EthioTena - ኢትዮጤና

  • Home
  • EthioTena - ኢትዮጤና

EthioTena - ኢትዮጤና EthioTena - ኢትዮጤና ገጽን ላይክና ፎሎው በማድረግ አዳዲስ የጤና መረጃዎችን እና ዕለታዊ የጤና ትምህርቶችን ያግኙ! https://linktr.ee/ethiotena

Follow Us On:

ቴሌግራም ቻናል: https://t.me/ethiotenadaniel
ቴሌግራም ግሩፕ: https://t.me/ethiotenadgroup
ኢንስታግራም: https://instagram.com/ethiotena
ቲክቶክ: https://tiktok.com/
ዩቲዩብ: https://youtube.com/channel/UCJkUBphmSRDWD2BvZznwFfg

23/02/2026

እነዚህን የሰውነት የማስጠንቀቂያ ምልክቶች ችላ አትበሉ! | ክፍል-2 | Your Body’s Warning Signs | Part-2 #ኢትዮጤና #ኢትዮጵያ #ኢትዮ

22/02/2026

እነዚህን የሰውነት የማስጠንቀቂያ ምልክቶች ችላ አትበሉ! | ክፍል-1 | Your Body’s Warning Signs | Part-1 #ኢትዮጤና #ኢትዮጵያ #ኢትዮ

💟💖🫀ለልብ ሕመም ተጋላጭ የሚያደርጉ 7 ልምዶች! 💓💝✦────────────────────────✦ብዙዎቻችን በዕለት ተዕለት ህይወታችን የምናደርጋቸው፤ ነገር ግን ሳናውቀው ለልብ ህመም አደጋ የሚ...
22/02/2026

💟💖🫀ለልብ ሕመም ተጋላጭ የሚያደርጉ 7 ልምዶች! 💓💝
✦────────────────────────✦

ብዙዎቻችን በዕለት ተዕለት ህይወታችን የምናደርጋቸው፤ ነገር ግን ሳናውቀው ለልብ ህመም አደጋ የሚዳርጉን ልማዶች አሉ።

👉 ጤናችሁ ያሳስባችኋል?

እንግዲያው እነዚህን 7 ነጥቦች በጥንቃቄ ያንብቧቸው!

✅💟 ለልብ ሕመም የሚያጋልጡን 7 የዕለት ተዕለት ልምዶች! 🫀
――――――――――――――――――――――――――

1️⃣ ቁርስ መዝለል!
•••••••••••••••••••

ቁርስ አለመብላት የደም ስኳር መጠን እንዲዛባ እና የኮሌስትሮል መጠን እንዲጨምር ያደርጋል።

ይህ ደግሞ በሂደት ለልብ ህመም ይዳርጋል። ቀንዎን በጤናማ ቁርስ ይጀምሩ!

2️⃣ ለረጅም ሰዓት ተቀምጦ ማሳለፍ!
••••••••••••••••••••••••••••••••••••

በቢሮ ሥራ ወይም በሌላ ምክንያት ለረጅም ሰዓት ሳይንቀሳቀሱ መቀመጥ የደም ዝውውርን ያቀዘቅዛል፤ የደም ግፊትንም ይጨምራል።

አልፎ አልፎ እየተነሱ መንቀሳቀስን አይርሱ።

3️⃣ በፋብሪካ የተቀነባበሩ ምግቦችን ማብዛት!
•••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••

በፋብሪካ የተቀነባበሩ፣ በዘይት የተጠበሱ እና የታሸጉ ምግቦች የደም ቱቦዎችን የመድፈን ዕድላቸው ሰፊ ነው።

ይህ ደግሞ ለውፍረት እና ለልብ ህመም መነሻ ነው።

4️⃣ ከፍተኛ ጭንቀት!
•••••••••••••••••••••

ጭንቀት የአእምሮ ጉዳይ ብቻ አይደለም!

በምንጨነቅበት ወቅት የደም ግፊታችን ይጨምራል፤ ይህ ደግሞ ለልብ ህመም ዋና መንስኤ ነው።

አእምሮን ዘና ማድረግ ለልብ ጤና ወሳኝ ነው።

5️⃣ በቂ እንቅልፍ አለማግኘት!
••••••••••••••••••••••••••••••

እንቅልፍ ማጣት ልባችንን ይጎዳል እንዲሁም በሰውነታችን ውስጥ ያለውን የሆርሞን ሚዛን ያዛባል።

በቀን ውስጥ ቢያንስ ከ 7 እስከ 8 ሰዓት መተኛት ለጤናማ ልብ ይመከራል።

6️⃣ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ አለማድረግ!
••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••

ስፖርት ለመሥራት የግድ "ጂም" መግባት አይጠበቅብንም።

ቀላል የእግር ጉዞ ማድረግ እንኳን ልብን ከተለያዩ በሽታዎች ለመታደግ ይረዳል።

እንቅስቃሴ የልብ ምርጥ ጓደኛ ነው።

7️⃣ ጨው እና ስኳር ማብዛት!
•••••••••••••••••••••••••••••

በምግብ ውስጥ ጨው እና ስኳርን ማብዛት የደም ቱቦዎችን ይጎዳል፤ ለደም ግፊትም ያጋልጣል።

መጠኑን መቀነስ ለጤናችን ዋስትና ነው።

👉 ጤናችን ሀብታችን ነው! እነዚህን ልማዶች በማስተካከል ራሳችንን ከልብ በሽታ እንጠብቅ።

💬 መረጃው ለሌሎች እንዲደርስ Like እና Share በማድረግ ለወዳጅ ዘመድዎ ያካፍሉ! 💚

🔄 ተጨማሪ የጤና መረጃዎችን ለማግኘት EthioTena - ኢትዮጤና የፌስቡክ ገጻችንን (Follow) ያድርጉ። 💙

💖 መልካም ጤንነት! 💖

▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰

ለበለጠ የጤና መረጃ ኢትዮጤና የፌስቡክ ገጽን ላይክ፣ ሼር፣ እና ፎሎው ያድርጉ!

👇🏼👇🏼👇🏼👇🏼👇🏼👇🏼👇🏼👇🏼
https://linktr.ee/ethiotena

▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰

#ልብ #የልብጤና #የልብበሽታ #የልብበሽታንመከላከል #ጤናማልምዶች #የልብናየደምቱቦጤና #የደምግፊትንመቆጣጠር #ጤናማየአኗኗርዘይቤ #እንቅልፍለጤንነት #ጭንቀትንመቆጣጠር #በጥንቀቄይመገቡ #እንቅስቃሴያድርጉ #የህብረተሰብጤና #ጤና #ኢትዮጤና

🔍 ምንጮች | 📚 Sources Websites
•••••••••••••••••••••••••••••••••••••••

1) Centers for Disease Control and Prevention (CDC)

Title: Heart Disease Basics
Full URL: https://www.cdc.gov/heartdisease/about.htm

2) American Heart Association (AHA)

Title: Prevention and Treatment of High Blood Pressure
Full URL: https://www.heart.org/en/health-topics/high-blood-pressure

3) World Health Organization (WHO)

Title: Cardiovascular Diseases (CVDs)
Full URL: https://www.who.int/news-room/fact-sheets/detail/cardiovascular-diseases-(cvds)

4) National Heart, Lung, and Blood Institute (NHLBI)

Title: Coronary Heart Disease
Full URL: https://www.nhlbi.nih.gov/health/coronary-heart-disease

5) Harvard T.H. Chan School of Public Health

Title: The Nutrition Source – Salt and Sodium
Full URL: https://www.hsph.harvard.edu/nutritionsource/salt-and-sodium/

6) National Institute of Diabetes and Digestive and Kidney Diseases (NIDDK)

Title: Health Risks of Overweight & Obesity
Full URL: https://www.niddk.nih.gov/health-information/weight-management/health-risks-overweight

21/02/2026

🫀 ለልብ ህመም የሚያጋልጡን 7 የዕለት ተዕለት ልምዶች! | ክፍል-2 | 🫀 7 Everyday Habits That Put Us at Risk for Heart Disease! | Part-2 #ኢትዮጵያ #ኢትዮ #ኢትዮጤና

21/02/2026

🫀 ለልብ ህመም ተጋላጭ የሚያደርጉ 7 የተለመዱ የዕለት ተዕለት ልምዶች! | ክፍል - 1 | 7 Normal Habits That May Increase the Risk of Heart Attacks | Part-1 | #ኢትዮጵያ #ኢትዮ #ኢትዮጤና

💧🚰 የውኃ እጥረት መኖሩን የሚያሳዩ 14 ምልክቶች! 💦 🧊✦────────────────────────✦🚏 ክፍል - 2 | Part - 2 🚏――――――――――――የውኃ ወይም የፈሳሽ እጥረት (Dehyd...
21/02/2026

💧🚰 የውኃ እጥረት መኖሩን የሚያሳዩ 14 ምልክቶች! 💦 🧊
✦────────────────────────✦

🚏 ክፍል - 2 | Part - 2 🚏
――――――――――――

የውኃ ወይም የፈሳሽ እጥረት (Dehydration) በሰውነታችን ላይ የተለያዩ የጤና እክሎችን ሊያስከትል ይችላል።

በሰውነታችን ውስጥ የውሃ መጠን መቀነሱን የሚጠቁሙ 14 ዋና ዋና ምልክቶች የሚከተሉት ናቸው፦

✅💧የውኃ እጥረት መኖሩን የሚያሳዩ 14 ምልክቶች!🚰
――――――――――――――――――――――――――

8️⃣ የጡንቻ መሸማቀቅ፦
•••••••••••••••••••••••••

በሰውነት ውስጥ እንደ ሶዲየም እና ፖታሺየም ያሉ ኤሌክትሮላይቶች መዛባት የነርቭ እና የጡንቻ ስራን ያውካል።

9️⃣ የምግብ ፍላጎት መቀነስ፦
••••••••••••••••••••••••••••

ሰውነታችን ያለውን የውሃ ክምችት ለመቆጠብ በሚሞክርበት ጊዜ የረሃብ ስሜትን የሚቀሰቅሱ ምልክቶችን ሊያጠፋ ይችላል።

🔟 ማዞር፦
••••••••••••

የፈሳሽ መጠን መቀነስ የደም ግፊት እንዲቀንስ ስለሚያደርግ፤ የራስ መቅለል ወይም የማዞር ስሜት ይፈጥራል።

1️⃣1️⃣ መጥፎ የአፍ ጠረን፦
•••••••••••••••••••••••••••

የምራቅ ምርት ስለሚቀንስ ባክቴሪያዎች በአፍ ውስጥ እንዲራቡ ምቹ ሁኔታ ይፈጠራል፤ ይህም ለመጥፎ የአፍ ጠረን ይዳርጋል።

1️⃣2️⃣ ግራ መጋባት ወይም መደናገር፦
••••••••••••••••••••••••••••••••••••

አንጎል የኤሌክትሪክ መልእክቶችን ለማስተላለፍ በውሃ ላይ የተመሰረተ ሚዛን ያስፈልገዋል፤ የውሃ እጥረት ደግሞ ይህንን ሂደት ያውካል።

1️⃣3️⃣ የልብ ምት መጨመር፦
•••••••••••••••••••••••••••••

ደም በመወፈሩ ምክንያት ወይም ስለሚወፍር፤ ልብ ደምና ኦክስጅንን ለተለያዩ የሰውነት ክፍሎች ለማድረስ ሲል በከፍተኛ ፍጥነት ይመታል።

1️⃣4️⃣ የእጅ እና የእግር መቀዝቀዝ፦
•••••••••••••••••••••••••••••••••••

የሰውነትን የውስጥ ሙቀት ለመጠበቅ ሲባል የደም ስሮች ስለሚኮማተሩ፤ ወደ እጅ እና እግር የሚሄደው የደም ዝውውር ይቀንሳል።

💥👉 እነዚህ ምልክቶች ከታዩብን በአፋጣኝ ውሃ ወይም ፈሳሽ ነገሮችን በመውሰድ ሰውነታችንን ማነቃቃት ይኖርብናል።

እነዚህን ምልክቶች ለመከላከል በቀን ውስጥ በቂ ውሃ መጠጣትዎን አይዘንጉ።

💬 ይህ መረጃ ጠቃሚ ሆኖ ካገኙት (Like) እንዲሁም ለወዳጅዎ (Share) ያድርጉ! 💚

🔄 ተጨማሪ የጤና መረጃዎችን ለማግኘት EthioTena - ኢትዮጤና የፌስቡክ ገጻችንን (Follow) ያድርጉ። 💙

▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰

ለበለጠ የጤና መረጃ ኢትዮጤና የፌስቡክ ገጽን ላይክ፣ ሼር፣ እና ፎሎው ያድርጉ!

👇🏼👇🏼👇🏼👇🏼👇🏼👇🏼👇🏼👇🏼
https://linktr.ee/ethiotena

▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰

#ውሃ #ውሃይጠጡ #ድርቀት #ድርቀትንመከላከል #ውሃበደንብይጠጡ #ጤናማልምዶች #የመከላከያእርምጃዎች #የጤናትምህርት #የጤናመረጃ #ጤና #ኢትዮጤና

🔍 ምንጮች | 📚 Sources Websites
•••••••••••••••••••••••••••••••••••••••

1. MedlinePlus – Dehydration

Website: U.S. National Library of Medicine
Full URL: https://medlineplus.gov/dehydration.html

2. Mayo Clinic – Dehydration

Website: Mayo Clinic
Full URL: https://www.mayoclinic.org/diseases-conditions/dehydration/symptoms-causes/syc-20354086

3. Cleveland Clinic – Dehydration: Symptoms & Causes

Website: Cleveland Clinic
Full URL: https://my.clevelandclinic.org/health/diseases/9013-dehydration

4. Centers for Disease Control and Prevention (CDC) – Dehydration

Website: CDC
Full URL: https://www.cdc.gov/nutrition/data-statistics/plain-water-the-healthier-choice.html

5. National Health Service (NHS) – Dehydration

Website: NHS (UK)
Full URL: https://www.nhs.uk/conditions/dehydration/

💧🚰 የውኃ እጥረት መኖሩን የሚያሳዩ 14 ምልክቶች! 💦 🧊✦────────────────────────✦🗼ክፍል - 1 | Part - 1🗼―――――――――――የውሃ ወይም የፈሳሽ እጥረት (Dehydrat...
20/02/2026

💧🚰 የውኃ እጥረት መኖሩን የሚያሳዩ 14 ምልክቶች! 💦 🧊
✦────────────────────────✦

🗼ክፍል - 1 | Part - 1🗼
―――――――――――

የውሃ ወይም የፈሳሽ እጥረት (Dehydration) በሰውነታችን ላይ የተለያዩ የጤና እክሎችን ሊያስከትል ይችላል።

በሰውነታችን ውስጥ የውሃ መጠን መቀነሱን የሚጠቁሙ 14 ዋና ዋና ምልክቶች የሚከተሉት ናቸው፦

✅💧የውሃ እጥረት መኖሩን የሚያሳዩ 14 ምልክቶች!🚰
――――――――――――――――――――――――――

1️⃣ ራስ ምታት፦
••••••••••••••••

አንጎል በፈሳሽ እጥረት ምክንያት በጊዜያዊነት ስለሚኮማተር ወይም (መጠኑ ስለሚቀንስ)፣ ከራስ ቅል ግድግዳ ጋር የሚያገናኙትን ጥቃቅን ነርቮችን በመሳብ ወይም በመጎተት የሕመም ስሜት ያስከትላል።"

ይህ ሂደት ሰውነታችን የውሃ ጥም ሲበረታበት የሚፈጠር የፊዚዮሎጂ ለውጥ ሲሆን፤ ለራስ ምታት ዋነኛው ምክንያት ነው።

2️⃣ የአፍ መድረቅ፦
•••••••••••••••••••

አብዛኛውን ጊዜ ሰውነታችን ተጨማሪ ውሃ ወይም ፈሳሽ እንደሚያስፈልገው የሚያሳይ የመጀመሪያው ግልጽ ምልክት ነው።

3️⃣ ከፍተኛ የውሃ ጥም፦
•••••••••••••••••••••••••

ሰውነታችን ውሃ በአስቸኳይ ማግኘት እንዳለበት የሚሰጠው ቀጥተኛ መልእክት ነው።

4️⃣ ድካም፦
••••••••••••

የደም መጠን ስለሚቀንስ እና ደም ስለሚወፍር፣ ልባችን ጠንክሮ ወይም በርትቶ እንዲሰራ ያስገድደዋል፤ ይህም ለከፍተኛ ድካም ይዳርጋል።

5️⃣ የቆዳ መድረቅ፦
•••••••••••••••••••

የቆዳ ሴሎች በቂ ውሃ ሲያጡ፤ ቆዳችን ወዙን፣ ልስላሴውንና የመለጠጥ ባህሪውን ያጣል።

6️⃣ የዓይን መጥቆር ወይም ማሳከክ፦
••••••••••••••••••••••••••••••••••••

የእንባ አመንጪ እጢዎች ስለሚደርቁ፤ ለዓይን ማቃጠል እና መቅላት ምክንያት ይሆናል ወይም ይዳርጋል።

7️⃣ የሽንት ቀለም መጥቆር፦
•••••••••••••••••••••••••••

ኩላሊቶቻችን ውሃን በሰውነት ውስጥ ስለሚይዙ ወይም (ስለሚቋጥሩ)፣ ሽንት በመርዛማ ኬሚካሎች የተሞላ እና ቀለሙ በጣም የጠቆረ ይሆናል።

💬 ይህ መረጃ ጠቃሚ ሆኖ ካገኙት (Like) እንዲሁም ለወዳጅዎ (Share) ያድርጉ! 💚

🔄 ተጨማሪ የጤና መረጃዎችን ለማግኘት EthioTena - ኢትዮጤና የፌስቡክ ገጻችንን (Follow) ያድርጉ። 💙

▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰

ለበለጠ የጤና መረጃ ኢትዮጤና የፌስቡክ ገጽን ላይክ፣ ሼር፣ እና ፎሎው ያድርጉ!

👇🏼👇🏼👇🏼👇🏼👇🏼👇🏼👇🏼👇🏼
https://linktr.ee/ethiotena

▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰

#ውሃ #ውሃይጠጡ #ድርቀት #ድርቀትንመከላከል #ውሃበደንብይጠጡ #ጤናማልምዶች #የመከላከያእርምጃዎች #የጤናትምህርት #የጤናመረጃ #ጤና #ኢትዮጤና

🔍 ምንጮች | 📚 Sources Websites
•••••••••••••••••••••••••••••••••••••••

1. MedlinePlus – Dehydration

Website: U.S. National Library of Medicine
Full URL: https://medlineplus.gov/dehydration.html

2. Mayo Clinic – Dehydration

Website: Mayo Clinic
Full URL: https://www.mayoclinic.org/diseases-conditions/dehydration/symptoms-causes/syc-20354086

3. Cleveland Clinic – Dehydration: Symptoms & Causes

Website: Cleveland Clinic
Full URL: https://my.clevelandclinic.org/health/diseases/9013-dehydration

4. Centers for Disease Control and Prevention (CDC) – Dehydration

Website: CDC
Full URL: https://www.cdc.gov/nutrition/data-statistics/plain-water-the-healthier-choice.html

19/02/2026

💧🚰 የውሃ ወይም የፈሳሽ እጥረት መኖሩን የሚያሳዩ 14 ምልክቶች! | ክፍል-2 | 14 Warning Signs You Are Dehydrated | Part-2 | #ኢትዮጵያ #ኢትዮ #ኢትዮጤና

19/02/2026

💧🚰 በሰውነታችን ውስጥ የውሃ እጥረት መኖሩን የሚጠቁሙ 14 የማስጠንቀቂያ ምልክቶች | ክፍል-1 | 14 Warning Signs You Are Dehydrated | Part-1 #ኢትዮጵያ #ኢትዮ #ኢትዮጤና

🧴☕️ ቆዳችን እንዲጠቁር ወይም ቀለሙን እንዲቀይር የሚያደርጉ 9 ልምዶች! | 9 Habits That Are Making Your Skin Darker! 🎯✦────────────────────────✦👉...
18/02/2026

🧴☕️ ቆዳችን እንዲጠቁር ወይም ቀለሙን እንዲቀይር የሚያደርጉ 9 ልምዶች! | 9 Habits That Are Making Your Skin Darker! 🎯
✦────────────────────────✦

👉 ለቆዳ መጥቆር ወይም መልክ/ቀለም መበላሸት መንስኤ ሊሆኑ የሚችሉ 9 ልማዶች የሚከተሉት ናቸው፦

1️⃣ ያለ መከላከያ ለፀሐይ ብርሃን ጨረር መጋለጥ!
•••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••

ቆዳን ከፀሐይ ብርሃን አልትራቫዮሌት ጨረር የሚከላከል ሰን ስክሪን ክሬም ሳይቀቡ ለፀሃይ ብርሃን መጋለጥ።

2️⃣ በቂ ውሃ አለመጠጣት!
•••••••••••••••••••••••••••

ሰውነታችን በቂ ፈሳሽ ሲያጣ ወይም የሚፈልገውን ያህል ውሃ ካላገኘ ቆዳ የመድረቅ፣ የመጥቆር፣ እና የመገርጣት ዝንባሌ ያሳያል።

3️⃣ በቂ እንቅልፍ አለማግኘት!
••••••••••••••••••••••••••••••

እንቅልፍ ማጣት የቆዳ ሴሎች ራሳቸውን እንዲያድሱ ዕድል አይሰጣቸውም።

4️⃣ ፊትን በሙቅ ውሃ መታጠብ!
••••••••••••••••••••••••••••••••

በጣም ትኩስ ውሃ የቆዳን ተፈጥሯዊ ዘይት በማጥፋት ለቆዳ መድረቅና መጥቆር ይዳርጋል።

5️⃣ ለቆዳ የማይስማሙ ምርቶችን መጠቀም!
••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••

ከቆዳዎ አይነት ጋር የማይሄዱ ወይም ለቆዳ አይነታችን የማይስማሙ የውበት መጠበቂያዎችን መጠቀም ለቆዳ መቆጣትና ቀለም መለዋወጥ ምክንያት ይሆናል።

6️⃣ ማጨስ!
•••••••••••••

ሲጋራ ማጨስ ወደ ቆዳ የሚሄደውን የደም ዝውውር በመቀነስ ቆዳ ጤናማ ያልሆነ መልክ እንዲኖረው ወይም የቆዳ ቀለም እንዲለወጥ ያደርጋል።

7️⃣ ቆዳን በኃይል ማሸት ወይም መፈግፈግ!
••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••

ቆዳን ከመጠን በላይ ወይም በሃይል ማሸት የቆዳ መቆጣትንና የቆዳ መጥቆርን ያስከትላል።

8️⃣ ለከፍተኛ ጭንቀት መጋለጥ!
••••••••••••••••••••••••••••••••

የማያቋርጥና ለረጅም ጊዜ የሚቆይ የአእምሮ ጭንቀት በሰውነታችን ውስጥ የሆርሞን መዛባትን በመፍጠር ለቆዳ መበላሸት ምክንያት ይሆናል።

9️⃣ የቆዳ ማቅለሚያ (ብሊቺንግ) ክሬሞችን መጠቀም!
•••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••

እነዚህ ክሬሞች በውስጣቸው ባሉ ጠንካራ ኬሚካሎች ምክንያት በጊዜ ሂደት ቆዳን ያበላሻሉ እንዲሁም ያጠቁራሉ።

💡 ጤናማ ቆዳ በአንድ አዳር አይመጣም! እነዚህን ልማዶች ቀስ በቀስ በማስተካከል የቆዳዎን ውበት ይጠብቁ።

💬 ይህ መረጃ ጠቃሚ ሆኖ ካገኙት (Like) እንዲሁም ለወዳጅዎ (Share) ያድርጉ! 💚

🔄 ተጨማሪ የጤና መረጃዎችን ለማግኘት EthioTena ገጻችንን (Follow) ያድርጉ። 💙

▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰

ለበለጠ የጤና መረጃ ኢትዮጤና የፌስቡክ ገጽን ላይክ፣ ሼር፣ እና ፎሎው ያድርጉ!

👇🏼👇🏼👇🏼👇🏼👇🏼👇🏼👇🏼👇🏼
https://linktr.ee/ethiotena

▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰

#ቆዳ #ደርማቶሎጂ #ሜላኒን #ጤና #ኢትዮጤና

🔍 ምንጮች | 📚 Sources Websites
•••••••••••••••••••••••••••••••••••••••

1. American Academy of Dermatology (AAD)
Title: Hyperpigmentation: Overview
URL: https://www.aad.org/public/diseases/a-z/hyperpigmentation-overview

2. American Academy of Dermatology (AAD)
Title: How to Prevent and Treat Hyperpigmentation
URL: https://www.aad.org/public/everyday-care/skin-care-basics/dark-spots

3. Harvard Health Publishing
Title: The Importance of Protecting Your Skin from the Sun
URL: https://www.health.harvard.edu/staying-healthy/the-importance-of-sun-protection

4. DermNet NZ (Dermatology Resource)
Title: Post-Inflammatory Hyperpigmentation
URL: https://dermnetnz.org/topics/postinflammatory-hyperpigmentation

5. National Institute on Aging (NIH)
Title: Skin Care and Aging
URL: https://www.nia.nih.gov/health/skin-care-and-aging

ለመላው የእስልምና እምነት ተከታዮች፤እንኳን ለ1447ኛው  የረመዷን ወር በሠላም አደረሳችሁ!  #ረመዳን  #ጾም    #ሙስሊም
18/02/2026

ለመላው የእስልምና እምነት ተከታዮች፤

እንኳን ለ1447ኛው የረመዷን ወር በሠላም አደረሳችሁ!

#ረመዳን #ጾም #ሙስሊም

18/02/2026

🥗🍱 ተፈጥሯዊ ምግቦች ለእውነተኛ ጤንነት! ክፍል-2 | REAL FOOD SUPPORTS REAL HEALTH | Part-2 🍲 #ኢትዮጤና #ኢትዮጵያ #ኢትዮ

Address


Alerts

Be the first to know and let us send you an email when EthioTena - ኢትዮጤና posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

  • Want your practice to be the top-listed Clinic?

Share

Share on Facebook Share on Twitter Share on LinkedIn
Share on Pinterest Share on Reddit Share via Email
Share on WhatsApp Share on Instagram Share on Telegram