30/09/2025
መስተፋቅር ሴቶች ላይ
ይህ ሲህር የሚሰራው ወንዱ ሴቷን ለማግኘት በርሱ ፍቅር ለማንበርከክ ካለው ፍላጎት አንፃረ ሲሆን ይህም በእጅጉ ለሴቷ ፈታኝና ከባድ ነው፡፡ የሚሰሩባቸው ሂደቶችን ተከትለው እንገት የሴቷን እጅ በመንካት ሴቷ ላይ በመትፋት ብሎም ሴቶን ስም በመጥራት ይህን ሲህር ይተገብሩታል፡፡ አላህም ይጠብቀን፡፡
ምልክቶቹ
1.ሴቷ ከዚህ ወንድ ሸሽታ ሌላ ወንድ ብታገባ እራሱ አልቅሺ አልቅሺ ሙቺ ሙቺ ይላታል፡፡ የአሁኑን ባሏን ብትወደብው እንድትጠላው ያደርጋታል፡፡
2.በህልሟ ስለዛ ወንድ ብቻ ማሰብ ትጀምራለች፡፡ ስሙ ሲጠራ ያስደነግጣታል የቀንም የማታም ህልሟ እሱን ማግኘት ነው፡፡
3.ጥርሷን በጣም ታፋጫለች ይህም በተኛችበት ጥርስ ጥርሶቿን መብላት ትጀምራለች፡፡
4.ከኢማን ከሰላት ከቂርአት ትሸሻለች፡፡ ይህ ሰው ቢርቃት እንኳ ካላገባሁት ሙቼ እገኛለሁ ትላለች፡፡
5.ይህ ሲህር ሲጀምር ሰውየውን መፍራት የምትጀምር ሲሆን ያም ፍራቻ ወደ ወሲባዊ ፍቅር ተለዋጭ ነው፡፡
6.ጅኖችም በዚህች ሴት አናት ላይ ያረፉ ሲሆኑ ይህች ሴት አብዛኛውን ግዜ የራስ ህመም አላት በመድሃኒት የማይፈታ፡፡
7.ብቻን ማልቀስ ብቸኝነት መሰማት ከሰዎች መሀል ውስጥ ሁና ብቸኝነት ይሰማታል፡፡ ይህም ስለርሱ ላታስብ ትችላለች ግና ብቸኝነቱ ከባድ ነው፡፡
ከዚህም በላይ ከሀያ ያላነሱ ምልክቶችን የምታሳይ ሲሆን ይህ ምልክት የሚታይባት ሴት በአፋጣኝ የሩቅያ ህክምና ልታደርግ ሲገባት ይህን ህክምና በግል ለማከናወን ይረዳት ዘንድ በመጀመርያ ዳእዋዎችን ማዳመጥ ስለ ቀብር ስለ አላህ ውዴታ የሚያስተምሩ ዳእዋዎችን መከታተል፡፡ በቀጣይም አያተል ኩርሲን መቅራት ያም ልጁን ስታስብ መቅራቱ ይረዳታል፡፡ በመቀጠልም ውዱእን መጠበቅ ከውዱእ ውጭ አለመሆንና የሰሃቦችን ታሪኮች ማንበብ ስሜት ቀስቃሽ ከሆኑ ነገሮች በሙሉ ልትርቅ ይገባታል፡፡ እንዲህ አይነት ነገር እንዳይገጥማችሁም ምሽት ላይ በአዳበነውም መሰረት እንቅልፍን መተኛት ጥዋትም በሚነሱበት ወቅት አያተል ኩርሲን ማንበብ ተገቢ ነው፡፡ ይህ ሳይሆን ቢቀርና ህክምናው በግል ቢከብድ ብሎም ከላይ ከተጠቀሱት ምልክቶች ውስጥ በዋናነት ከሶስት በላይ ቢገኝቦት ባፋጣኝ የሩቅያ ህክምናን ያግኙ፡፡
ቻናላችንን ለኡማው ያስተዋውቁ 👇
https://t.me/Qallbdoc
ህክምና ለማግኘት👇
https://t.me/freeeeeeeeeeeere
👆
ህክምና ለማግኘት👇
https://t.me/UstazulQallb
👆