Global Oromo Health Professionals

Global  Oromo Health Professionals Global Oromo Health Professionals-for peace & social Responsibility is a Nonprofit Organization to help the Displaced Oromos with in the Ethiopia.

03/14/2022

☀️
Yooyyaa!
Dilbata ganamaan walitti deebine.
Akkuma yeroo hundaa goonu mammaaksaan eegalleerra.
''Akka duriifi harka xuriitti hin hafan,'' jedha. Maal jechuudha?
Nagaan oolaa.

09/13/2019

ሞባይል ስልክ የሚያመጣብን ጣጣ

(በዳንኤል አማረ @ኢትዮጤና)

የአይን ማኩላር እርጅና እስከ ቅርብ ጊዜ ድረስ እድሜአቸው በገፋ ሰዎች ላይ ብቻ ነበር የሚታየው።አሁን ግን ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ከ30 እስከ 40 አመት የሆኑ ወጣቶች ሁሉ ‘ማኩላር ዲጀኔሬሽን’ የተባለና ወደ አይነ ስውርነት የሚያደርስ ሕመም እየተጠናወታቸው መጥተዋል ይላሉ የሲንጋፖር የአይን ሕክምና ሆስፒታል ዋና ዳይሬክተር ፕሮፌሰር ሊሊ።

ይሄም የሆነበት ማክንያት ብዙ ሰዎች ማታ መብራት ካጠፉ በኋላ ተንቀሳቃሽ ስልክ እየከፈቱ ያያሉ።በጨለማ ውስጥ ወይም ጨለም ባለ አካባቢ የሞባይል ስልክን ለ30
ደቂቃ እንኳን መጠቀም መታረም የማይችል አደጋ ውስጥ የሚከት ነው።

ሕመሙም ካታራክት አይነት ሕመም ማስከተል ብቻ ሳይሆን የአይን ካንሰርም ያስከትላል። ይህ ደግሞ መድሃኒት የሌለው በመሆኑ አይን ሲጠፋ ብቻ ቁጭ ብሎ መመልከት ነው
ይላሉ ሃኪሙ።ይህን መልዕክት ያስተላለፉት 254 የሚሆኑ የአይን ስፔሻሊት ሃኪሞች አንድ ላይ በመሆን ነው።

ብዙ ሰዎች ማታ አልጋቸው ላይ ሆነው መብራት አጥፍተው ወይም ፈዘዝ ባለ መብራት ተንቀሳቃሽ ስልካቸውን እንደሚጠቀሙ ስለምናውቅ አደራ፣ አደራ፣ ራሳችሁን ከማይድን ሕመም ጠብቁ ብለዋል።

መልካም ጤንነት!!

ለበለጠ የጤና መረጃ ይህን ገጽ ላይክ ያድርጉ
www.facebook.com/EthioTena

08/09/2018



ከእለታት አንድ ቀን አንዲት በጣም ውሀ የተጠማች እርጉዝ ሴት በጉዟዋ ላይ እያለች ምንም የውሀ ምንጭ በሌለበት አካባቢ ከአንድ ዛፍ ስር ተቀምጣ ነበር፡፡
በውሀ ጥም ምክንያት ጉሮሮዋ ደርቋል፡፡ድንገት ግን ቀስ በቀስ ከዛፉ ቅጠል የሚንጠባጠብ ውሀ አየችና ለጉዟ ይዛችው ከነበረ ሻንጣ ውስጥ አንድ የውሀ መጠጫ ብርጭቆ አውጥታ የሚንጠባጠበውን ውሀ ማጠራቀም ጀመረች፡፡
የተጠራቀመው ውሀ የብርጭቆው ግማሽ አካባቢ ደረሰና ለመጠጣት ስትሞክር ድንገት ሳታስበው አንዲት ወፍ መጥታ ልትጠጣ ስትል ሴትዮዋ እጅ ላይ የነበረው ብርጭቆ ወድቆ ተሰበረና ውሀው ፈሰሰ፡፡
በዚህ የተነሳ ሴትዮዋ በጣም ተናደደች፤ወፏንም ከዛፉ ካባረረች በሇላ እንደገና አዲስ ብርጭቆ አውጥታ የሚንጠባጠበውን ውሀ ስታጠራቅም አሁንም ወፏ መጥታ ለመጠጣት ስትል ውሀውን አፈሰሰችው፡፡ እርጉዟ ሴትዮ አሁንም በጣም ተናዳ ድንጋይ አንስታ ወፏን ለመግደል ሞክራ አልተሳካላትም፡፡ይህ ድርጊት ለሦስተኛ ጊዜ ተፈፀመ፡፡ መጨረሻ ላይ ሴትዮዋ ቀስ ብላ ወፊቷ ሳትነቃባት ድንጋይ ወርውራ ገደለቻት፡፡
ከዚህ በሇላ ውሀውም አለቀና ሴትዮዋም ወደ ነበረችበት ተመልሳ ስትቀመጥ በጣም ትልቅ እና ረዥም እባብ ከዛፋ ቁልቁል ወደሷ ሲመጣባት አይታ ሮጣ አመለጠች፡፡ በዚህ ጊዜ ከዛፉ ይንጠባጠብ የነበረ የእባቡ መርዝ እንጂ ውሀ አለመሆኑ ስላወቀች ህይወቷን ያተረፈችላትን ወፍ በመግደሏ በጣም አዘነች ከልቧም ተፀፀተች፡፡.......
ወዳጆቼ አንዳንድ ጊዜ ፈጣሪ ለኛ ልክ እንደዚህች ወፍ ነው፡፡መርዙ መቼ እንደምንጠጣው ያውቃል ይሁን እንጂ መርዙ ከመጠጣት
ሲያድነን፤እኛ ግን የገጠመንን ትንሽ ችግር በማየት ብቻ እናማርረዋለን(እንወቅሰዋለን)፡፡
ነገር ግን የሆነውን፣እየሆነ ያለውን እና የሚሆነውን ሁሉ ለበጎ መሆኑን ማወቅ ይገባናል፡፡

ስለዚህ ምንም ሳናማርር እርሱን እንከተለው፤በፍፁም አያሳፍረንም፡፡
እኛም ካጋጠመን አንድ ችግር ይልቅ ያሉንን ብዙ በረከቶች እያየን አመስጋኝ እንሁን።.....
መልእክቱን ከወደዳችሁት Like~share

ቶሎ ቶሎ እንዲደርስወ ፔጁን ሼር ላይክ ያርጉት

✔ 250,000 ላይክ ደርሰናል

ስለ ፔጁ አስተያየት ይስጡን ??

08/08/2018
03/12/2018

Address

Minneapolis, MN
55454

Telephone

+19524561248

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Global Oromo Health Professionals posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share

Share on Facebook Share on Twitter Share on LinkedIn
Share on Pinterest Share on Reddit Share via Email
Share on WhatsApp Share on Instagram Share on Telegram