮች መውጣት፡፡
6.የቡጉር መብዛት፡፡ እነኛም ብጉሮች ትልለቅ እየሆኑ መቸገር ፡፡
7.ከሰላትና ከእስልምና ሙሉ ለሙሉ መራቅ፡፡ በጅኑም ቁጥጥር ስር መዋል፡፡
ይህ ጅኑ ሲቆጣጠሮት የሚያሳዩ ምልክቶች ሲሆኑ ባፈጣኝ ህክምና መውሰድ ብልህነት ነው፡፡ ምክንያቱም በየሆስፒታሉ ደጃፍ ቢጠኑ ምንም አይነት መፍትሄ እንደማያገኙ አስቀድመን ለመንገር እንወዳለን፡፡ ይሁንና ከላይ ያሉት ሲጀምር አይነት ምልክቶች ካሎት ሁሌም ቢሆን ማታ ላይ ሙአወዘተይን መቅራት አያተልኩርሲ የጠቀራበትን ውሃ መጉመጥመጥ እጅግ በጣም አስፈላጊ ህክምና ነው፡፡ አላህም ከእንዲህ አይነቱ ጥቃት ይጠብቀን፡፡

👉ኡስታዞችን ለማናገር

በሴት ልጅ ፔሬድ የሚሰራ እና ሙእሚኖችን አዛ ያደረገው ሲህር እና ምልክቱክፍል 1በአላህ ዘንድ የተረገሙ ሴት ጠንቋዮች ( በዶክተር አቡ ያህያ)ይህ እውነተኛ አጭር ታሪክ ማስተማርያ ይሆነን ዘ...
30/08/2022

በሴት ልጅ ፔሬድ የሚሰራ እና ሙእሚኖችን አዛ ያደረገው ሲህር
እና ምልክቱ
ክፍል 1
በአላህ ዘንድ የተረገሙ ሴት ጠንቋዮች ( በዶክተር አቡ ያህያ)
ይህ እውነተኛ አጭር ታሪክ ማስተማርያ ይሆነን ዘንድ አላህን እለምነዋለሁ፡፡ አንድ አካባቢ ላይ ለሴቶች ደርስ የሚሰጥ ኡስታዝ ነበር፡፡ ይህን ኡስታዝ በእጅጉ እቀርበዋለሁ እወደዋለሁ እግባባዋለሁ አብሮ አደጌ የእውቀት ማእድን አንድ ላይ የተቋደሰኝ ሰው ነው፡፡ አካባቢው ግማሽ ሱዳን ግማሽ ኢትዮጵያ ድንበር ላይ ነው፡፡ እዚያ ቦታ የሄድነው በጥቆማ ነበር፡፡ ቦታው ላይ እጅግ በጣም ብዙ ሷሂሮች ያሉበት ሲሆን እማማ ገለመሌ የሚሏትም ጠንቋይ በዋናነት ህዝቡን አጥማሚ ናት፡፡ ይህን በ ፔሬድ ላይ የሚሰራ ሲህር ስለመኖሩ ከኡስታዝ አቡ ፈርሀን ጋር ባደረግነው የእውቀት ልውውጥ በባልደረባዬ ላይ የተቃጣውን ሲህር ከአላህ ጋር ልንመክተው ችለናል፡፡ ባልደረባዬ ሴቶችን በህብረት ሰብስቦ በሚያስተምርበት ወቅት ከመሃከላቸው አንዲት በእድሜ ገፋ ያለች ሴት ከርሱ ጋር ግንኙነት እንዲኖራት በጣም ጥራለች፡፡ ያም እርሱንና ባልደረቦቹን ወደ ቤቷ በመጋበዝ ምግቦችን አበላችው፡፡ ይህ ሲህር በርሱ ላይ የተነጣጠረ ነበርና ከዚያ እለት አንስቶ አቅሉ ልክ አልመጣም፡፡ ይህች እንስት በስተመጨረሻ ተውበት ታድርግ እንጂ መጀመርያውኑ ይህን ሲህር እንድታደርግ ያስገደደቻት የዚያው አካባቢ ጠንቋይ እንደነበር ልናውቅ ችለናል፡፡ አልሀምዱሊላህ ውዱ ወንድሜን ባልደረባዬን በቀልብ ዶክተር ምክንያት በተሰጠ አዝካር ልናድን በመቻላችን ደስታን ተሰምቶናል፡፡ በውህደትም ይህን ስራ አለም ላይ ያለ ምንም ጥቅም በነፃ ለመስራት ቃል በገባነው መሰረት እነሆ በስራው ላይ ሳለን የገጠመንን በፔሬድ የተሰራ ሲህር ምልክቶቹን ለመንገር እንገደዳለን፡፡
ምልክቱ
1.እጅግ በጣም ወደ አንዲት ሴት በፍቅር መሳብ… ይህች ሴት ከወንዱ ጋር በምንም ተአምር የማትመጥን የእድሜም ልዩነት ከፍ ሊል ይችላል ይሁንና ይህ ካለ ባስቸኳ እርሱን የሚቀርብ ሰው ወደ ህክምና ሊያመራለት ይገባል ተጠቂው ይህን አይገነዘብምና የእምነት ደረጃው ምንም ያህል ከፍ ቢል እንኳን፡፡
2. ሆድ መነፋት፡፡ ይህም ግዜን ያልጠበቀ ነው፡፡ ጥዋትም ምሽትም ለሊትም ሆድ ሊነፋ ይችላል፡፡ አላህ ይሰውረንና ብስናት አለው ይህም ልክ እንደገማ እንቁላል ማግሳት አለው፡፡ ከኡስታዝ አቡፈርሀን ጋር ሹራ ባደረግነው መሰረት ይህ የጨጓራ በሽታ ምልክት ሊሆን እንደሚችል ብናውቅም በሲህር ከመጠቃት በፊት የሌለ ምልክት ከሆነ የጨጓራን በሲህሩ መነካት ብቻ አመላካች ነው፡፡
3. ሽንት በሚሸኑበት ወቅት ማቃጠል፡፡ ይህም ሲባል ሽንቱ በምንም ሁኔታ መሽተት ይጀምራል፡፡ ሱሪ ሲከፈትም የብልቶቹ እንቁላሎች መሽተትና ማቃጠል ምልክት አላቸው፡፡
4. በቀን ውስጥ በተደጋጋሚ ማስታወክ፡፡ ይህ ትውኪያ ደም ሊቀላቅል ይችላል ይሁንና ምግብን ወዲያው እንደተመገቡ የሚያስታውክ ነው፡፡ በዚህ ትውኪያ ወቅት ሆድ ውስጥ ምንም ነገር ላይኖር ይችላል አልያም ገና ውሀ እንኳ ቢጠጡ ያስታውካል፡፡
5.ፍቅር መነደፍ፡፡ አዎ አሁን ይሄ ምልክቱን ለየት ያደርገዋል፡፡ ከአንድ ሰው ጋር ብቻ ከዚህ በፊት ያልነበረ ፍቅር መኖርን ያንን ሰው ካላገኙ እንደማይኖሩ ማሰብን ይጨምራል፡፡ በዚህ ወቅት ስለዚያ ሰው ሙሉ ለሙሉ መጥፎ ነገር ቢወራ እንኳን ያን ሰው በጣም መውደድ ይኖረዋልና ከሚደው ሰው ጋር ለማጣላት አለመሞከር ነው፡፡ ምክንያቱም ለናንተ ያለውን ጥላቻ ይጨምራል፡፡
6.ሽንት ቤት በሚቀመጡበት ወቅት ከመካከለኛ ተቅማጥ አንስቶ ደም እስከማስቀመጥ እረስ መድረስ፡፡
7.የምግብ ፍላጎት መቀነስ ይህም እጅግ በጣም መክሳትን ያመጣልና፡፡
8

በአንድ ቤት ውስጥ አስቸጋሪ ጅን መኖሩን በምን እናውቃለን!!ከዶ/ር አቡ ፈርሃን መጣጥፍ ላይ የተወሰደ፡፡ክፍል 1በቤት ውስጥ አዲስ ተከራይ አዲስ ገዢ አዲስ ሰፈር ውስጥ የሚገቡ ሰዎች ብሎም ...
29/08/2022

በአንድ ቤት ውስጥ አስቸጋሪ ጅን መኖሩን በምን እናውቃለን!!
ከዶ/ር አቡ ፈርሃን መጣጥፍ ላይ የተወሰደ፡፡
ክፍል 1
በቤት ውስጥ አዲስ ተከራይ አዲስ ገዢ አዲስ ሰፈር ውስጥ የሚገቡ ሰዎች ብሎም በአካባቢያው ሩቅያህ የሚሰራባቸው ሰፈሮች ላይ ይህ አይነቱ ክስተት ይፈጠራል፡፡ ኢንሻአላዋኅ ከነኚህም ውስጥ የምናያቸው ይኞራሉ…..
ምልክቶቹ፡፡
1.ብዙውን ግዜ ምሽት ላይም ይሁን ቀን ላይ ቤት ውስጥ ኮቴ አይጠፋም፡፡ ልክ ሰው ልጅ እንደሚራመደው አይነት ኮቴዎች ሊኖሩ ይችላሉ፡፡
2.ምሽት ላይ የሴት ልጅ ጩሀቶች ይኖራሉ፡፡ አደራ ይህም ከንፋስ ሊሆን ይችላልና ያን ማጣራት የግድ ነው፡፡ ንፋስ በተፈጥሮው ከሰፊ ቦታ ወደ ጠባብ ቦታ ሲወርድ ጩሀት የሚመስሉ ድምፆች ይሰማሉ፡፡ ይህን ጩሀት ለየት የሚያደርገው አልፎ አልፎ የሚመጣ ጭንቅላታችን ውስጥ ጭምር የሚሰማና በቀላሉ የሚሰማው ሰው የሚለየው ነው፡፡
3. የህፃናት እልቅሻ፡፡ ይህ የሚገርመውና በአጭሩ የሚለይ ነው፡፡ በጎረቤት ይቅርና በሰፈር ውስጥ አንድም አይነት ህፃን በማይኖርበት ስፍራ ላይ ለሊት ከእንቅልፍ የሚቀሰቅስ አይነት የህፃን ልጅ እልቅሻ እጅግም በጣም ከማስፈራቱ የተነሳ ወደ እብደት የሚስጠጋ ገጠመኝን ልናሳልፍ እንችላለን፡፡ ህፃኑ ልጅ በጣም እየጮሀ ያለቅሳል፡፡ በዛ ሰአት መውጣት እንኳ ያስፈራናል፡፡ አያተል ኩርሲን መቅራቱ ወድያው የተወደደ ነው፡፡
4. ቤት ውስጥ ሁሌም ቢሆን ጭቅጭቅ ነው፡፡ ምንም አይነት መስማማት አይፈጠርም፡፡ ነጋ ጠባ መጠላላት መራራቅ፡፡ ይህም የሲህርን አይነት ምልክቶችን ስለሚያሳይ ይበልጥ እርግጠኛ ምንሆነው ሌሎች ምልክቶች ሲኖሩና ቤት ውስጥ ሁሉም ስምምነት ሲያጡ ብቻ ነው፡፡
5. ስም ይጣራል፡፡ ይህ ሸይጧን ብዙውን ግዜ የሴቶችን ብሎም ኢማናቸው ደከም ያሉ ወንዶችን ሳይቀር በስማቸው ይጣራል፡፡ እነኚህ ሰዎች አቤት ሊሉ ሲዞሩ ማንም የለም፡፡ ይህ አይነቱ ጥሪ ከቤት ውጭም ይፈጠራል፡፡ ቤት ውስጥም ይከሰታል፡፡ ለሊትም ስማቸው ሲጠራ በርግገው አቤት ብለው የሚነሱ አሉ፡፡
6.ብቸኝነት ስሜት ቤት ውስጥ፡፡ ብዙ ሰው አለ፡፡ ጫወታ ሳቅ ሊኖር ይችላል ግን ሁሉም ብቸኝነት ይሰማዋል፡፡ ሁሉም ከሰው ጋር ሁኖ ሳይቀር ብቸኛ ነው፡፡ ውስጡ ባዶ ነው፡፡
7.ቅዝቃዜ፡፡ ይህ ቤት ወና በረዶ ይመስላል ፡፡ እሳት ቢነድበት በራሱ የሚሞቅ አይመስልም፡፡ ይህን ምክንያቱን ማወቅ አልቻልንም፡፡ ግና ጅኖች የሚደበቁበት ቤቶች በጣም በጣም ቀዝቃዛ ናቸው ብዙውን ግዜ፡፡
8. ሴትም ይሁኑ ወንዶች ባለትዳርም ይሁኑ ያላገቡ በዚህ ቤት የሚኖሩ እድሜያቸው ዝቅም ይበል ከፍ በማስተርቤሽን የተጠቁ ናቸው፡፡ እራስን በራስ የማርካት ወሲባዊ ፊልሞችን በማየት ሱስ የተጠመዱ ናቸው፡፡
ህክምናውም ቁጥር 2 ምልክቶችም በቀልብ ዶክተር ቻናል ይቀጥላል፡፡

ቻናላችንን ለኡማው ያስተዋውቁ 👇
https://t.me/Qallbdoc

ህክምና ለማግኘት👇
https://t.me/freeeeeeeeeeeere

👆

ህክምና ለማግኘት👇
https://t.me/UstazulQallb

👆

ማሰብያን የሚቆጣጠሩ የሲህር ምልክቶች ፡፡በኡስታዝ ዶክተር አቡ ፈርሃን፡፡ክፍል 2አልሃምዱሊላህ እነሆ አሏህም ብሎ እዚህ ደርሰናል፡፡ አላህ ምንግዜም አሸናፊ ነው፡፡ ከአላህም ጋር የተዋደደ የ...
25/08/2022

ማሰብያን የሚቆጣጠሩ የሲህር ምልክቶች ፡፡
በኡስታዝ ዶክተር አቡ ፈርሃን፡፡
ክፍል 2
አልሃምዱሊላህ እነሆ አሏህም ብሎ እዚህ ደርሰናል፡፡ አላህ ምንግዜም አሸናፊ ነው፡፡ ከአላህም ጋር የተዋደደ የርሱንም ጥበቃ የሚሻ ሰው በሙሉ በርሱ መንገድ ላይ ቀጥ ለጥ እስካለ ድረስ አሸናፊ ነው፡፡ እነሆ እናንተም የሚታይባችሁን ምልክቶች ቁብ በመስጠት እራሳችሁን በቁርአን አሸናፊ አድርጉ፡፡

1.የፊት መጥቆር፡፡
ፊታቸው እጅግ በጣም ከሰል ይሆናል፡፡ ይህም ለተመልካች የሆነ ችግር መኖሩን ያውቃል ይረዳል፡፡ በዚህም ወቅት እጅግ በጣም ሰው አስተያየት ለቤተሰብ ይበዛል፡፡
2. ሰው በአንዳች ነገር ሲስቅ ‹‹በኔ ነው የምትስቁት››
ብሎ ማሰብ፡፡ ሰው ሲያወራ በኔ ላይ ነው ሚመክሩት ብሎ ማሰብ ሰው ሲያዩ እኔን እየተከለታተለኝ ነው ብሎ ማሰብ፡፡ ይህ ለእብደት ሩብ ጉዳይ የቀረው ሁኔታ አስቸኳይ ወደ ሩቅያህ መጠጋት ያለበት ጉዳይ ነው፡፡
3.ከተቀመጡበት አይነሱም፡፡
ይህ ሚን አጃኢበቲሂ ታካሚ ቤታችሁ ኑሮ ብታዩ በተርግጠኝት ታውቃላችሁ፡፡ ከጸባያቸው መለዋወጥ በተጨማሪ አንድ ቦታ ላይ ተቀምጠው ሶስት ሳምንት ሊሞላቸው ይችላል፡፡ ከዚያ ቦታ ሰው ጎትቶ ካላነሳቸው አይነሱም፡፡ ሰውነታቸው ቆስሎ እስኪተላ ድረስ ከቦታቸው ላይ አይነሱም፡፡
4. የአመጋገብ ስርአታቸው መበላሸት፡፡
ይህም ምግብ እየተመገቡ በፊት የሚወዱት ምግብ ተሰርቶ አንድ ጉርሻ እንኳን አይበሉም፡፡ በተቃራኒው አፈር መብላት ቆሻሸ መብላት ካልሲ የተለበሰ መመገብን ይወዳሉ፡፡ አንዳንዴም መጥፎ ነገርን ተመግበው ልታገኟቸው ይችላሉ፡
5. የወሲብ ፍላጎት እጅግ በጣም መቀነስ፡፡
ይህ በብዙውን ግዜ በሴቶች ላይ ያይላል፡፡ ውስጣቸው ጭራሽ የወሲብ ፍላጎት ይሞታል፡፡ ባል በየግዜው ስሞታ የሞያሰማውም በዚሁ ላይ ነው፡፡
6. እላያቸው ላይ መጠቃቀም መጀመር፡፡
ይህ በመሃል በቀልድ ዝም እየተባለ ይመጣና እዚህ እስቴጅ ላይ ሲደርሱ ደህና ነበረችኮ ወደሚለው ቀልድ ይመጣል፡፡ በፈስ መልክ እላያቸው ላይ ይጸዳዳሉ፡፡ እነርሱ መበላሸታቸውን ቢያዩ እንኳ ከመለቃለቅ ይልቅ ሰው እንዳይነካቸው ያደርጋሉ፡፡ ሰው ወደነርሱ ሲቀርብ ነብር ይሆናሉ፡፡ ይህን የማያደርጉና ዝም የሚሉ ከሆነ ደግሞ የበሽታውን እጅግ ስር መስደድ አመላካች ነው፡፡

በጅንም ይሁን በሲህ ልክፍት ለደረሰባችሁ በሙሉ፡፡ በቀልብ ዶክተር የቴሌግራም አድራሻ ቻናል ውስጥ በመግባት የኡስታዞችን ወይም የዶክተሮችን አድራሻ በመውሰድና ምልክቶቻችሁን በማስረዳት ህክምናችሁን መከታተል ትችላላችሁ፡፡

ቻናላችንን ለኡማው ያስተዋውቁ 👇
https://t.me/Qallbdoc

ህክምና ለማግኘት👇
https://t.me/freeeeeeeeeeeere

👆

ህክምና ለማግኘት👇
https://t.me/UstazulQallb

👆

ባለ ሃዘንተኞቹ ጅኖች ጥቃት!ከዶክተር አቡ ፈርሃ ጥናታዊ መጣጥፍ ላይ የተወሰደ!!ብዙውን ግዜ በደማቅ ሳቅ ደስታ ውስጥ ያሳለፈ ቤተሰብ አንዴ በሚደርስበት ዱብዳ ምክንያት እንዲያ ‹‹ታምራላችሁ...
19/08/2022

ባለ ሃዘንተኞቹ ጅኖች ጥቃት!
ከዶክተር አቡ ፈርሃ ጥናታዊ መጣጥፍ ላይ የተወሰደ!!
ብዙውን ግዜ በደማቅ ሳቅ ደስታ ውስጥ ያሳለፈ ቤተሰብ አንዴ በሚደርስበት ዱብዳ ምክንያት እንዲያ ‹‹ታምራላችሁ›› የተባለን ቤተሰብ የሚበትኑ እነኚህ ባለ ሃዘንተኛ ጅኖች ለበርካታ ጤነኛ ትዳር ቤተሰብ ብሎም ወንድማማችነት እና እህትማማችነት መቃቃርን ፈጥረዋል፡፡
ቢስሚሏህ በዚያ ሰው ልጅን ባስገኘው ሰማይን ያለ ምሶሶ በገነባው በገናናው አሏህ ስም፡፡ አሏህ ያድናል ሌላው አያድንም!! በዚህ ስራ ላይ ከየአለማቱ ኡማውን ለማገልገል የተሰባሰባችሁ ባልደረቦቼ ወንድሞቼ እህቶቼ በሙሉ እንኳን ደስ ያላችሁ፡፡ በዚህች ዘላቂ ባልሆነችው ዱንያ ውስጥ ስንሰባሰብ ለሰዎች መፍትሄን አፈላላጊ እንጂ ለሰዎች አዛ አድርጎ አላሰባሰበንም፡፡ ምንኛ ያማረ እድል ነው!! ይህን እድል ብዙሃኑ አያገኙትም ! ለማግኘትም ቢሞክሩ አይችሉም!! ምክንያቱም መነሻ አላማቸው ኡማውን እውን ለመርዳት አይደለምና!! ወይ እውቅናን ፈልገው (እከሌማ እየተባሉ እንዲወራላቸው፣ወይ ምቀኝነት ፣ አልያም መነሻቸው ብር ለመሰብሰብ ኡማውን ለመበዝበዝ ነው) ታድያ አስታውሱ የኛ መነሻ አንድና አንድ ነው ያም ‹‹ጥቅማችን ጀነት ነው! ጥቅማችን የአላህ ውዴታ ነው የላከንም አላህ ነው እኛም የርሱ ባሮች ሙስሊሞች ነን›› ምንኛ ያማረ አላማ ነው!!
እስኪ ባለ ሃዘንተኛ ጅኖች ማለት ምን አይነት ናቸው! በጥቂቱ ካልን ኋላ ስለ ምልክቶቹ እንወያያለን፡፡ በረጅም ግዜ የህክምና ጥናት ባገኘነው እውቀት እኔም ሆንኩ ባልደረቦቼ በተደጋጋሚ ባደረግነው ጥናት ላይ አንድ ያገኘነው እውነታ እነኚህ ባለሃዘንተኛ ጅኖች የሰውን ልጅ ሲያጠቁ የሚፈጥሩት ስሜት የተለየ ነው፡፡ ለዚያም ነው ባለ ሃዘንተኛ ስንል ስም ያወጣንላቸው፡፡ እነርሱ መሆናቸውን ከስር ባሉ ምልክቶች ከለየን ኋላ በቀጥታ ህክምናውን ለማድረግ ቀላል ስለሚሆን ይህም ጠቃሚ ነው!!
ምልክቶቹ !!
ክፍል 2
8. የእንቅልፍ ሁኔታቸውን በተመለከተ በጥናቱ ላይ የተለያዩ ባህሪ ይኑራቸው እንጂ እኛ ይህ የከፋ ደረጃ ነው ብለን እንድንለይ ያስቻለን ባህሪያቸው መሃል እንቅልፍ አልባ ናቸው ወይ ደግሞ እንቅልፍ ካሉ አይጠግቡም፡፡ ሃያ አራት ሰአት ከእንቅልፍ መነሳት አይፈልጉም አልጋ ስር ቢደበቁ ደስ ይላቸዋል፡፡ አልያም ለሊቱን ሙሉ ሲገላበጡ ያድራሉ እንቅልፍ የሚባል የለም፡፡
9. በብዛት ወንዶች ላይ ቁጡነት ባህሪ እረፍት የለሽ ይሆናሉ፡፡ ወደው ግን አይደለም፡፡ የጠፋ ማንነታቸውን ለመመለስ የሚደርጉት ግብግብ ነው፡፡ እራሳቸውን በጣም ቢዚ በማድረግ ከጭንቀት ከፍርሃት ደስ ከማይል ስሜት ለማውጣት ይጥራሉ ግና አይቻላቸውም፡፡ ቶሎ ሆድ ይብሳቸዋል፡፡ እንዲህ ሆኜ እንዲህ አድርጌ የሚለው ግጥም ሁሌም የነርሱ ብቻ ነው፡፡
10.በወሲብ አለም ዙርያ ፍላጎት ማጣት፡፡ ይህ ብዙውን ግዜ ባለትዳሮች ላይ የሚፈጠር ችግር ነው፡፡ ምንም አይነት የወሲብ ፍላጎት የላቸውም፡፡ ቅፍፍ ነው የሚላቸው፡፡ መደሰቱን መጫወቱን ጠልተው አይደለም ግና ውስጣቸው ደስ አይለውም፡፡ ብዙም ስራ መስሎ ይታያቸዋል፡፡
11.ከዚህ ፊት የተጠቀሱ ስሜቶች መሰማት ከቆዩ ኋላ ደግሞ ሰውነታቸው ህመምን መፍጠር ይጀምራል፡፡ ለምሳሌ ያህል የመገጣጠምያ ህመሞች የኩላሊት ውጋት እና የመሳሰሉት ህመሞች ይጀምራሉ፡፡
12.እራሳቸውን ማግለል ይፈልጋሉ፡፡ ይህ ፀባያቸው በጣም አስቸጋሪ ባህሪ ነው፡፡ ማንም ጋር መቀላቀል አይፈልጉም፡፡ ብዙውን ግዜ ባል ሚስቱን ጥሎ ይጠፋል ወይ ደግሞ ሚስት ባሏን ጥላ ትጠፋለች፡፡ ይህ ባህሪ በጣም አስቸጋሪ ሁኔታ ላይ ይጥላቸዋል፡፡
፡፡ አሁንም ከላይ ከተገለፁት ምልክቶች ውስጥ ከ 2 እና ከሶስት በላይ ካለባችሁ በአፋጣኝ ወደ ቻናሉ በማምራት ኡስታዞችን ዶክተሮችን ማናገር፡፡

ሙሉዉን ከቴሌ ግራም ቻናላችን ያገኙታል
ቻናላችንን ለኡማው ያስተዋውቁ 👇
https://t.me/Qallbdoc

ህክምና ለማግኘት👇
https://t.me/freeeeeeeeeeeere

👆

ህክምና ለማግኘት👇
https://t.me/UstazulQallb

👆

በዶክተር አቡ ፈርሀንየትዳር አሳጭ ጂን ሲህር (ይህ ጅን ጥቃት የደረሰበት ሰው ትዳር አይሳካለትም)ጅኑ ሁለት አማራጭ አለው፡፡ ሀ. የመጀመርያው አማራጭ አንዲትን ሴት ከተፀናወተ ውስጧ በመሆን...
18/08/2022

በዶክተር አቡ ፈርሀን

የትዳር አሳጭ ጂን ሲህር (ይህ ጅን ጥቃት የደረሰበት ሰው ትዳር አይሳካለትም)

ጅኑ ሁለት አማራጭ አለው፡፡

ሀ. የመጀመርያው አማራጭ አንዲትን ሴት ከተፀናወተ ውስጧ በመሆን የትዳር ጥያቄ ሲመጣላት እንዳይስማማት እንድትታመም እንድትጠላ በማድረግ ትዳሩን እምቢ እንድትል ያስደርጋል

ለ. ይህ ጅን በሴቷ ሰውነት ውስጥ መግባት ካልቻለ ደግሞ የማመሳሰል ቴክኒክ በመጠቀም ልጅቷን ከውጭ በመሆን ለትዳር የሚመጡ ወንዶች በሙሉ ሴቷ ጋር ተስማምተው በስተመጨረሻው ሰአት ወንድ ሆና እንድትታያቸው እንዳትስማማቸው ያደርጋል፡፡ ይህንም በ መጪው ባል ጆሮ ላይ ድግምትን በመድገም ያከናውነዋል፡፡

እጅግ በጣም ጠንካራ የሆነ ሲህር ከሆነ ደግሞ የሴቷን እጅ ጠያቂ የሆነ ሰው የሴቷ ቤተሰቦች ቤት ለሽምግልና የመጣ ወቅት በእጅጉ ይጨንቀዋል ውጣ ውጣ ይለዋል፡፡ እስር ቤት የገባ ያክል ይሰማዋል፡፡ ጅኑም የተቻለውን ድግምት ሙሉ በሙሉ በመጠቀም ጠያቂውን አሸማቅቆ ከቤቱ በማስወጣት ሁለተኛ እንዳይመለስ ያደርገዋል፡፡

ምልክቶቹ

1.አልፎ አልፎ የሚመጣ እራስ ምታት በመድሀኒት እንኳን ሊፈታ አይችልም፡፡

2.ልብ አካባቢ መጨናነቅ እፍን ማድረግ በተለይ ከአስር ሰላት ቡሀላ እና እስከ እኩለ ለሊት ባለው ግዜያት ውስጥ፡፡

3.ጠያቂው ሴቷን ሊጠይቅ በመጣ ሰአት በእጅጉ ወንድ መስላው ወይ ደግሞ አስቀይማው ይመለከታል፡፡

4.ታማሚዋ ጭንቅላቷ ወና ይሆናል ነገሮችን ማስታወስ ይሳናታል፡፡

5.በእንቅልፍ ወቅት ልብ ጭንቅ ማለት መጨናነቅ እና መፍራት

6.አልፎ አልፎ የሆድ ህመም

7.በታችኛው የወገብ ስፍራ ህመም መሰማት፡፡

ይህ በራሶ ምንም የሚያደርጉት ነገር አይኖርም ፈጥነው ያናግሩንና የሩቃ ህክምናውን ይጀምሩ፡፡

ህክምና ለማግኘት👇
https://t.me/freeeeeeeeeeeere

👆

ህክምና ለማግኘት👇
https://t.me/UstazulQallb

የወሲብ ባርነት ሲህር!!ሴቷን የወሲብ እስረኛ ለማድረግ የሚሰሩ ሲህሮች (ጥንቆላዎች) ምልክቶችበዶክተር ኡሙ ሚስባህ!አሏህ ይጠብቀን በማለት ለመጀመር እወዳለሁ፡፡ ብዙ ፈተናዎች አሉብን እነኛ ...
17/08/2022

የወሲብ ባርነት ሲህር!!
ሴቷን የወሲብ እስረኛ ለማድረግ የሚሰሩ ሲህሮች (ጥንቆላዎች) ምልክቶች
በዶክተር ኡሙ ሚስባህ!
አሏህ ይጠብቀን በማለት ለመጀመር እወዳለሁ፡፡ ብዙ ፈተናዎች አሉብን እነኛ ፈተናዎችን የምንወጣው በእውቀት የተመሰረተ ህክምናን ስናገኝ ብቻ እንጂ እንዲህ ያለ ችግር ያለባቸው ሴት እህቶች ብዙዎቹ ያክመኛል ብለው የሚጠጉት ሰው ሳይቀር ይጠቀማቸዋል፡፡ ሲህር እጅግም አስፈሪ አስጠሊታ ነገር ነው፡፡ ሴትን ልጅ ለርካሽ አላማ የሚጠቀም ወንድ ለዚያም አላማ እንድትውል የሚያደርግ ወንድ በሙሉ የአላህ እርግማን ይውረድበት ፡፡ እህት እናት ሚስት ልጅ መሆን የምትችለዋን በጥንካሬ ኢስላምን መጠበቅ የምትችለዋን ሴት ለእኩይ ተግባር ተሳታፊ ለማድረግ የሚሸርቡ ሷሂሮች ጠንቋዮችን አላህ ባሉበት ያውድማቸው፡፡
ቢስሚሏህ
አለም ለየቅል ነች፡፡ አንዱ ለዱንያ ለኸምር ለሴራ ለወንጀል ሌላውን ሲጠራ አንዱ ደግሞ ለኸይር ስራ እንሰባሰብ ሲል ከየአለማቱ ዳኢዎችን የሩቅያህ አሊሞችን ይጠራል፡፡ እነሆ የሁልግዜም ዱአዬ ለኡስታዝ ዶክተር አቡ ፈርሃን ይሁን አላህም ስራውን ይውደድለትና ባመቻቸልን መስመር ላይ ተሰባሰብን፡፡ አልሃምዱሊላህ፡፡
በዛሬው ርእስ ላይ ለሁለት ክፍል በመከፋፈለም ምልቶቻቸውን ከነማብራሪያዎቻቸው ከኡስታዝ አቡ ፈርሃን መጣጥፍ ላይ በማጣቀስ ኡማውን ለማስተማር ወሰንኩ፡፡ እነሆ የሴትን ችግር ሴት ይበልጥ ትረዳዋለችና እህቴ እባክሽን ልብ ሰጥተሸ አድምጪኝ የማንም መጠቀምያ እንዳትሆኝ!!
ምልክቶቹ

ክፍል 2
4.ማስተርቤሽን (እራስን በራስ ማርካት)!!
በዚህ ላይ ሁክም ልሰጥ አይደለም የመጣሁት እይታው እንደየ አሊም ነኝ ባዩ ሙፍቲሁ ይለያያል፡፡ እኛ ከጤና አንፃር ብቻ ለማብራራ እንሞክራለን፡፡ ይህ አይነቱ ስራ ቀጣይ ባንቺ ላይ የሚከሰቱ ምልክቶች ናቸው፡፡ እራስን ከመነካካት አልፎ ብልት ውስጥ ግኡዝ ነገራትን መጨመር፡፡ የተለያዩ ወንዶችን መመኘት ፡፡ ይህ እጅግም አስፈሪ ሁኔታ ውስጥ ይከትሻል እራስሽን መቆጣጠር እንደማትችይ የምታውቂው ይሄኔ ነው፡፡ ያም ማለት በቀን ውስጥ እስከ 70 ግዜ እራሳቸው የሚያረኩ ሰዎች አንስቶ በትንሹ በቀን ውስጥ ከ 1 እስከ 3 ማስተርቤሽን የሚያደርጉ ታካሚዎች ይገጥሙናል፡፡ ይህን ተግባር በሩቅያህ ህክምና ብቻ ሳይሆን በሳይኮሎጂያዊ ህክምና የተደገፈ መሆን ይገባዋል፡፡ ይህን ማውራት ኖርማል ባልሆነበት አካባቢና ቦታ ላይ ያሉ ሴቶች በቃኝ ይህ ስራ ከሲህር ጋር አንድ ነው እራሴን መቆጣጠር አልቻልኩም ሲሉ ይቀርቡናል፡፡ በድጋሚ ለእነኚህ ልባም ሴቶች አሁንም ክብራችን ላቅ ያለ ነው፡፡ ይህ ማስተርቤሽን ሲቀጥል ወደ መጥፎ የጤና እክል ውስጥ ይከተናል፡፡ የአእምሮ መታወክ ደግሞ በሲህር ምክንያት ለተጸናወተን ጅን ሙሉ ለሙሉ እጅ እንድንሰጥ ያደርገናል፡፡ ለዚህም ሩቅያህ ብቸኛ አማራጭ ነው፡፡ ሩቅያህ ሲባል ሙአወዘተይን መቅራት አያተል ኩርሲን መቅራት ብቻ የሚመስላቸው ከእውቀት ነፃ የሆኑ ሰዎች የሚሰጡሽ ጥራዝ ነጠቅ ምክር ሊኖር ይችላል ያም ሲባል ተይው ይተውሻል ሃራም ነው ስራውን አቁሚ ብለው የሚፈርዱብሽ ውስጥሽን ሳይረዱ ባንቺ ላየ ጣት ለመቀሰር የሚቀናቸው ጃሂሎችም አሉና ከነርሱ ራቂ የምንለው በምክንያት ነው፡፡ አንድ ሰው ወደ አንድ ሃኪም ነኝ ባይ ግለሰብ መጥቶ ‹‹በጣም ይጨንቀኛል እፈራለሁ ምን ላድረግ ›› ብሎ ሲጠይቅ ይሀው ሃኪም ነኝ ባይ ግለሰብ..‹‹እንዴ ሞኝ ነህ እንዴ አትጨነቅ መጨነቅ አይጠቅምም አትፍራ ጀግና ሁን ›› እንዳለው ይሄ ችግር አለብኝ ብለሽ ስትቀርቢ ከመረዳት ይልቅ ያልጠፋሽን ሃቅ አመላክተው እራሳቸውን በጀብደኞች ሂሳብ ከሚያዩና ምስጢርሽን ከሚነዙ ሰዎች ተቆጠቢ አደራ…አደራ…አደራ፡፡
5. ልቅ የሆኑ ግንኙነቶች!!
ይህን በሁለት መልኩ ከፍለን ማየት ይኖርብናል፡፡ አዎ አንቺ እህቴ ከላይ ያሉትን ምልክቶች በሙሉ አልፈሻል፡፡ ከዚህ ኋላ ዘካሪ መካሪ እንኳ ቢመጣ መላቀቅ አልቻልኩም በሚል አባዜ ጥልቀት ውርደት ውስጥ ገብተሻል፡፡ ውርደት ሲባል ለራስሽ ለህሊናሽ እንጂ እኛ ዘንድ እንደ ዳይመንድ የምትታይ ሙስሊም እህታችን ነሽ እኛ ዘንድ ክብር አለሽ አሏህ ዘንድ ክብር አለሽ ምክንያቱም አሏህ የሰውን ልጅ ቀልብ ገለባባጭ ጌታ ነውና፡፡
ሀ. የመቀመጫ ግንኙነቶች ከትዳር ውጭ፡፡ ማለትም በፊንጢጣ ወሲብ ማድረግን የሚወተውት ሲህር፡፡ ይህ ግንኙነት ከትዳር ውጭ ነው፡፡ ትዳር የለሽም ግን በወሲብ ወቅት ከተፈቀደው ውጭ የሆኑ ግንኙነቶችንም ትጠቀምያለሽ፡፡ ይህ በሩቅያህ ኡስታዞች እ ዶክተሮች ዘንድ አስቸጋሪው የጅን ጥቃት መሆኑ ይታመንበታል፡፡ ይህ ከወሲብ አልፎ ሱስ ሁኗል፡፡ ይህን ለመተው ካንቺ የሚጠበቀው ጥርስሽን ነክሰሽ ህክምና መጀመር ብቻ ነው፡፡ በዚህ ግዜ ውስጥሽ አይጠቅመኝም ተመልሼ ያው ነኝ ሊል ይችላል፡፡ ግና በፍፁም ተመልሰሽ ያው አትሆኝም አትሞኚ ይህ የጅኒው መልእክት ነው፡፡ ይህ አይነቱን ሲህር ሌሎች በሴቶች ላይ ሲሰሩ ብዙውን ግዜ ሴቶቹን መጀመርያ ወጥመድ ውስጥ ከጣሏቸው ኋላ ነው፡፡ ሴቷ በመሃል ተነስታ ታለቅሳለች ታብዳለች ትጎዳለች ግን ደግሞ መልሳ ያው ልትሆንም ትችላለች፡፡ እህቴ አንቺ የወንዶች መጫወቻ ለመሆን የቀረሽ ወራቶች ናቸው፡፡ በህክምና ወቅት የሚፈጠሩ አጂብ የሚያሰኙ ታሪኮች አሉ ኢንሻአላህ እሱን ሌላ ግዜ በስፋት እንዘረዝራቸዋል፡፡
ለ. የመቀመጫ ግንኙነቶች በትዳር ውስጥ፡፡ ኢስላም ይህን አይነቱን ልቅ ግንኙነት አይደግፍም ይሁንና በባልና ሚስት መካከል ሰላማዊ ሁኖ የሚኖሩ ጅኖች አሉ እነኚህ ጅኖች ሁለቱንም ሀሳባቸውን በመጥፎ መለወጥ የሚችሉ ናቸው፡፡ብዙዎች በባሎቻቸው የሚደፈሩ ሚስቶች ሲሆኑ የተቀሩት ደግሞ በራሳቸው ተነሳሽነት ይህን የሚፈፅሙ እንስቶች ናቸው፡፡ ይህ የተጠላ ተግባር ብዙውን ግዜ በህክምና ላይ እንዳጋጠመን ከሆነ ተንቀሳቃሽ ወሲብ ቀስቃሽ ፊልሞችን በማየት የሚጠመዱ እንስቶች በዚህ ዙርያ ላይ እንደሚውሉ የተረጋገጠ ነው፡፡ እናም የሩቅያህ ዶክተሮች ያለ ሲህር በዚህ የትዳር ግንኙነት ወቅት በጅን ጥቃት ብቻ ይህን እንዲፈፅሙ ይገደዳሉ፡፡ በጥልቀት ጉዳዩን ለመረዳት በሚያዳግት መልኩ እንዲህ ያሉ ባለትዳሮች ሩቅያህ ህክምና ከጀመሩ ኋላ ተውበት አድርገው ይመለሳሉ፡፡
ይቀጥላል…
ህክምናውንም የቀልብ ዶክተር ቻናል ላይ ያገኙታል፡፡

ቻናላችንን ለኡማው ያስተዋውቁ 👇
https://t.me/Qallbdoc

ህክምና ለማግኘት👇
https://t.me/freeeeeeeeeeeere

👆

ህክምና ለማግኘት👇
https://t.me/UstazulQallb

👆

Address

جدة, السعودية
Jeddah
22233

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when የአፊያዎ ምርጫ በቀልብ ዶክተር posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share

Share on Facebook Share on Twitter Share on LinkedIn
Share on Pinterest Share on Reddit Share via Email
Share on WhatsApp Share on Instagram Share on Telegram