Doctor Tena

Doctor Tena ጠቃሚ የጤና ምክሮች!
(1)

ቦርጭን እንዴት እናጥፋ??Dr. Tena - Bethel🖐🖐🖐  ሰላም የዶክተር ጤና ቤተሰቦች!!  🖐🖐🖐ዛሬ የብዙዎች ችግር ስለሆነው ቦርጭ የማጥፊያ መንገዶች በአጭሩ እናያለን፡፡ቦርጭ ምንድነው?...
08/26/2020

ቦርጭን እንዴት እናጥፋ??
Dr. Tena - Bethel

🖐🖐🖐 ሰላም የዶክተር ጤና ቤተሰቦች!! 🖐🖐🖐

ዛሬ የብዙዎች ችግር ስለሆነው ቦርጭ የማጥፊያ መንገዶች በአጭሩ እናያለን፡፡

ቦርጭ ምንድነው??
ቦርጭ እጅግ በጤና ረገድ አሳሳቢ ጉዳይ ነው፡፡ ይህ አይነት ስብ የውስጥ አካት ስብ ነው፡፡ ቦርጭ ለስካር በሽታ፣ ለልብ በሽታ እንዲሁም ለሌሎች በሽታዎች አጋላጭ ያደርጋል፡፡

ቦርጭን እንዴት ማጥፋት ይቻላል??
1. በፋይበር የበለጸጉ ምግቦችን ማዘውተር

2. መጥፎ ስብ አለመብላት

3. ብዙ አልኮል አለመጠጣት

4. በፕሮቲን የበለጸጉ ምግቦችን መውሰድ

5. ጭንቀት እና ውጥረትን መቀነስ

6. የሚወስዱትን የስካር መጠን መቀነስ

7. እንቅስቃሴ ማዘውተር

8. ካርቦሃይድሬት ያላቸውን ምግቦች አለመውሰድ

9. የኮኮናት ወይም የወይራ ዘይት መጠቀም

10. ክብደት ማንሳት

11. ጣፋጭ የበዛበት መጠጥ አለመውሰድ

12. በቂ እንቅልፍ መጠጣት

13. አመጋገቦን እና እንቅስቃሴዎትን መመዝገብ

14. አሳ በየሳምንቱ መብላት

15. የፍራፍሬ ጁስ አለማብዛት

16. ምግቦት ላይ ፖም ያለበት ኮምጣጤ መጨመር

17. ፕሮባዮቲክ ያለበትን ምግብ ማዘውተር

18. ለረጅም ሰዓታት መፆም

19. አረንÕዴ ሻይ መጠጣት

20. የኑሮ ዘይቤዎን ይቀይሩ

ይህንን መረጃ ሼር በማድረግ ለሌሎች ያጋሩ!!


ተጨማሪ የጤና መረጃ እንዲደርሶ፦

የዶክተር ጤና ቴሌግራም ገፅ

t.me/DoctorTena

የዶክተር ጤና ፌስቡክ ገፅ፦

fb.com/DoctorTenaEthiopia

ቫይታሚን ኤ!! (Vitamin A)Dr. Tena - BethelAugust 19, 2020🖐🖐🖐  ሰላም የዶክተር ጤና ቤተሰቦች!!  🖐🖐🖐እንደምን ሰነበታችሁ?? በአዲስ መልኩ እናንተን ይጠቅማሉ የ...
08/19/2020

ቫይታሚን ኤ!! (Vitamin A)
Dr. Tena - BethelAugust 19, 2020

🖐🖐🖐 ሰላም የዶክተር ጤና ቤተሰቦች!! 🖐🖐🖐
እንደምን ሰነበታችሁ??

በአዲስ መልኩ እናንተን ይጠቅማሉ የምንላቸውን የጤና ምክሮች ይዘን ተመልሰናል፡፡ በዛሬው ጥንክራችን ስለ ቫይታሚን ኤ ጉልህ የጤና ጠቀሜታ እናወራለን፤ ተከታተሉን፡፡ ሃሳብ አስተያየታችሁን በመልዕክት መላክ ትችላላቹ፡፡

ቫይታሚን ኤ እንዴት ለጤና ይጠቅማል??

ቫይታሚን ኤ ለጤና እጅግ ከፍተኛ ጥቅም ያላቸው ፋት ሶሊብል የሚባሉ ውህዶች የጋራ ስያሜ ነው፡፡ የሰውነትን ስርዓት በማሳለጥ አቻ አይገኝለትም፡፡ ከዋነኛ ጠቀሜታዎቹ መሃል እይታን ለመጠበቅ፣ የሰውነትን በሽታ የመከላከል አቅም ለማጎልበት እና የፅንስን በማህፀን ውስጥ እድገት ለማገዝ ይጠቀሳሉ፡፡

ይህ ቫይታሚን የእፅዋት እና የእንስሳት ተዋፅዕዎ በሁለት አይነት መልክ ይገኛል፤ ፕሪፎርምድ ቫይታሚን ኤ እና ፕሮቫይታሚን ኤ ይባላል፡፡ ፕሪፎርምድ የተባለው የቫይታሚን ኤ አይነት ሰውነት ሊጠቀመው የሚችለው አይነት ሲሆን የእንስሳት ተዋፅጦ ውስጥ እንደ ስጋ፣ አሳ፣ ዶሮ፣ እን የወተት ተዋፅዖ ውስጥ ይገኛል፡፡ ፕሮቫየረታሚን ኤ ከፅዋት የሚገኝ ሰውነታችን በቀጥታ ሊጠቀመው የማይችለው የቫይታሚን ኤ አይነት ነው፡፡

ፕሮቫይታሚን ኤ በሰውነታችን ውስጥ ሰውነት ሊጠቀምበት ወደሚችል አይነት ይቀየራል፤ ለምሳሌ ትንሹ አንጀት ውስጥ ቤታ ካሮቲን የተባለው የቫታሚን ኤ አይነት ወደ ሬቲናል በመለወጥ ለሰውነት ጠቀሜታ ይሰጣል፡፡

ቀጥሎ ቫታሚን ኤ ለሰውነት የሚሰጠውን ጠቀሜታ እናነሳለን፤
ቫይታሚን ኤ በምሽት ጊዜ ከሚኖርን የእይታ ችግር እና ከእድሜ ጋር ተያይዞ ከሚመጣ የእይታ መቀነስ ይጠብቃል
የአንዳንድ የካንሰር አይነቶች ተጋላጭነትን ይቀንሳል
የሰውነትን በሽታ የመከላከል አቅምን ያግዛል
በብጉር የመጠቃትን መጠን እጅጉን ይቀንሳል
የአጥንትን ጤንንት ይጠብቃል
ጤናማ የሆነ እድገት እና የስነ-ተዋልዶ ጤና ለመጠበቅ ይረዳል

እናስተውል!!
ከመጠን በላይ ቫታሚን ኤ ጉዳት አለው!!
ቫታሚን ኤን ከመጠን በላይ ሲከማች ሰውነትን ሊጎዳ ይችላል፡፡ ይህ ሁኔታ ሃይፐርቫታሚኖሲስ ኤ ይባላል፡፡ በአብዛኛው ጊዜ ቫታሚን ኤ የሚይዙ መድሃኒቶች ከመጠን በላይ ሲወሰዱ ይከሰታል፤ ከምግብ ከሚገኝ ቫታሚን ኤ ሃይፐርቫታሚኖሲስ ኤ ሲመጣ አይታይም፡፡ የሃይፐርቫይታሚኖሲስ ኤ ምልክቶች ማቅለሽለሽ፣ ማዞር፣ ራስ ምታት፣ ህመም እንዲሁም እስከ ሞት ድረስ ሊደርስ ይችላል፡፡

የትኞቹ ምግቦች ቫይታሚን ኤ አላቸው??

- የበሬ ጉበት

- የበግ ጉበት

- የኮድሊቨር ዘይት

- ሳልመን

- ቱና

- ቺዝ

- ቅቤ

- የተቀቀለ እንቁላል

- ስ£ር ድንች

- ካሮት

- ቀይ ቃሪያ

- ቅስጣ

- ሰላጣ

ይህንን መረጃ ሼር በማድረግ ለሌሎች ያጋሩ!!


ተጨማሪ የጤና መረጃ እንዲደርሶ፦

የዶክተር ጤና ቴሌግራም ገፅ

t.me/DoctorTena

የዶክተር ጤና ፌስቡክ ገፅ፦

fb.com/DoctorTenaEthiopia





EDIT

የጣፊያ ካንሰርDr. Tena - Bethel🖐🖐🖐  ሰላም የዶክተር ጤና ቤተሰቦች!!  🖐🖐🖐ካንሰር እጅግ አስከፊ በሽታ መሆኑ እሙን ነው፡፡ ዛሬ የጣፊያ ካንሰርን አጠቃላይ መረጃ እንሰጣለን፡፡ ...
06/28/2020

የጣፊያ ካንሰር
Dr. Tena - Bethel

🖐🖐🖐 ሰላም የዶክተር ጤና ቤተሰቦች!! 🖐🖐🖐
ካንሰር እጅግ አስከፊ በሽታ መሆኑ እሙን ነው፡፡ ዛሬ የጣፊያ ካንሰርን አጠቃላይ መረጃ እንሰጣለን፡፡

ጣፊያ
የጣፊያ ካንሰር ከጣፊያ ሲሎች የሚነሳ ካንሰር ሲሆን፤ ጣፊያ ከታችኛው የጨጓራ ክፍል ጀርባ የሚገኝ የሆድ ክፍል ነው፡፡ ጣፊያ ለምግብ መፈጨት የሚረዳ ኢንዛም ያመነጫል፤ እንዲሁም የደም ውስጥ ስኳር መጠንን ለመቆጣጠር የሚረዳ ሆርሞንም ያመነጫል፡፡

የጣፊያ ካንሰር
የተለያዩ ባዕድ ነገሮች ከጣፊያ ሊበቅሉ ይችላሉ፤ የካንሰር ባህሪ ሊኖራቸውም ላይኖራቸውም ይችላል፡፡ በጣም የተለመደው የካንሰር አይነት ፓንክሪያቲክ ዳክታል አዴኖ ካርሲኖማ (Pancreatic Ductal Adenocarcinoma) ይባላል፡፡

የጣፊያ ቻንሰር ብዙውን ጊዜ መዳን በሚችልበት ደረጃ አይገኝም፤ አስከፊ ደረጃ ሲደርስ ነው የሚታወቀው፡፡ ምክንቱም ወደ ሌሎች የሰውነት ክፍሎች ከመሰራጨቱ በፊት ምንመ አይነት ምልክት አያሳይም፡፡

ህክምናው በስርጭቱ መጠን ላይ ይወሰናል፡፡ ቀዶ ጥገና፣ ኬሞቴራፒ፣ የጨረር ህክምና ወይም እነዚህ አንድ ላይ ሊሰጡ ይችላሉ፡፡

ምልክቶች
ከላይ እንደጠቀስነው ካንሰሩ ሳይሰራጭ ምልክት አያሳይም፤ ከዛ በኋላ ግን የሚከተሉትን ምልክቶች ሊያሳይ ይችላል፤

- ወደ ጀርባ የሚሄድ የሆድ ህመም

- የምግብ ፍላጎት መቀነስ

- ክብደት መቀነስ

- የቆዳ ቢጫ መሆን

- የሰገራ መንጣት

- የሽንት መጥቆር

- የቆዳ ማሳከክ

- የነበረን የስኳር በሽታን ለመቆጣጠር መቸገር ወይም የስኳር በሽተኛ ያልነበረ ሰው ላይ የስኳር በሽታ ሲገኝ

- የደም መርጋት

- ድካም

ሃኪሞት ጋር መቼ መሄድ አለቦት?
ለምን እንደሆነ በማታቁት መልኩ ምልክቶች ካስተዋሉ ሃኪሞትን ቢያማክሩ ይመከራል፡፡

በምን ምክንያት ይመጣል?
የጣፊያ ካንሰር በምን ምክንያት እንደሚመጣ የተረጋገጠ ምክንያት የለም፡፡ ሃኪሞች አንዳንድ ነገሮች ተጋላጭነትን እንደሚጨምሩ ታይቷል፡፡ ከነዚህም ውስጥ ሲጃራ ማጨስ እና ከቤተሰብ የሚወረስ የጂን ችግር ይጠቀሳሉ፡፡

ተጋላጭነት
· ሲጃራ ማጨስ

· የስኳር በሽታ

· ለረጅም ጊዜ የሚቆይ የጣፊያ መቆጣት

· በቤተሰብ የጣፊያ ካንሰር ወይም ሌሎች ለካንሰር የሚጋልጡ የጀነቲክ ችግር መኖር

· ከልክ ያለፈ ውፍረት

· የእድሜ መግፋት (በተለይ ከ65 ዓመት በላይ መሆን)

ጥናቶች እንደሚያሳዩት ከሆነ እነዚህ ተጋላጭ የሚያደርጉ ሁኔታዎች በአንድ ላይ መገኘት (በተለይ ሲጃራ ማጨስ፣ የስኳር በሽታ እና ጤናማ ያልሆነ አመጋገብ) የበለጠ ተጋላጭነትን ይጨምራል፡፡

ምን ሊያመጣ ይችላል?
የጣፊያ ካንሰር ቀስ በቀስ የሚብስ በሽታ ነው፤ በተያያዥነት የሚከተሉት ሊመጡ ይችላሉ፡፡

· ክብደት መቀነስ

· የቆዳ ቢጫ መሆን

· የሆድ ህመም

· የአንጀት መዘጋት

እንዴት መከላከል ይቻላል?
- የሚከተሉት የጣፊያ ካንሰር ተጋላጭነትን ሊቀንሱ ይችላሉ፤

- ሲጃራ ማጨስን ማቆም

- ጤናማ የሰውነት ክብደት

- ጤናማ አመጋገብ



ምርመራ
ሃኪሞ የጣፊያ ካንሰር ሊሆን ይችላል ብሎ ካሰበ የተለያዩ የደም፣ አላትራሳውንት፣ ሲቲስካን እና ሌሎች ምርመራዎችን ያዛል፡፡ የጣፊያ ካንሰር መሆኑ ከተረጋገጠ የትኛው ደረጃ ላይ እንዳለ ይለያል፤ ምክንያቱም የህክምናው አይነት ለመወሰን እጅግ አስፈላጊ ነው፡፡

ሕክምና
በካንሰሩ ደረጃ መሰረት የተለያዩ የህክምና አማራጮች አሉ፤ ቀዶ ጥገና፣ ኬሞ ቴራፒ እና የጨረር ህክምና ይጠቀሳሉ፡፡

በሽታው የከፋ ደረጃ ከደረሰ ግን የህክምናው አላማ ማዳን ሳይሆን ህይወት እስኪያልፍ ድረስ ህመም እንዳይሰማ ማድረግ እና ሌሎች ምልክቶችን ለማስወገድ ይሆናል፡፡

ይህንን መረጃ ሼር በማድረግ ለሌሎች ያጋሩ!!


ተጨማሪ የጤና መረጃ እንዲደርሶ፦

የዶክተር ጤና ቴሌግራም ገፅ

t.me/DoctorTena

የዶክተር ጤና ፌስቡክ ገፅ፦

fb.com/DoctorTenaEthiopia

በፋይበር የበለፀገ ምግብ…Dr. Tena - Bethel🖐🖐🖐 ሰላም የዶክተር ጤና ቤተሰቦች!!  🖐🖐🖐 በብዙ ጤና ነክ ምክሮች ላይ ፋይበር የመመገብን ጠቀሜታ በተደጋጋሚ ሲነሳ ይታያል፡፡ በዛሬው...
06/27/2020

በፋይበር የበለፀገ ምግብ…
Dr. Tena - Bethel

🖐🖐🖐 ሰላም የዶክተር ጤና ቤተሰቦች!! 🖐🖐🖐

በብዙ ጤና ነክ ምክሮች ላይ ፋይበር የመመገብን ጠቀሜታ በተደጋጋሚ ሲነሳ ይታያል፡፡ በዛሬው ጥንክራችን ይህንን ብዥታ ለመግለጥ እንሞክራለን፡፡

ፋይበር ምንድነው?

የምግብ ፋይበር የሚባለው ከምንመገበው እፅዋት ውስጥ ሰውነት ሊፈጨው ሊዋሃደን የማይችለው ክፍል ነው፡፡ ፋይበር ስለማይፈጭ እንዳለ ሆኖ የስነ-ልመት አካላቶችን እንደ ጨጓራ፣ ትልቁ እና ትንሹ አንጀትን በማለፍ ከሰገራ ጋር ይወጣል፡፡፡፡ሌሎች የምግብ አይነቶች እንደ ካርቦሃይድሬት፣ ስብ፣ ፕሮቲን ሰውነታችን ፈጭቶ ይዋሃደናል፡፡

ፋይበርን በሁለት ከፍለን ማየት እንችላለን፤

1. የሚሟሟ የፋይበር አይነት

- ይሄኛው የፋይበር አይነት ውሃ ውስጥ ሲሟሟ የሚዝለገለግ ይሆናል፡፡ የደም ውስጥ ኮሌስትሮል እና ስኳር መጠንን በመቀነስ ይታወቃል፡፡ የሚሟሟው ፋይበር በኦትስ፣ ባቄላ፣ ፖም፣ ገብስ እና ካሮት ውስጥ ይገኛል፡፡

2. የማይሟሟ የፋይበር አይነት

- ሌላው የፋበር አይነት የማይሟሟው ነው፤ ይህ አይነት ለምግብ መፍጨት ስርዓት ተቃሚው ነው፡፡ በውሃ ስለማይሟሟ የስነ-ልመት አካላትን ማለፍ ስለሚችል የሰገራን መጠን ይጨምራል፡፡ ስለዚህ በድርቀት ለሚሰቃዩ ሰዎች መፍትሔ ነው፡፡ ያልተፈተገ እህል፣ ኦቾሎኒ፣ ጥራጥሬዎች፣ አትክልት እንደ ጥቅል ጎመን፣ ድንች፣ አረንጓዴ እሸት በማሟሟ የፋይበር አይነት በለፀጉ ናቸው፡፡

ሁለቱ የፋበር አይነቶች በምግቦች ውስጥ በተለያየ መጠን ይገኛሉ፡፡ በመሆኑም የተለያዩ በፋይበር የበለፀጉ ምግቦችን መመገብ ጠቀሜታው ላቅ ያለ ነው፡፡

በፋበር የበለፀገ ምግብ ለምን ይጠቅማል?

· የአንጀትን እንቅስቃሴ ያስተካክላል

· የአንጀትን ጤንነት ለመጠበቅ ይረዳል

· የደም ውስጥ ኮሌስትሮል መጠንን ይቀንሳል

· የደም ውስጥ ስኳር መጠንን ያስተካክላል

· ጤናማ ክብደት እንዲኖር ይረዳል

· ረጅም እድሜ ለመኖር ይጠቅማል

ፋይበር ከየት ይገኛል?

በቀላሉ የሚገኙ ነገር ግን የፋይበር ይዘታቸው ከፍተኛ የሆኑ የምግብ አይነቶች፤

- ያልተፈተገ እህል

- ፍራፍሬ

- አትክልት

- ባቄላ፣ አተር እና ሌሎች ጥራጥሬዎች

- ኦቾሎኒ እና ሌሎች ፍሬዎች

እናስተውል!!

ፋይበር እጅግ ጠቃሚ ቢሆንም ከመጠን በላይ ከተወሰደ የሆድ መነፋት፣ ቁርጠት እና አየር (ፈስ) ሊያመጣ ይችላል፡፡ የሚወስዱትን የፋይበር መጠንን ቀስ በቀስ በሳምንታት ውስጥ መጨመር ይመከራል፡፡ እንዲህ ማድረግ የስነ-ልመት ስርዓት ውስጥ ያሉ ተፈጥሮአዊ ጠቃሚ ባክቴሪያዎች እንዲኖሩ ያደርጋል፡፡

በተጨማሪም ውሃ በደንብ መጠጣት እጅግ ይጠቅማል፡፡ ፋይበር ውሃ ሲያገኝ የተሻለ ይጠቅማል፤ ከዚህ ጋርም ተያይዞ ሰገራን ለማለስለስ እና ለመጨመር ይረዳል፡፡



ይህንን መረጃ ሼር በማድረግ ለሌሎች ያጋሩ!!


ተጨማሪ የጤና መረጃ እንዲደርሶ፦

የዶክተር ጤና ቴሌግራም ገፅ

t.me/DoctorTena

የዶክተር ጤና ፌስቡክ ገፅ፦

fb.com/DoctorTenaEthiopia

ካሮትDr. Tena - Bethel🖐🖐🖐 ሰላም የዶክተር ጤና ቤተሰቦች!!  🖐🖐🖐ካሮት ለእይታ እንደሚጠቅም በሁሉም ዘንድ ሲነገር እንሰማለን፡፡ ዛሬ ካሮትን የመመገብ ጥቅምን ጥናቶችን በመጠቆም ...
06/25/2020

ካሮት
Dr. Tena - Bethel

🖐🖐🖐 ሰላም የዶክተር ጤና ቤተሰቦች!! 🖐🖐🖐

ካሮት ለእይታ እንደሚጠቅም በሁሉም ዘንድ ሲነገር እንሰማለን፡፡ ዛሬ ካሮትን የመመገብ ጥቅምን ጥናቶችን በመጠቆም እናያለን፡፡

ካሮት
ከጣፋጭ ጣዕሙ ባሻገር ካሮት በቤታ ካሮቲን፣ ቫታሚን፣ ሚነራል እና አንታኦክሲዳንት የበለጸገ ነው፡፡

የጥናት የተረጋገጡ የካሮት የጤና ጥቅሞች፤

1. ካሮት ለተሸለ እይታ

- ጥናቶች እንደሚያሳዩት ካሮት ውስጥ ያለው ሉቲን እና ላዮኮፔን የተባሉ ንጥረ-ነገሮች እይታን ከመጠበቅ ባሻገር በምሽት ጊዜ ለማየት ይጠቅማል፡፡

2. ካሮት ለተሸለ በሽታ የመከላከል አቅም

- ካሮት በውስጡ የተለያዩ ንጥረ-ነገሮች እንደ ቫይታሚን ሲ፣ አንታይኦክሲዳንት ይይዛል፤ ይህም የሰውነትን መከላከል አቅም ይጨምራል፡፡ ሁልጊዜ ካሮት መመገብ ሰውነትን ከበሽታ አምጪ ተዋህሲያን ይጠብቃል፡፡

3. ካሮት ክብደት ለመቀነስ

- ክብደት ለመቀነስ ካሰቡ ምግቦ ውስጥ በፋይበር የበለፀጉ የምግብ አይነቶችን ማካተት ያስፈልጋል፡፡ ካሮት የሚዚው የፋይበር መጠን ከፍተኛ በመሆኑ ለዚህ ይጠቅማል፡፡

4. ካሮት የምግብ መፈጨት ለማስተካከል

- በፋይበር የበለፀገ በመሆኑ የስነ-ልመት ስርዓትነ ለማሳለጥ ይጠቅማል፡፡ ድርቀትንም ይከላከላል፡፡

5. ካሮት ኮሌስትሮልን ለመከላከል እና የልብን ጤንነት ለመጠበቅ

- አሁንም በፋይበር ይዘቱ ምክንያት የበዛ መጥፎ ኮሌስትሮልን ለመቀነስ ይጠቅማል፡፡ ተያይዞም የልብን ጤንነት ለመጠበቅ ይረዳል፡፡

6. ካሮት የደም ግፊትን ለመቀነስ

- መጥፎ ኮሌስትሮልን ከመቀነስ ጋር ተያይዞ ካሮት በፖታሺየም የበለፀገ ነው፡፡ ፖታሺየም በደም ስሮች ውስጥ ያለውን ውጥረት በመቀነስ የደም ዝውውርን ያስተካክላል፤ ተያይዞም ግፊትን ይቀንሳል፡፡

7. ካሮት ለጤናማ ፀጉር

- አንደኛውና ዋነኛው የካሮት ጥቅም ጠፀጉርን ጤንነት መጠበቅ ነው፡፡ ለፀጉር አስፈላጊ የሆነውን ቫይታሚን በማድረስ ፀጉርን ጠንካራ፣ ወፍራም እና የሚምር ያደርገዋል፡፡

8. ካሮት ለሚያበራ ቆዳ

- ካሮት ዘወትር መጠቀም ቆዳን የሚያምር ያደርጋል፡፡ ካሮትን ብርቱካናማ ቀለም የሰጠው ቤታ ካሮቲን ቆዳን በማፍካት ውበትን ያጎናፅፋል፡፡

9. ካሮት የቆዳ መጠማደድን ለመከላከል

- ካሮት ውስጥ የሚገኘው ቤታ ካሮቲን ሰውነታችን ውስጥ ሲገባ ወደ ቫይታሚን ኤ ይለወጣል፡፡ ቫይታሚን ኤ የቆዳን ልስላሴ እና ጤንነት ይጠብቃል፡፡

10. ካሮት ለጤናማ ጥርስ

- ካሮት የጥርስን መቦርቦር የሚከላከል አትክልት ነው፡፡ ጥሬ ካሮት ማኘክ እንደ በተፈጥሮአዊ መንገድ ጥርስን መቦረሽ ይቆጠራል፡፡

11. ካሮት ቆዳን ልስላሴ ለመጠበቅ

- ቆዳዎ ደረቅ ከሆነ ካሮት ሁነኛ መፍትሔ ነው፤ ምክንያቱም በፖታሺየም የበለፀገ ስለሆነ፡፡ የካሮት ጁስ መጠጣት ሰውነትን እና ቆዳን የውሃ መጠን ያስተካክላል፡፡ ዕንዲሁም ከካሮት የተሰሩ የቆዳ ውጤቶች ጠቃሚ ናቸው፡፡

12. ካሮት የቆዳን ጠባሳ ለመቀነስ

- በተለያዩ ምክንያቶች ቆዳ ላይ የሚቀረውን ጠባሳ ለመቀነስ እንደሚረዳ ጥናቶች ያሳያሉ፡፡ ጁሱን ወይም የቆዳ ክሬሙን መጠቀም ይቻላል፡፡

13. ካሮት ቆዳን ከፀሃይ ለመከላከል

- ካሮት ቆዳን ከፀሃይ ጨረር ይከላከላል፡፡ ሰውነት ውስጥ ሲገባ ወደ ቫይታሚን ኤ የሚለወጠው ቤታ ካሮቲን ለቆዳ እጅግ ጠቃሚ ነው፡፡ የሞቱ የቆዳ ሴሎችን ይጠግናል፤ እንዲሁም ቆዳን ከጨረር ጥቃት ይከላከላል፡፡

ይህንን መረጃ ሼር በማድረግ ለሌሎች ያጋሩ!!

ተጨማሪ የጤና መረጃ እንዲደርሶ፦

የዶክተር ጤና ቴሌግራም ገፅ

t.me/DoctorTena

የዶክተር ጤና ፌስቡክ ገፅ፦

fb.com/DoctorTenaEthiopia

ወተት መጠጣትDr. Tena - Bethel 🖐🖐🖐  ሰላም የዶክተር ጤና ቤተሰቦች!!  🖐🖐🖐ወተት መጠጣት ለልጆች እንጂ ለአዋቂ ያን ያህል እንደማይጠቅም ይታመናል፡፡ ይህ ስህተት ነው፤ ወተት በ...
06/23/2020

ወተት መጠጣት
Dr. Tena - Bethel

🖐🖐🖐 ሰላም የዶክተር ጤና ቤተሰቦች!! 🖐🖐🖐

ወተት መጠጣት ለልጆች እንጂ ለአዋቂ ያን ያህል እንደማይጠቅም ይታመናል፡፡ ይህ ስህተት ነው፤ ወተት በማንኛውም እድሜ ላይ ያሉ ሰዎች አያሌ ጠቀሜታ አለው፡፡

ወተት
“በቀን አንድ ብርጭቆ ወተት!!” በብዙ ዶክተሮች የሚመከር ነው፡፡ ለዘመናት ወተት እጅግ ጤናማ ፈሳሽ ነው፡፡ በውስጡ ያለው ካልሺየም በቀላሉ በሚገኝ ሌላ የምግብ አይነት ውስጥ አይገኝም፡፡ ለሰውነት እድገት እና ጤንነት አስፈላጊ ንጥረ-ነገር ይይዛል፡፡ ወተት የማይወዱ ከሆነ እርጎ፣ አይብ እና ሌሎች የወተት ተዋጽኦ መጠቀም ይቻላል፡፡

ወተት ለምን ይጠቅማል?
1. ካልሺየም

- ወተት በውስጡ የሚይዘው የካልሺየም መጠን ከፍተኛ ነው፡፡ ለዚህም ነው በቀን አንድ ብርጭቆ ወተት የሚመከረው፡፡

2. አስፈላጊ ንጥረ-ነገሮች

- ሌሎች ንጥረ-ነገሮች እንደ ፕሮቲነተ፣ ቫይታሚን ኤ፣ ቢ1፣ ቢ2፣ ቢ12፣ ዲ፣ ኮሊን፣ ፖታሺየም እና ማግኒዢየም ይይዛል፡፡

3. ከአካላዊ እንቅስቃሴ በኋላ

- ከአካላዊ እንቅስቃሴ በኋላ ወተት መጠጣት አቅምን እና ብርታትን ይጨምራል፡፡ እንዲሁም ለጡንቻ መጠንፈር የሚጠቅም ንጥረ-ነገርም አለው፡፡

4. ክብደት ለመቀነስ

- አዳዲስ ጥናቶች ወተት ውስጥ የሚገኘው ሊኖለኒክ አሲድ ስብን ለማቅለጥ ይረዳል፡፡

5. ለጠንካራ አጥንት

- ወተት ውስጥ ያለው ካልሺየም እና ቫይታሚን ዲ ለአጥንት ጥንካሬ እና ጤንነት እጅግ አስፈላጊ ነው፡፡ ሁልጊዜ ወተት መጠጣት የአይንት መሳሳትን እና ኦስቲዮአርትራይቲስን ለመከላከል ይጠቅማል፡፡

6. በሽታ የመከላከል አቅም

- በተለይ ወተት ላይ እርድ ጨምሮ መጠጣት በሽታ የመከላከል አቅምን በመጨመር ወቅቶች ሲቀያየሩ ለመቋቋም ይረዳል፡፡

7. ጉንፋን እና የአፍንጫ መታፈን

- ለጎሮሮ ቁስለት ሙቅ ወተት እንደሚረዳ ጥናቶች ያሳያሉ፡፡ ትንሽ ኦቾሎኒ መጨመር በተለይ ለህፃናት ይጠቅማል፡፡

8. ለውብ ቆዳ

- ከድሮ ጀምሮ ወተት በባህላዊ መልኩ ውበትን ለመጠበቅ ይረዳል፡፡ የተለያዩ የፊት ቅባቶች ከወተት ይሰራሉ፡፡ በተለይ ለፊት ጥራት ተመራጭ ነው፡፡

9. ለፀጉር ጤንነት

- ወተት ከሙዝ እና ከማር ጋር በመቀላቀል ፀጉርን መቀባትና ለከ15-20 ደቂቃ ማቆየት፣ መታጠብ ለደረቅ ፀጉር መፍትሔ እንደሆነ ታይቷል፡፡

10. የደም ግፊት

- የላም ወተት በውስጡ በሚይዘው ፖታሺየም የደም ግፊትን ያስተካክላል፡፡

ይህንን መረጃ ሼር በማድረግ ለሌሎች ያጋሩ!!


ተጨማሪ የጤና መረጃ እንዲደርሶ፦

የዶክተር ጤና ቴሌግራም ገፅ

t.me/DoctorTena

የዶክተር ጤና ፌስቡክ ገፅ፦

fb.com/DoctorTenaEthiopia

የስክሪን ብርሃን እና የልጆች አይንDr. Tena - Bethel🖐🖐🖐  ሰላም የዶክተር ጤና ቤተሰቦች!!  🖐🖐🖐በዚህ ወቅት ብዙ ወላጆች የሚቸገሩበት ጉዳይ የልጆች ስልክ፣ ታብሌት ወይም ኮምፒዩ...
06/22/2020

የስክሪን ብርሃን እና የልጆች አይን
Dr. Tena - Bethel

🖐🖐🖐 ሰላም የዶክተር ጤና ቤተሰቦች!! 🖐🖐🖐

በዚህ ወቅት ብዙ ወላጆች የሚቸገሩበት ጉዳይ የልጆች ስልክ፣ ታብሌት ወይም ኮምፒዩተር ይዞ መቆየት ነው፡፡ ዛሬ ከእነዚህ ስክሪኖች የሚወጡት ጨረር እንዴት አይንን እንደሚጎዳ እናያለን፡፡


የስክሪን ብርሃን እና የልጆች አይን ጤንነት



የልጆችን ስክሪን የሚያዩበትን ሰዓት መወሰን እጅግ አስፈላጊ ነው፡፡ በዚህ መልኩ ውጪ እንዲጫወቱ፣ እንቅስቃሴ እንዲያደርጉ፣ ጥሩ እንቅልፍ እንዲያገኙ እንዲሁም ከሌሎች ጋር ጥሩ ግንኙነት እንዲፈጥሩ ያስችላቸዋል፡፡ ሌላው ዋነኛው ነጥብ ደግሞ የአይንን ጤንነት ለመጠበቅ አስፈላጊ ነው፡፡


ከዚህ በታች እንዴት የስክሪን ብርሃን አይንን እንደሚጎዳ እናያለን፡፡

ብዙ ወላጆች የሞባይል እና ሌሎች ስክሪኖችን ለገጅም ጊዜ ማየት ጉዳት እንዳለው ሲጠይቁ ይሰማል፡፡ ከዚህ በታች አንዳንድ የሚጠበቂ እና አስደንጋጭ ውጤቶችን እንመለከታለን፡፡


1. ብዙ ጊዜ በቤት ውስጥ መሆን እና ሩቅ ነገርን ያለማየት ችግር (Near Sightedness)



- አንደኛው ችግር ስክሪን ብዙ ጊዜ መጠቀም ልጆችን ቤት ውስጥ እንዲቆዩ ያደርጋቸዋል፡፡ ጥናቶች እንደሚያሳዩት ከሆነ የፀሐይ ብርሃን ለአይን ጤንነት አስፈላጊ ነው፡፡ ስለዚህ ልጆች ውጪ እንዲጫወቱ ማድረግ ከአካላዊ ጤናቸው ባለፈ ለአይን ጤንነትም ጉልህ ሚና ይጫወታል፡፡



- እንዲሁም ሌሎች ጥናቶች እንዳከሉት ልጆች በቤት ውስጥ ብዙ ሲቆዩ የሩቅ ነገርን ያለማየት ችግር (Near Sightedness) ተጠቂ ይሆናሉ፡፡ ምክንያቱ በትክክል ባታወቅም የተለያዩ መላምቶች አሉ፤ ከእነዚህም ተመራማሪዎች በፀሃይ ጨረር ውስጥ ያለው ዩቪ ብርሃን ለጤናማ አይን እድገትአስፈላጊ እንደሆነ አሳይተዋል፡፡ ተያይዞም ባለፉት 30 ዓመታት የሩቅ ነገርን ያለማየት ችግር (Near Sightedness) በልጆች ላይ እጅጉን እንደጨመረ ታይቷል፡፡


2. የአይን መድከም



- አይናችን እረፍት ይፈልጋል፡፡ ልጆች ደግሞ አንድ ነግር ሲይዙ ቶሎ ላተዉ ስለሚችሉ ለብዙ ሰዓታት ሊቆዩ ይችላሉ፡፡ ትኩረት የሚፈልግ ነገር በተለይ ከስክሪን የሚወጣው ብርሃን አይንን የበለጠ ያደክማል፡፡


3. የአይን መድረቅ እና መቆጣት

- ረጀረመረ ሰዓት ስክሪን ላይ ማሳለፍ የአይን ድርቀት እና መቆጣትን ያስከትላል፡፡ ጥናቶች እንደሚጠቁሙት ከሆነ በማንኛውም እድሜ ላይ ያሉ ሰዎች ስክሪን ላይ ሲቆዩ ትኩረታቸው ስለሚወሰድ አይናቸውም ብዙ አይከድኑም፤ ይህም የአይን መድረቅን ያመጣል፡፡ ለጥሩ እይታ አይን ላይ ቀጭን የእምባ ሽፋን በጣም አስፈላጊ ነው፡፡ ይህ ችግር ህፃናት ላይ ሲሆን ይብሳል ምክንያቱም የአዋቂ አይን ተብሎ የሚሰራ ስክሪን ስለሚጠቀሙ፡፡


4. የአይን ትኩረትን ለመቀያየር መቸገር



- አንድ ነገር ላይ ለገጅም ጊዜ አትኩሮ መቆየት እይታን አስተካክሎ ሌሎች ነገሮችን ለማየት በተለይ የርቀትእይታ ላይ ያስቸግራል፡፡ ይህ ጊዜያዊ ችግር ነው በጥቂት ሰዓታት፣ ቀናት አሊያም ሳምንታት ወደ ቀድሞ እይታ ይመለሳል፡፡


5. ከእይታ በላይ እንቅልፍ ላይ ያለው ችግር



- የእንቅልፍ ጊዜን መሻማት ሌላኛው ህፃናት ላይ የሚፈጥረው ችግር ነው፡፡ ጥናቶች እንደሚያሳዩት ከሆነ ከስልክ፣ ታብሌት፣ ኮምፒዩተር ወይም ሌሎች ባለ ስክሪን እቃዎች የሚወጣው ሰማያዊ ጨረር በተለይ ማታ ማታ መጠቀም የአእምሮን የእንቅልፍ ስርዓት ያዛባል፡፡ እነዚህን የስክሪን መብራቶች አእምሮአችን እንደ ቀን ስለሚያይ ሰውነት የእንቅልፍ ጊዜውን ይለውጣል፡፡ በተጨማሪም የቪዲዮ ጌሞች ስለሚያጓጉ ልጆች የእንቅልፍ ጊዜያቸውን መስዋት አድርገው ይቀመጣሉ፡፡


ምን ማድረግ አለብን?

· ስክሪን የሚጠቀሙበትን ጊዜ መገደብ

- ልጆች በዚህ እቅድ እንደሚመሩ ማረጋገጥ

- ልጅዎ ውጪ እንዲጫወት ማበረታታት

- ስልክ ወይም ታብሌት መጠቀም የማይችሉባቸውን ቦታዎች መለየት

- በተለይ ከመኝታ በፊት መኝታ ቤት ውስጥ ስልክ እንዳይጠቀሙ ማድረግ

- ወላጆች ለልጆች ሞዴል መሆን አለባቸው፤ እነርሱም ቢሆን ስልክ የሚጠቀሙበትን ጊዜ መገደብ አለባቸው


ይህንን መረጃ ሼር በማድረግ ለሌሎች ያጋሩ!!



ተጨማሪ የጤና መረጃ እንዲደርሶ፦

የዶክተር ጤና ቴሌግራም ገፅ

t.me/DoctorTena

የዶክተር ጤና ፌስቡክ ገፅ፦

fb.com/DoctorTenaEthiopia

ሶሻል ፎቢያ (Social Anxiety Disorder)Dr. Tena - Bethel🖐🖐🖐  ሰላም የዶክተር ጤና ቤተሰቦች!!  🖐🖐🖐 በጥያቄያችሁ መሰረት ሰዎች በበዙባቸው ቦታዎች ላይ የፍርሃት ስ...
06/21/2020

ሶሻል ፎቢያ (Social Anxiety Disorder)
Dr. Tena - Bethel

🖐🖐🖐 ሰላም የዶክተር ጤና ቤተሰቦች!! 🖐🖐🖐

በጥያቄያችሁ መሰረት ሰዎች በበዙባቸው ቦታዎች ላይ የፍርሃት ስሜት በምን ምንያት እንደሚመጣ እና መፍትሔዎቹ እናወራለን፤ አብራችሁን ቆዩ!!


ሶሻል ፎቢያ (Social Anxiety Disorder) ምንድነው?

ሰዎች ባሉባቸው ቦታዎች ላይ የፍርሃት ስሜት የተለመደ እና ጤናማ ነው፡፡ ለምሳሌ ከአዲስ ሰው ጋር ቀጠሮ ሲኖረን ወይም ተመልካች ባለበት የምናቀርበው ነገር ሲኖር ልንፈራ እንችላለን ፡፡ ነገር ግን ሶሻል ፎቢያ (Social Anxiety Disorder) በእለት ተእለት እንቅስቃሴ ላይ ከሰዎች ጋር ባለን መስተጋብር በሌሎች የመተቸት ስጋት ስለሚኖር ከባድ ፍርሃት፣ ጭንቀት፣ የሚከብድ ስሜት እንዲሁም በራስ አለመተማመን ሲሰማ ነው፡፡



መሰል ስሜቶች ማህበረሰባዊ መስተጋብርን ጭራሹን ሊያስቀሩት ይችላሉ፡፡ ተያይዞም የትምህርት፣ የስራ፣ እና ሎች እንቅስቃሴዎች ይገደባሉ፡፡

Social Anxiety Disorder አብሮ የሚቆይ የአእምሮ በሽታ ነው፤ የተለያዩ መንገዶችን መለማመድ፣ የንግግር ህክምና እንዲሁም አንዳንድ መድሐኒቶች በራስ መተማመን ስሜትን ዳግም ሊያመጡ እና ከሰዎች ጋር ያለን ግንኙነት የማሻሻል ብቃት እንዳላቸው ይነገራል፡፡


ምልክቶች

ሰዎች ባሉበት ቦታዎች የማፈር ወይም ያለመመቸት ስሜት በተለይ ልጆች ላይ ሲታይ የሶሻል ፎቢያ ላይሆን ይችላል፡፡ እነዚህ ስሜቶች እንደየ ማህበራዊ ሁኔታዎች ይለያያሉ እንዲሁም እንደየሰዉ የህይወት ልምት የተለያዩ ናቸው፡፡ አንዳንድ በተፈጥሮ ተግባቢ ሰዎች እንዳሉ ሁሉ የተቆጠቡ ሰዎችም እንዳሉ መዘንጋት የለበትም፡፡
የስሜት ምልክቶች

- ሰዎች ይፈርዱብኛል ተብሎ የሚታሰቡ ሁኔታዎችን መፍራት

- እራስን ላለማዋረድ መጠንቀቅ

- ከአዲስ ሰዎች ጋር በሚነጋገሩ ወቅት ጥልቅ የሆነ የፍራቻ ስሜት

- ሰዎች እንደተጨነቁ እንዳያውቁ መፍራት

- ከፍራቻ ጋር አካላዊ ለውጦች (እንደ ላብ፣ የፊት መቅላት፣ የእጅ መንቀጥቀጥ ወይም የድምፅ መቅጠን) ሲታዩ የመሳቀቅ ስሜት

- ሰዎች የበዙበት ቦታ ላይ አለመናገር

- አትኩሮት የሚሰበስብ ነገር በጭራሽ አለማድረግ

- ገና ለገና የሚያስፈሩ ነገሮችን ለማድረግ ሲያስቡ ከባድ ጭንቀት ውስጥ መውደቅ

- ከማህበራዊ መስተጋብሮች በኋላ ምን እንዳሉ ማሰብ እና የት የት ጋር እንደተሳሳቱ ማንሰላሰል

- ከሰዎች ጋር በሚኖር ማህበራዊ ቅርርበት ላይ በጣም መጥፎ ነገር ሊፈጠር እንደሚችል ማሰብ



አካላዊ ምልክቶች

- የፊት መቅላት

- የልብ ምት መጨመር

- የእጅ መንቀጥቀጥ

- ላብ

- የሆድ መረበሽ፣ ማቅለሽለሽ

- ትንፋሽ ማጠር

- ራስ ማዞር

- የጡንቻ ውጥረት


የማህበራዊ ግንኙነቶችን ማስወገድ

ለምሳሌ፤

- ከአዲስ ሰዎች ማግኘት

- ብዙ ሰው የሚገኝባቸው ቦታዎች መሄድ

- ስራ ወይም ትምህርት ቤት መሄድ

- ንግግር መጀመር

- ፆታዊ ግንኙነት መጀመር

- ሰዎች ከተቀመጡ በኋላ መግባት

- ሰዎች ፊት መብላት

- የጋራ መጸዳጃ ቤቶችን መጠቀም



ምልክቶቹ ከጊዜ እና ከሁኔታዎች ጋር ይለዋወጣሉ፡፡ ውጥረት ውስጥ ካለን ሊነሳ ይችላል፡፡ መሰል ስሜቶችን የሚያመጡ ሁኔታዎችን ማስወገድ ለጊዜው ጥሩ ስሜት ቢሰጥም የፍርሃት ስሜቱን በተገቢው መፍትሔ ካልተፈለገለት አብሮ ይቆያል፡፡


ሃኪሞት ጋር መቼ ሄድ አለቦት?

በፍርሃት፣ መሳቀቅ እና ጭንቀት ምክንያት የተለመዱ የማህበራዊ ግንኙነቶችን እና መሰል ሁኔታዎችን የሚፈሩ እና የሚሸሹ ከሆነ የህክምና እርዳታ ያስፈልጎታል፡፡


በምን ምክንያት ይመጣል?

እንደሌሎች የስነ-አእምሮ በሽታዎች ይሄም በጣም ብዙ ምክንያቶች እንደሚያመጡት ይታመናል፡፡ ከእነዚህም ውስጥ የሚከተሉት ይጠቀሳሉ፤

1. ከቤተሰብ የሚወረስ

2. የአእምሮ ክፍል ችግር

3. የአካባቢ ተፅዕኖ


ተጋላጭነት

· በቤተሰብ ተመሳሳይ ችግር ካለ

· መጭፎ ልምድ

· ተጨቁኖ ማደግ

· አዲስ ማህበራዊ ወይም የስራ ሁኔታ

· የሰዎችን ትኩረት የሚስብ ገፅታ


ምን ሊያመጣ ይችላል?

- የወረደ በራስ መተማመን ስሜት

- ስለራስ ጥሩ ያልሆነ አስተሳሰብ

- ትችትን መፍራት

- የማህበራዊ ግንኙነት ቀውስ

- ማህበራዊ ተግባቦቶችን ማስወገድ እና መለየት

- የስራ እና የትምህርት ውጤት መቀነስ

- ሱስ ውስጥ መግባት (እንደ አልኮል፣ ጫት…)

- ራስን ለማጥፋት መሞከር ወይም ማድረግ


እንዴት መከላል ይቻላል?

ይህን መሰል የፍርሃት ስሜት ማን ላይ ወይም በምን ሰዓት ሊከሰት እንደሚችል መገመት አይቻልም፡፡ ነገር ግን እንደዚህ አይነት ስሜቶች ሲኖሩ ለመቀነስ ወይም እንዳኖሩ ለማድረግ የሚከተሉትን ማድረግ ይመከራል፤

· ሳይዘገዩ ወደ ህክምና ተቋም መሄድ

· የእለት ተእለት ውሎን መፃፍ

· በህይወት ውስጥ ቅድሚያ የምንሰጣቸውን ነገሮች መለየት

· ሱስ ከሚያስይዙ ነገሮች መራቅ


ምርመራ

ሃኪም ጋር ሲቀርቡ የተለያዩ አካላዊ ምርመራዎች በማድረግ፣ ጥያቄዎች በመጠየቅ ስለሁኔታው ይበልጥ ለመረዳት ይሞክራል፡፡ የቤት ስራዎችን ሊሰጦትም ይችላል፤ እንደ የፍርሃት ስሜት ሊያመጡ የሚችሉ ሁኔታዎችን መዘርዘር፣ ስሜቱን በደንብ አዳምጦ መመዝገብ እና ሌሎችም፡፡ በአለም አቀፍ ደረጃ ባሉ መስፈርቶች አንፃር የፍርሃቱን አይነት ለማወቅ ይሞክራል፤ ከዚያም ወደ መፍትሔው ይሄዳል፡፡


ህክምናው

ስሜቱ የእለት ተእለት እንቅስቃሴን የሚጎዳበት መጠን የህክምናውን አይነት ይወስናል፡፡ ይህን ከግምት ውስጥ በማስገባት የንግግር ህክምና ወይም የሚዋጡ መድሐኒቶች ይታዘዛሉ፡፡


አስታውሱ!!

- የህክምናው ውጤት ቢዘገይም ተስፋ እንዳይቆርጡ፤ ምክንያቱም እስከ ወራት ሊወስድ ስለሚችል

- ለእርሶ የሚሆን የህክምና መንገድ መምረጥ ሙከራዎች ያስፈልጉታል

- አንዳንዶች ህክምናውን ለረጅም ጊዜ መውሰድ ይኖርባቸዋል፤ ሌሎች ደግሞ በጥቂት ጊዜ መሻሻል ሊያሳዩ ይችላሉ

- መድሐኒት ማቋረጥ በሽታው እንዲብስ ያደርገዋል

- የሃኪሞትን ምክር በተገቢው መልኩ ተግባራዊ ያድርጉ



ይህንን መረጃ ሼር በማድረግ ለሌሎች ያጋሩ!!



ተጨማሪ የጤና መረጃ እንዲደርሶ፦

የዶክተር ጤና ቴሌግራም ገፅ

t.me/DoctorTena

የዶክተር ጤና ፌስቡክ ገፅ፦

fb.com/DoctorTenaEthiopia

የፀሐይግርዶሽ እና ዓይናችንDr. Tena - Bethel🖐🖐🖐  ሰላም የዶክተር ጤና ቤተሰቦች!!  🖐🖐🖐  በነገው እለት የየፀሐይ ግርዶሽ በ ኢትዮጵያ እንደሚታይ ከመዘገቡ ጋር ተያይዞ የፀሐይ ...
06/20/2020

የፀሐይግርዶሽ እና ዓይናችን
Dr. Tena - Bethel

🖐🖐🖐 ሰላም የዶክተር ጤና ቤተሰቦች!! 🖐🖐🖐



በነገው እለት የየፀሐይ ግርዶሽ በ ኢትዮጵያ እንደሚታይ ከመዘገቡ ጋር ተያይዞ የፀሐይ ግርዶሹን ለማየት ሲባል ቀጥታ ወደ ፀሐይ ማየት ስለሚያስከትለው ጕዳትና እንዴት መከላከል እንደሚቻል በአይን ስፔሻሊስት ሐኪም የተሰጠ ማብራሪያ ቀጥሎ እናቀርባለን፡፡


የፀሐይ ግርዶሽ እና ዓይናችን

በፀሐይ ጨረር የሚመጣ የ ሬቲና (የብርሃን መቀበያ) ጉዳት ይባላል። ይኽ ጉዳት የሚከሰተው በቀጥታ ፀሐይን ወይም የፀሐይ ግርዶሽን ለማየት ሲሞከር የሚከሰት ችግር ሲሆን የብርሃን መቀበያችን(ሬቲና) ላይ ጉዳት በማድረስ ዕይታችንን ይቀንሳል፡፡



ጨረሩን ለአንድ ደቂቃ እንኳን ያዩ ሰዎች ጉዳት ደርሶባቸዋል፡፡ በዚህ ምክኒያት የሚከሰተው ጉዳት ለመዳን ከ3-6 ወር ሊፈጅ ይችላል። እንደዛም ሆኖ ግን ወደቀድሞው የዕይታ አቅም ሳይመለስ ዘለቄታዊ የዕይታ መቀነስ ሊያስከትል ይችላል።



የዚህ ችግር ዋና መንስዔ ከፀሐይ የሚወጣው ጨረር ቢሆንም በብረት ብየዳ ጊዜ ከሚወጣ ጨረር፣ ከትክክለኛው ኃይል በላይ የሚለቀቁ ሌሎች የብርሃንና የሌዘር ምንጮችም ሊከሰት ይችላል። ጨረሩን (በተለይ ልዕለሐምራዊ-ለ Ultraviolet -B )በቀጥታ የብርሃን መቀበያና መጋቢ ህዋሳት ላይ ኬማካዊ ለውጥ በመፍጠር ጉዳት ያስከትላል።


አጋላጭ ሁኔታዎች

· ህጻናትና ወጣቶች የተፈጥሮ ሌንሳቸው ሞራ ያልጀመረው ስለሚሆን በቀጥታ ፀሐይን ሲያዩ ሊጐዱ ይችላሉ፡፡



· ባንጻራዊነት እድሜያቸው የገፋ ሰዎች ላይ ሞራ ስለሚጀምር ወደ ዓይን የሚገባው ጨረር ይቀንሳል፡፡



· ሆኖም የሞራ ቀዶ ጥገና አድርገው አርቲፊሻል ሌንስ የገባላቸው ሰዎች ወደ ፀሐይ ቀጥታ ማየት የለባቸውም፡፡



· የአዕምሮ ህመም ወይም ውስንነት ያላቸው ሰዎች በብዛት ወደፀሐይ ቀጥታ ሊያዩ ስለሚችሉ ጥንቃቄና እርዳታ ያሻቸዋል፡፡



· ወንዶች ከሴቶች የበለጠ ተጋላጭ ናቸው



· ነጮች ከጥቁሮች የበለጠ ተጋላጭ ናቸው



· በብየዳ ጊዜ ተገቢውን መነጽርና የፊት ጋሻ አለመጠቀም ለተመሳሳይ ጉዳት ይደርጋል።




ምልክቶች



· በዚህ ችግር የተጠቁ ሰዎች ለጨረሩ በተጋለጡ በጥቂት ሰዓታት ውስጥ ብዙ ጊዜ በሁለቱም ዓይን ላይ፦

- የዕይታ መቀነስ

- በዕይታ አድማስ ውስጥ የሚታይ ጥላ

- የዕይታ ቅርጽ መዛባት (የሚያዩት ነገር የተጣመመ ፣ በመጠን ያነሰ ወይም የተለቀ መምሰል)

- በተጨማሪም በግንባርና በጭንቅላት ጐን አካባቢ ራስ ምታት ሊከሰት ይችላል፡፡



ይህን ችግር መከሰቱን ለማወቅ የዓይን ምርመራ ማድረግ ያስፈልጋል፡፡ በማይክሮስኮፕ በማየት ወይም ሬቲናውን ፎቶ በማንሳት ወይም OCT በሚባል መሳሪያ በማየት ችግሩ መከሰቱን ማረጋገጥ ይቻላል።




ህክምናው

ምንም እንኳን ይህን ችግር ለማከም የተለያዩ መድኃኒቶች (ስቴሮይድን ጨምሮ) ቢሞክሩም አጥጋቢ ውጤት አላመጡም፡፡ ስለዚህ ዋነኛው ነገር ችግሩ እንዳይከሰት አስቀድሞ መከላከል ነው ።


መከላከያ መንገዶች

- ፀሐይን ፣ ፀሐይ ግርዶሽን ፣ የብየዳ ጨረርና ሌሎች ኃይለኛ ብርሃን የሚረጩ ነገሮችን በቀጥታ አለማየት፣



- በፀሐይ ግርዶሽ በዓመታት አንዴ የሚታይ በመሆኑና ብርሃኑም የቀነሰ ስለሚመስለን ለማየት ሊያጓጓን ይችላል... ሆኖም በፍጹም በቀጥታ ማየት የለብንም



- ህጻናት፣ የአዕምሮ ህመምና ውስንነት ያለባቸውን ሰዎች ወደ ፀሐይ እንዳያዩ መከላከል፣ ጥንቃቄ ማድረግ፣ መርዳት



- የፀሐይ ግርዶሽን ለማየት ዓላማ የተሰሩ ISO እና CE ሰርቲፊኬት ያላቸው ልዕለሐምራዊ (UV) ንዑሰ - ቀይ (Infrared) ጨረሮችን 99 - 1ዐዐ% የሚከላከሉ ጥቁረታቸው (shade no 12) የሆኑ መነጽሮችን ብቻ መጠቀም ይቻላል።



- ሆኖም እንደነዚህ ዓይነት መነጽሮች በሀገራችን ስለመግባታቸው እርግጠኛ አይደለሁም፡፡ ቱሪስቶች ወደእኛ ሀገር ሲመጡ ይዘው ይመጡ ይሆናል፡፡




የተለመዱትን የፀሐይ መነጽሮች ማድረግ ይቻላል ?



· በፍጹም! ምንም እንኳን የፀሐይ መነጽሮች ጐጂ ጨረሮችን መቀነስ ቢችሉም በቀጥታ ወደ ፀሐይ ለማየት ተብሎ ስላልተሰሩ ተጨማሪ ጨረሮችን ወደ ዓይን ያስተላልፋሉና በፍጹም እነዚህን መነጽሮች ተማምነው ወደ ፀሐይ/ ፀሐይ ግርዶሽ ማየት የለብዎትም፡፡



· ጥቁር መነጽር መሆኑ ብቻ ጨረሮቹን ይከላከላል ማለት አይደለም።



- መንግስት ይኽን አጋጣሚ ተጠቅመው ጥራታቸው ያልተረጋገጠ መነጽሮች እንዳይሸጡ ቁጥጥር ማድረግ ይገባዋል።



ምንጭ:- ዶ/ር ጸደቀ አሳምነው

(የዓይን ሐኪም፣ የቪትሮ-ሬቲና ድህረ-ስፔሻሊስት)


ይህንን መረጃ ሼር በማድረግ ለሌሎች ያጋሩ!!



ተጨማሪ የጤና መረጃ እንዲደርሶ፦

የዶክተር ጤና ቴሌግራም ገፅ

t.me/DoctorTena

የዶክተር ጤና ፌስቡክ ገፅ፦

fb.com/DoctorTenaEthiopia

የአሳ ዘይት Dr, Tena - Bethel🖐🖐🖐  ሰላም የዶክተር ጤና ቤተሰቦች!!  🖐🖐🖐ለዘመናት በጠቀሜታው ሲወደስ የኖረውን የአሳ ዘይት የተረጋገጡ ጠቀሜታዎች እናያለን፤ ተከታተሉን፡፡ የአሳ...
06/19/2020

የአሳ ዘይት
Dr, Tena - Bethel

🖐🖐🖐 ሰላም የዶክተር ጤና ቤተሰቦች!! 🖐🖐🖐

ለዘመናት በጠቀሜታው ሲወደስ የኖረውን የአሳ ዘይት የተረጋገጡ ጠቀሜታዎች እናያለን፤ ተከታተሉን፡፡

የአሳ ዘይት

የአሳ ዘይት በጣም ከሚዘወትር የንጥረ-ነገር ሰፕሊመንት አንደኛው ነው፡፡ በኦሜጋ 3 የበለጸገ መሆኑ ለጤና ተመራጭ ያደርገዋል፡፡ የአሳ ዘይት - ዘይት ካላቸው የአሳ አይነቶች የሚዘጋጅ ነው፡፡

ባለለፉት አመታት በተለይ ባደጉት ሀገራት የአሳ ዘይት በጠቀሜታው በጣም የሚደነቅ እና በብዙ የህክምና ባለሙያዎች የሚመከር እንደሆነ ይታወቃል፡፡ በውስጡ እጅግ ጠቃሚ የሆኑ ንጥረ- ምግቦችን በመያዙ በተለይ የልብ በሽታን ለመከላከል ሁነኛ እንደሆነ ይነገራል፡፡

የአሳ ዘይት ጥቅሞች

- የደም ግፊትን ለመቀነስ

- መጥፎ የኮሌስትሮል አይነትን ለመቀነስ

- በደም ስር እና ጉበት ውስጥ የሚከማችን እና የሚጋገር ስብን ለመቀነስ

- የልብን ጤንነት ለመጠበቅ

- የልብ ምት አመታትን ለማስተካከል

- የልብ ድካምን እና የጭንቅላት ውስጥ ደም መፍሰስን ተጋላጭነት ለመቀነስ

- የልብ በሽታ ያለባቸው ሰዎች ላይ ድንገተኛ ሞትን ለመከላከል

- አንዳንድ የስነ-አእምሮ በሽታዎችን ለማከም

- የድብርትን ስሜት ለመቀነስ

- ክብደት ለመቀነስ

- የአይንን ጤንነት ለመጠበቅ

- የሰውነትን ሴሎች መቆጣት ለመቀነስ

- ለጤናማ ቆዳ

- በእርግዝና ወቅት እና ለህፃናት ሁለንተናዊ ጤንነት

- ልጆች ላይ ትኩረትን ለማስተካከል

- የአስምን እና የአለርጂ ምልክቶችን ለመቀነስ

- የአጥንትን ጤንነት ለመጠበቅ

የአሜሪካ የልብ ማህበር ማንኛውም ሰው በሳምንት ቢያንስ ሁለት ጊዜ የአሳ ዘይት እንዲወስዱ ይመከራል፡፡ በቀን ከ3 ግራም በላይ መውሰድ ግን አይመከርም፡፡ የአሳ ውጤቶችን መመገብም የአሳ ዘይት ከመውሰድ አይተናነስም፡፡


ይህንን መረጃ ሼር በማድረግ ለሌሎች ያጋሩ!!



ተጨማሪ የጤና መረጃ እንዲደርሶ፦

የዶክተር ጤና ቴሌግራም ገፅ

t.me/DoctorTena

የዶክተር ጤና ፌስቡክ ገፅ፦

fb.com/DoctorTenaEthiopia

ተአምረኛው ፌጦDr. Tena - Bethel🖐🖐🖐  ሰላም የዶክተር ጤና ቤተሰቦች!!  🖐🖐🖐ለብዙ ችግሮች ሁነኛ መድሐኒት ስለሆነው ፌጦ እናወራለን፡፡ ስለፌጦ  ጥቅም የማያቅ ባይኖርም ሰብሰብ አ...
06/18/2020

ተአምረኛው ፌጦ
Dr. Tena - Bethel

🖐🖐🖐 ሰላም የዶክተር ጤና ቤተሰቦች!! 🖐🖐🖐

ለብዙ ችግሮች ሁነኛ መድሐኒት ስለሆነው ፌጦ እናወራለን፡፡ ስለፌጦ ጥቅም የማያቅ ባይኖርም ሰብሰብ አድርገን ይዘን ቀርበናል፡፡


የፌጦ የጤና ጥቅሞች

ፌጦ (Lapidium sativum) በርካታ በሽታዎችን በመቀነስ ረገድ ትልቅ ድርሻ አለው። በሃበሻ አባባልም "ለሁሉም ፌጦ መድሃኒት ነው" እንል የለ። ለማንኛውም ይህችን ታነቡ ዘንድ ጋበዝን።

1. ለመተንፈሻ አካል ችግር



- ለጉንፋን፣ አስም፣ ሳል፣ ራስ ምታት፣ ለጉሮሮ ቁስል ሁለት ማንኪያ ፌጦ ፈጨት አድርገው ከማር ጋር በመለወስ ይዋጡት፡፡



2. በብረት (iron) ማነስ ምክንያት የሚከሰትን አኒሚያ የተሰኘ በሽታን ለማቃለል



- ከፍተኛ የብረት ማዕድን የያዘው ፌጦ በአንጀታችን ውስጥ በቀላሉ ስለሚመጠጥ በደም ውስጥ የሚገኘውን የሂሞግሎቢን መጠን ይጨምራል፡፡



3. የቆዳ ችግርን ለማስተካከል



- በፀሐይ የተቃጠለ ቆዳ፣ የተቆጣ ቆዳ፣ ደረቅ ቆዳ ካሎት የተፈጨ ፌጦ ከማር ጋር ቀላቅለው ይቀቡት ችግሩን ለማባረር ይረዳዎታል፡፡



4. ለአንጀትና ለሆድ ዕቃ ሕክምና



- ለተቅማጥ፣ ለሆድ ድርቀት እና ለምግብ ያለመንሸራሸር ወይም የመፈጨት ችግር ሁነኛ መፍትሔ ነው፡፡ በተላይ የፌጦ ፍትፍት ምርጥ ነው፡፡



5. ደም ግፊትን ይቀንሳል፣ የተፈጥሮ የበሽታ የመከላከል አቅምን ያጠናክራል



- ጠቃሚ የሆኑ የተለያዩ አሲዶችን ማለትም ፋቲ አሲድ፣ አስፓርቲክ አሲድ፣ ግሉታሚክ አሲድ፣ ሊኖሊክ አሲድ፣ ኦሊክ አሲድ፣ ኦሜጋ 3 ፋቲ አሲድ ያሉት በመሆኑ ደም ግፊትን ይቀንሳል፣ የተፈጥሮ የበሽታ የመከላከል አቅምን ያጠናክራል፣ የደም ስኳር መጠንን ይቀንሳል፣ ለአእምሮ እና የልብ ጤናን ከመጠበቅ በተጨማሪ ድባቴንና ጭንቀት አዲዮስ ያሰኛል፡፡



6. በአየርና በኬሚካል ሳቢያ የሚከሰትን የካንሰር ዓይነት ነጥሎ ይዋጋል

- ፀረ-ብግነት እና ቫይታሚን ኢ ስለያዘ በአየርና በኬሚካል ሳቢያ የሚከሰትን የካንሰር ዓይነት ነጥሎ ይዋጋል፡፡ የሕዋሳትን ውድመት በመከላከሉም ያለዕድሜ ማርጀትን ይከላከላል፡፡



7. የወር አበባ አመጣጥን ያስተካክላል

- ፌጦ የወር አበባ አመጣጥን ያስተካክላል፡፡ እንዲሁም ለምታጠባ እናት የጡት ወተቷን ይጨምራል፡፡

8. የፀጉር መነቀልን ይከላከላል

- መጥፎ የሰውነትን ጠረን ከማስወገዱ በተጨማሪ የፀጉር መነቀልን ይከላከላል፡፡

9. የአይን ጤንና ያሻሽላል



ምን ያህል መወሰድ እንዳለበት በሳይንስ የተረጋገጠ ነገር ባይኖርም የመድሐኒት ያህል በትንሹ ብቻ መጠቀም ይመከራል፡፡

ምንጭ - ኢትዮ-ሳይንስ


ይህንን መረጃ ሼር በማድረግ ለሌሎች ያጋሩ!!



ተጨማሪ የጤና መረጃ እንዲደርሶ፦

የዶክተር ጤና ቴሌግራም ገፅ

t.me/DoctorTena

የዶክተር ጤና ፌስቡክ ገፅ፦

fb.com/DoctorTenaEthiopia

ለውዝ እና ጠቀሜታውDr. Tena - Bethel 🖐🖐🖐  ሰላም የዶክተር ጤና ቤተሰቦች!!  🖐🖐🖐በሀገራችን በብዙ መደብሮች የመይጠፋው ለውዝ ተወዳጅ እንደሆነ ይታወቃል፡፡ ጠቀሜታውን እያወቅን ...
06/17/2020

ለውዝ እና ጠቀሜታው
Dr. Tena - Bethel

🖐🖐🖐 ሰላም የዶክተር ጤና ቤተሰቦች!! 🖐🖐🖐

በሀገራችን በብዙ መደብሮች የመይጠፋው ለውዝ ተወዳጅ እንደሆነ ይታወቃል፡፡ ጠቀሜታውን እያወቅን እንድንመገበው በዛሬው ጥንክራችን እናነሳለን፡፡


ለውዝ

ለውጥ የጥራጥሬ አይነት ሲሆን ከወደ ደቡብ አሜሪካ እንደመጣ ይነገራል፡፡ በተለያዩ ሀገራት የተለያየ ስያሜ አለው፡፡ ለውዝ በፕሮቲን፣ ስብ እና ሌሎች አስፈላጊ ንጥረ ምግቦች እንደ ማግኒዢየም፣ ፋይበር፣ ኮፐር፣ ቫይታሚን ኢ እና አርጂኒን የበለፀገ ነው፤ በአንጻሩ ደግሞ የካርቦሀይድሬት ይዘቱ ዝቅተኛ ነው፡፡ ጥናቶች እናዳመለከቱት ከሆነ ለውዝ ውፍረት ለመቀነስ እና የልብ በሽታ ተጋላጭነትን ለመቀነስ ይረዳል፡፡



ነገር ግን ለለውዝ አለርጂክ የሆኑ ሰዎች በጭራሽ መውሰድ የለባቸውም፡፡ ምክንያቱም መሰል አለርጂዎች ህይወትን ሊቀጥፉ ይችላሉ፡፡



በቀን ሳይበዛ የተወሰኑ የለውዝ ፍሬዎችን መውሰድ እጅግ ይረዳል፡፡



ከለውዝ ጥቅሞች ውስ የተወሰኑት የሚከተሉት ናቸው፤

- በብዙ ጠቃሚ ንጥረ-ምግቦች የበለጸገ ነው

- ከልብ እና ካንሰር በሽታ ይከላከላል

- የድብርትን ስሜት ይቀንሳል

- ከእድሜ ጋር ተያይዞ የሚመጣን የመርሳት በሽታ ይከላከላል

- የማስታወስ ችሎታን ይጨምራል

- የደም ውስጥ ስኳር መጠንን ያስተካክላል

- የሐሞት ጠጠርን ይከላከላል


ይህንን መረጃ ሼር በማድረግ ለሌሎች ያጋሩ!!



ተጨማሪ የጤና መረጃ እንዲደርሶ፦

የዶክተር ጤና ቴሌግራም ገፅ

t.me/DoctorTena

የዶክተር ጤና ፌስቡክ ገፅ፦

fb.com/DoctorTenaEthiopia

Address

Williamsburg, NY
00544

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Doctor Tena posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share

Share on Facebook Share on Twitter Share on LinkedIn
Share on Pinterest Share on Reddit Share via Email
Share on WhatsApp Share on Instagram Share on Telegram

Category

Dr. Tena

Dr. Tena