01/20/2026
የአደባባይ በዓላት ድንገተኛ ሕክምና አገልግሎት ክፍል በጥምቀት በዓል ላይ አገልግሎት ሰጠ።
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ሕክምና ማኅበር የአደባባይ በዓላት ድንገተኛ ሕክምና አገልግሎት ክፍል በየዓመቱ እንደሚያደርገው በጥምቀት በዓል ላይ በመገኘት አገልግሎት ለመስጠት ችሏል።
በዚህም አገልግሎት ከተለያዩ ስፔሺያሊቲ የተውጣጡ ባለሙያዎች ተሳትፈዋል። የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ሕክምና ማኅበር በዕለቱ በበጎ አገልግሎት ለተሳተፉ የጤና ባለሙያዎች የላቀ ምስጋና ለማቅረብ ይወዳል።
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ሕክምና ማኅበር የአደባባይ በዓላት ድንገተኛ ሕክምና አገልግሎት ክፍል የአደባባይ በዓላት ላይ እና ህዝብ በሚበዛባቸው ክስተቶች (Public events) ላይ የድንገተኛ ሕክምና አገልግሎት መስጠት ከጀመረ 5 ዓመታትን ያስቆጠረ ሲሆን በዚህም አገልግሎት ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው ባለሙያዎች ተሳትፈዋል ብዙዎችም የአገልግሎቱ ተጠቃሚ ለመሆን ችለዋል።
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ሕክምና ማኅበር ለሁሉም በሁሉም!
# eotma_for_all_by_all